Connect with us

በእውቀቱ፣ በጥሪቱና በሕይወቱ ለሀገሩ የቆመው ምሁር

በእውቀቱ፣ በጥሪቱና በሕይወቱ ለሀገሩ የቆመው ምሁር

ባህልና ታሪክ

በእውቀቱ፣ በጥሪቱና በሕይወቱ ለሀገሩ የቆመው ምሁር

በእውቀቱ፣ በጥሪቱና በሕይወቱ ለሀገሩ የቆመው ምሁር
ጌትነት አልማው ጥሩነህ!
(ሄኖክ ስዩም ~ድሬቲዩብ)

ይገርመኛል፡፡ ይበጃል ያለውን ሀሳብ ለሀገሩ ከመስጠት ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም፡፡ በምክንያት ለመሞገት አደባባይ መውጣትን ይፈራም፡፡ ለምስማማበትም ለማልስማማበትን ሀሳቡ ልዩ ክብር የምሰጠው በተለየ መልኩ ምን አገባኝ ብሎ ቤቱ የተቀመጠ ምሁር ባለመሆኑ ነው፡፡

ፖለቲካውን ለማቅናት እውቀት ይዞ አውዱን ከመቀላቀሉ በላይ ምሁር ነው፡፡ በተማረበት ሙያ ሀገርና ወገን ለማገልገል ታላቁ መካነ አእምሮ ውስጥ በመምህርነት ያገለግላል፡፡ ረዳት ፕሮፌሰሩ ጌትነት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያስተምራል፡፡
Getnet Almaw Tiruneh – ጌትነት አልማው ጥሩነህ ትህነግ ወረራ ሲጀምር የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን ክተት ተከትሎ ደግሞ ሀገሬን እንዲህ ባለ ሰዓት በህይወቴ ነው የማገለግላት በማለት ወደ ግንባር ዘመተ፡፡ አሁን በጠለምት ግንባር ለሀገሩ ክብር ተሰልፎ ይገኛል፡፡

እኔ ተንታንኝ ነኝ፤ ምን ግንባር ወስዶ የግንባር ስጋ አደረገኝ ካላሉት ወገን ስሙን በታሪክ አጽፏል፡፡ የአቅሙን ለማድረግ ሲጀግን ለእናት ሀገር ህይወቱን ለመስጠት መወሰኑ ነው፡፡ በዚህ እጅግ ሊከበር ይገባል፡፡

የሚገርመው ነገር ከተሰለፈበት ግንባር ሆኖ ደግሞ ለምሁራንና ለደጀኑ የቀረውን ጥሪ አቤት ለማለት የሚቀድመው የለም፡፡ በሳይበር የገጠመንን ጦርነት ከጦርነት ቦታ ሆኖ ተቀላቅሏል፡፡ ፕሮፖጋንዳ እየመከተ ያለው ጥይት ከሚተኮስበት ግንባር ሆኖ ነው፡፡

ጌትነት በፌስ ቡክና በቲውተር በሚደረጉ ዘመቻዎች ንቁ ተሳታፊ ነው፡፡ ደጀንም ወታደርም በመሆን ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል፡፡ ደግሞ ሰሞኑን በወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተጠራውን የድጋፍ እናድርግ ዘመቻ እዚያ ሆኖ በጥሪቱ አለሁ አለ፡፡

ምሁሩ በማህበራዊ ሚዲያ የፌስ ቡክ ገጹ ድርጊቱን መሰል ወገኖቹ ይጋሩት ዘንድ እንዲህ ብሎ ከልመና ጋር አጋራ
“ለወሎ ወገኖቻችን እጃችንን እንዘርጋ ለደጉ የወሎ ወገናችን ካለን ሳይሆን ከሌለን የመስጠት የሞራል ግዴታ ስላለብን ብር 5,000 (አምስት ሺሕ ብር ብቻ) የቀን ልብ ባለቤቶች በመሰረቱት “ወሎ ኅብረት – Wollo Hibret የልማትና በጎ አድራጎት” ሒሳብ ገቢ አድርገናል!!

ወራሪው፣ ጨፍጫፊውና አሸባሪው የትግራይ ሃይል ከደጉ የወሎ ምድር ተነቅሎ ወገኔ ወደ ቀዬው ተመልሶ ኑሮውን እስኪጀምርና እስኪቋቋም ድረስ ድጋፌ የማይቋረጥ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ!!
መስጠት መታወቂያው ደግነት መገለጫው ለሆነው የወሎ ሕዝብ የበጎነት እጅዎትን ይዘርጉ!!”

በተሰለፈበት ግንባር ሆኖ የድል ዜናዎችን ከማብሰር ባሻገር ወጣቶች ሀገራቸውን ይታደጉ ዘንድ ለሀገራችሁ ቁሙ ብሎ ይቀሰቅሳል፡፡ የወራሪው የትህግን ሴራ ሀሰትና ተንኮል ያጋልጣል፡፡ ዓለም አቀፋዊ በሆነው አውድ ለሀገሩ የሳይበር ሠራዊት ሆኖ ይፋለማል፡፡ የጥይት ድምጽ ከሚሰማበት ግንባር ነገ ብሩህ እንደሚሆን አምኖ ተስፋን ያካፍላል፡፡

እንዲህ ለወገን እንድረስ ጥሪንም ቢሆን ሩቅ እና የማይመች ቦታ ነኝ አይልም፡፡ አቤት ብሎ ካለው ያካፍላል፡፡ ካላችሁ አካፍላችሁ ይሄንን ቀን እንለፍ ብሎ ወገን ይቀሰቅሳል፡፡ እንዲህ ያለ ብዙ ተግባር የሚያስመሰግን ነውና ጌትነት ጥሩነህ አልማውን በእናት ሀገራችን፣ በህዝቦቿና ስለ ክብሯ በወደቁ አበው ሰማዕታት ስም እናመሰግነዋለን፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top