Connect with us

እንደወልቃይትና ራያ ሁሉ መከላከያም «ርስታችን» ነው (? )!

Social media

ነፃ ሃሳብ

እንደወልቃይትና ራያ ሁሉ መከላከያም «ርስታችን» ነው (? )!

እንደወልቃይትና ራያ ሁሉ መከላከያም «ርስታችን» ነው (? )!
(ክርስቲያን ታደለ)

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአማራ ወጣት ወደ መከላከያ እንዳይገባ አሉታዊ ቅስቀሳ የምታደርጉ ሁሉ በዚህ ድርጊታችሁ የምትፀፀቱበት ቀን ሩቅ አይደለም።
እኛ ወጣቱ መከላከያን እንዲቀላቀል የምንወተውተው በቀጣይ የሚመጣውን ወጀብ ብርቱነት በአንፃራዊነት ቀርበን ስለገመገምን ነው።

ትናንት ወጣቱ ልዩ ኃይሉን እንዲቀላቀል ጥሪ በማቅረባችን ቢያንስ ስለነገ ለመወካከር ጊዜ መግዣ ሆኖናል። ወጣቶቻችን ልዩ ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ስናስተላልፍ ሲቃወሙ የነበሩ ወገኖች ዛሬ ላይ ተፀፅተው ነጋችንን በሚበይነው መከላከያን የመገንባት ተልእኮ ወጣቶች እንዲሳተፉ አጋዥ ኃይል ሆነዋል።
ዛሬ «መከላከያን አትቀላቀሉ» የምትሉ ወንድሞችና እህቶች ግን ለመፀፀትና የዛሬ ስህተታችሁን ለማረም ጊዜ አይኖራችሁም። እናም በፈጠራችሁ አምላክ ልለምናችሁ…በሰማይም በምድርም በምትወዱት ይሁንባችሁ…ከስህተታችሁ ተመለሱ!
ግድየላችሁም ወንድሞቻችሁ በአገርና ሕዝብ የሚጨክን አንጀት የለንምና…ለብዙ ፖለቲካዊ እውነታዎችም በአንፃራዊነት የቀረብን ነንና…ደስ ባይላችሁ እንኳን ላሁኑ ከእኛ ጋር ቁሙ! ወጣቶቻችን ወደ መከላከያው እንዲገቡ በጋራ እንቀስቅስ።
ደግሞስ እናንተ ካላዳመጣችሁን ማን ሊያዳምጠን ነው? ለሕዝባችን ዘላቂ መብቶች፣ ጥቅሞችና ፍላጎቶች መከበር ስንታገል ማንን ደጀን ልናደርግ ነው? መከላከያስ እንደወልቃይትና ራያ ሁሉ የእኛነታችን መገለጫ የጋራ አገራዊ «ርስታችን» አይደለም ወይ?

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top