Connect with us

ወይ አለማወቅ?!

ወይ አለማወቅ?!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ወይ አለማወቅ?!

ወይ አለማወቅ?!

“አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም” በማለት የህግ ሙያተኞች ደጋግመው የሚጠቅሱት አባባል እንዲህ ላለው ተግባር በግድም በውድም መሥራት አለበት። “አውቀው በድፍረት” ወይም “ሳያውቁ በስህተት” ቢፈጽሙት ለውጥ አያመጣም፤ ምክንያቱም “ስህተቱን” ስህተት ከመሆን  አያድነውምና/አላዳነውምና። 

የኮንክሪቱ ቀለም በቂና ተገቢ፣  ቋሚ ቀለም ሆኖ ሳለ፣ ተፈጥሯዊ መልኩንና የሕንጻውን ቀልብ የሚያሳጣ ነጭና ሰማያዊ ቀለም እንዲቀባ ተፈረደበት። ይህ ውሳኔ ስህተትም አላዋቂነትም ነው። ሕንጻው በኬሚካል መታጠብ ብቻውን በቂ ነበር።

ሰሚው ክፍል ስሞታ ካደመጠ ስህተቱ ሊታረም፤ ህንጻውም፣ እንደሚገባው ሊታደስ/ሊታከም ይችላል።  ላላስፈላጊ ጫጫታና ሆታ የዳረጉንም አካላት “ተጠያቂነት” እንዳለ ቢማሩ መልካም ነው። ብዙኃኑን ይመራሉ፥ ያስተምራሉ፥ ቀና መንገድ ያመላክታሉ የተባሉ እንዲህ በህዝብ ወጀብና ሆታ የሚመሩ ከሆነ፥ “ስንት የማናየውና የማናውቀው ስህተት ተፈጽሞ ይሆን?” ማስባሉ አይቀርም።

#አገኘሁ_አዳነ_ድልነሣሁ

4/01/2014

***

#በቀለ_መኮንን

በዚች ሰዓት በኪዳኔ በየነ ህንፃ ላይ እየተፈፀመ ያለው ወንጀል የዛሬ አራትና አምስት ዓመት በምኒልክ ሀውልት ላይ ከተፈፀመው ጋር ፍፁም ተመሣሣይ ነው። የምኒልክ ሀውልት ያኔ ሲጫወቱበት መልኩን እንዲያብረቀርቅ  አድርገው  ነበርና የላዩን ወርቅማ ቀለም እንጂ የውስጡን ወንጀል  ብዙሃኑ እስከዛሬም ያወቀ አይመሥለኝም።

የነሀስ ሀውልት ያውም ያደባባይ ቅርፅ  በየትኛውም ዘመን በየትኛውም ሀገር ቀለም ተቀብቶ አያውቅም። ሙያዊ ነውር ስለሆነ። ነገር ግን ኬሚካላዊ ሂደትን አልፎ የራሱ ቀለም እንዲኖረው የሚደረግበት  ነባር ስርዓት አለው ። እየነገርናቸው አሻፈረኝ ብለው ነሀስን  ቀለም የቀባች  ብቸኛ  የደንቆሮ አገር ሰዎች አርገው ያዋረዱን እነሆ አሁን ደግሞ ይሁነኝ ብለው  ከነመልኩ አልቆለት  የተገነባን  ህንፃ ዳግም የጥፋት ቀለም እየለቀለቁት  ነው ፣ እግዚኦ !

አሁን  እንኳ እንደያኔው ብዙ  የማስጠንቀቂያ ጩኸት አልተሰማም።ለነገሩ  እነሱ የቀደመ ጩኸትም ሆነ የዘገየን  ምክር ከጉዳይ ባይጥፉም።

የምኒልክ ሀውልት ከተተከለ ጀምሮ ጣሊያኖች በጠላትነት አንዴ   ሲያበላሹት እኛ ግን  ተዉ እየተባልን በድንቁርና ሶስት ጊዜ አበላሽተነዋል። የመጨረሻው ብልሽት የዛሬ አራት ዓመት ከመፈፀሙ በፊት እባካችሁ ሀገሪቱን አታዋርዱ ስራው መካሄድ ያለበት በዚህ በዚህ መንገድ ብቻ ነው የሚል ብዙ ኡኡታ ከጊዜው ባህል ሚኒስትር እስከ ሳይት ላይ ሰራተኛ እንዲደርሰው ተደርጎ ነበር። 

 ማንም ከቁብ ሳይቆጠር ለሳንቲም ቅርምት ሲባል አግባብ ባልሆነ መንገድ ጥፋት ተፈፅሞበት ለጥፋት መሸፈኛ እንደ ስኒ የሚያብረቀርቅ ወርቅማ ቀለም ይለቀለቅ ዘንድ ተፈርዶበት ይኸው አሁን በሙቀትና በቅዝቃዜ እየረገፈ ገመናው መታየት  ጀምሯል።ዝገቱም በቅርብ ወራት መገለጥ  ይጀምራል።አሻግሮ ማለም  ደክሞን  የዕለት የዕለቱን ብቻ እያየን ላብረቀረቀ ሁሉ ያለጥርጥር እንደምናጨበጭብ ሹመኛና  ጉልበተኛ አወቀብን። አራዳ ጊዮርጊስ ሙያዊ ወንጀል መፈፀሙን ብዙዎቻችን እስከዛሬም የምናውቅ አልመሠለኝም።

ቤትን ወይም ሀውልትን ሰርቶ   ከማቆም ቀጥሎ የሚመጣው ዝርዝር  የፍፅምና ጉዳይ ለሀገራችን ጉልበተኞችና  በላተኞች የቅንጦት እንጂ የህይወት ዋነኛ  ክፍል መሆኑ እስቲገለጥላቸው ክርስቶስ ተመልሶ እንዳይመጣ እሰጋለሁ።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top