Connect with us

አሳሳቢው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነገር

Social media

ነፃ ሃሳብ

አሳሳቢው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነገር

አሳሳቢው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነገር
(ሙክታሮቪች)

ጁንታው እንደጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ እያለቀሰ ይገኛል። ሁለት ትልልቅ ሚዲያዎች (Telegraph&CNN) በዚህ ሁለት ቀን ሁመራ ላይ ጭፍጨፋ ተፈፀመ፣ ተከዜ ወንዝ ውስጥ ሬሳ ተጣለ በማለት ፍፁም ሀሰት የሆነ ዘገባ ሲሰሩ በዋሺንግተንና በለንደን ያሉ ኢምባሲዎች ማስተባበያ እንዲፅፉ የውጪ ጉዳይ መመሪያ መስጠት ሲኖርበት አልሰጠም። የአሜሪካ እና የእንግሊዝ አማባሳደሮችም ማስተባበያ አልሰጡም።

የሀሰት ዘገባው በርቀት የተጠናቀረ እንደሆነ ጋዜጦቹም አልካዱም። የተፈለገው ጭፍጨፋ አለ ብሎ ማስጮህን ነው። የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአማራና አፋር ህዝብ ላይ የደረሰውን መዓት በመጥቀስ የእነዚህ ሚዲያዎችን አድሎኣዊ አሰራር መተቸት ይችል ነበረ። በዚህም በዲፕሎማሲው ሀገር ዋጋ እየከፈለች ነው።

ባለፉት ወራቶች ለደረሰብን የዲፕሎማሲ ውድቀት የውጪ ጉዳይ የራሱ ድርሻ እንዳለው አይካድም። እየተሻሻለ የመጣ ቢመስልም አሁንም የተፋዘዘ መስሪያ ቤት መሆኑ ያበሳጫል።

ጁንታው የእምነት ተቋማትን አፍርሷል

በሰሜን ወሎ መድረሳ ገብቶ የቁርአን ተማሪዎችን አርዷል። ( ይህን ለአረብ ሀገራት ብናሳውቅ የዲፕሎማሲ ጥቅም ነበረው)

ጁንታው ገበሬ እያረደ፣ ከብት እየጨፈጨፈ ነው።

ነጋሊኮማ
በአጋምሳ
ጭፍጨፋ ፈፅሟል።

ግን ይህ በደሉን ማጮህ አልተቻለም።

ጁንታው በአማራ ክልል የተገደሉበትን ወታደሮች በሲኖ ጭኖ በጅምላ እየቀበረ ነው። ለውጪ ሚዲያ ሊያሳየው ነው። እንዲህ እንዲህ እየቀደሙን ያሉት የውጪ ጉዳይ እያንቀላፋ ስለሆነ ነው።

ወታደሩ አፈር በልቶ የሚያመጣው ድልን የማይስጠብቅና በዲፕሎማሲ የሚያስበልጠን ከሆነ፣ ይህንን መስሪያቤት ለሀገር ጥቅም ስንል አጥብቀን እንታገለዋለን። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆምጨጭ ያለ ትዕዛዝ ለዚህ መስሪያቤት ሊሰጠው ግድ ይላል።

ወታደር ነፍሱን እየሰጠ የውጪ ጉዳይ ጊዜውን ለሀገር የማይሰጥበት ምክንያት ስለምንድነው?

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top