Connect with us

እንኳን ለትምህርት ቤት ውድመት ለራሳቸው ለአንድ ፍሬ ተማሪዎች የማይሳሳ አረመኔ ነው።

Social media

ነፃ ሃሳብ

እንኳን ለትምህርት ቤት ውድመት ለራሳቸው ለአንድ ፍሬ ተማሪዎች የማይሳሳ አረመኔ ነው።

እንኳን ለትምህርት ቤት ውድመት ለራሳቸው ለአንድ ፍሬ ተማሪዎች የማይሳሳ አረመኔ ነው። ይኽ የኢትዮጵያ የዛሬ ብቻ ሳይሆን የዘለዓለም ጠላቷ መሆኑን ማሳያ ነው!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)
በወራሪው የትህነግ ቡድን ተግባር ቀስ እያለ የሚገረመው ህዝብ ጨምሯል። ዓለምም እውነቱን ከማወቅ ወደ ማሳወቅ ተሸጋግሯል። ሮይተርስ ወራሪው ኃይል በአማራ ክልል የፈፀመውን ጅምላ ጭፍጨፋ ይፋ አድርጓል። ትግራይን አውድሞ የሚያጠፋው ሲያጣ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የገባው ሃይል ነውሩን ለመፈጸም አሳምኖም ይሁን አስገድዶ የትግራይ ወጣቶችን አሰልፏል።

የረገፈበትን መቁጠር ሲያቅተው የአፋርን ግንባር የለቀኩት በደንብ ተደራጅቼ ልመለስ ነው ሲል በየቀኑ እልቂት በሚያውጅበት ቃል አቀባዩ በኩል ይፋ አድርጓል።

ሊጥ በመስረቅ የነውሩን አድማስ ያሳየውና የአረመኔ ግብሩ መጠን ለደገፉት ሃይሎች እስኪያሸማቅቅ የተገለፀው ትህነግ አብይ አህመድና ብልፅግናን እንጂ ከህዝብ ጠብ የለኝም ብሎ በወረረው ከተማ አብሲት ሳይቀር ጭኖ ሄዷል። ዘራፊዎቹና ተቀባዮቹ ያን በልተው ትውልድ ማሻገር ከቻሉ አብረን እናየዋለን።

ከማሳ ላይ እህል ከአፈር አላቆ በመዝረፍ በዓለም የመጀመሪያው ትህነግ ነው። የጋይንትን ማሳ ያልበሰለ ድንች ከመሬት ቆፍሮ አግዞበታል። ሆስፒታል አውድሟል። ትምህርት ቤቶችንና ቤተ እምነቶችን አፍርሷል።

የአማራን ገዳማት ቆምኩለት እንዳለው ክልል ቤተ ክርስቲያናት ቅርሳቸውን ዘርፏል። መንግሥት ሆኖ ሲዘርፍ ላባከነው ጊዜ ነውሩን የሸፈኑ ትጉህ ሰዎች የዳስ ትምህርት ቤት ባለ ሁለት አህዝ እድገት አስመዝግቤያለሁ በምትል ሀገር ልክ አይደለም ብለው የገነቡትን ትምህርት ቤት አፍርሷል።

ሃይሌ ትምህርት ቤቱ በመውደሙ አምርሮ ማዘኑን አየሁ ሰው ስለሆነ አልፈርድበትም ምክንያቱም ሀገሩን የሚወድ ጀግና ነውና ግን እዚያ ውስጥ ተማሪ ቢያገኙም አይምሩም ነበር።
ንፁሃን ቤት ከባድ መሳሪያ ከሚተኩስ የሕይወት ዘመን ሽፍታ ለትምህርት ቤት መራራትን መጠበቅ የዋህነት ነው። እንኳን ለትምህርት ቤት ለተማሪ ነፍስ ግድ የሌለው እናት አሰቃይቶና ደፍሮ የሄደ የአንድ መንደር የአፋር ሴትና ሕፃናትን የጨፈጨፈ አውሬ ነው።

በየቀኑ ከሰማናቸው የስቆቃ ዜናዎች ተነስተን ጉድ ብንል አይገርምም የበለጠ ጉድ የምንሰማው ወደ ፊት ነው። በኢትዮጵያ ያወጁት ጥፋት መጠኑ ምን ያህል እንደነበር የሚገባን ከአጋዙት ሊጥና ከዘረፋት ዱቄት በላይ ያወደሙት ሀገር የጨረሱት ወገንና የፈፀሙት ነውር ሲሰማ ነው።
ይሄን በዓለም የቱም ሽብርተኛ አድርጎት የማያውቅ የጦር ወንጀል ተቀናጅተን አለም እንዲያውቀው እናደርጋለን። አሁን እየተደረጉ ያሉ አለም አቀፍ የማጋለጥ ዘመቻዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።

ያኔ እውነት ስትወጣ ከጎናቸው የቆመ ለዘለዓለም አንገቱን ይደፋል። ያለ ማንም ጫና ከዚህ ወንጀል ጎን መቆም ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ሀፍረት ሆኖ ይቀራል። እነሱ በሰሩት ድራማ በሀውዜን ላስጨረሱት የትግራይ ህዝብ በቀል ማኖሪያ ከሚያከብሩት የሰማዕታት ቀን በላይ ትህነግ በኢትዮጵያ ያደረሰው መከራ የልጅ ልጅ የሚማረው አፍሪካ ጭምር በእኔ ይብቃ የምትልበት ክስተት ሆኖ ይኖራል። ኢትዮጵያ ታሸንፋለች። ዛሬ የጀግኖች ቀን ነው። የጀግኖች ሀገር በጀግኖች ታሸንፋለች።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top