Connect with us

እዩልኝ ይህቺን የሴት ጣይቱ ንግሥት ይርጋን ግንባር ወርዳ የእናቶቿን ታሪክ ስትደግም፤

ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

እዩልኝ ይህቺን የሴት ጣይቱ ንግሥት ይርጋን ግንባር ወርዳ የእናቶቿን ታሪክ ስትደግም፤

እዩልኝ ይህቺን የሴት ጣይቱ ንግሥት ይርጋን ግንባር ወርዳ የእናቶቿን ታሪክ ስትደግም፤
“ግንባር ያለውን ሠራዊት ቢያንስ በቀን አንዴ እንጀራ እንዲበላ ብላለች!”

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
እንዲህ ነበሩ ጀግና እናቶች፤ እንዲህ ነበሩ የቀደሙቱ፤ አልቅሰው አይሸኙም አብረው ይጓዛሉ፡፡ ሀገር የሚደፍር ሲባል የማይደፍሩት የለም፡፡ ንግሥት ይርጋ ለሀገሬ ሰው እንግዳ አይደለችም፡፡ ዛሬ ሲዖል ወርደን ሀገር እናፈርሳለን ያሉቱ ባንኩን፣ ቤተ መንግሥቱን፣ ውጪ ጉዳዩን፣ አጋዚውንና ደህንነቱን ይዘው ሳለ “ወይድ” ብላ አደባባይ የቆመች፤ የጎንደር የዚህ ትውልድ የትግል ተምሳሌት ነች፡፡ በዝምታችን ያልጣልናቸውን የሀገር ጠላቶች በወኔዋ ጎንደር ጎዳናዎች ላይ አንገት ያስደፋች፡፡

ንግሥት ዛሬም እዚያው ናት፤ የትናንትናዋ የሀገር መውደድ ስፍራዋ ላይ፤ ደባርቅ ግንባር እየደከመች ነው፡፡ እንደ እቴጌ እሌኒ፣ እንደ ሰብለ ወንጌል እንደ እቴጌ ጣይቱ፤ ንግሥት ይርጋ የኔ ዘመን እቴጌ፤

እንዲህ አለች “በደባርቅ ግንባር ላለው ሰራዊት ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ እንጀራ እንዲመገቡ” ይሄ በሀሳብ አልቀረም፡፡ ደባርቅ ከተማ ለዘመቻው የሚውል ሀሳቧ የሚሳካበት ሚንስ ቤት በማዘጋጀት እንጀራው ተጋግሮ ወጡ ተሰርቶ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ለሚሊሻ እንዲሁም ለፋኖ እየቀረበ ይገኛል፡፡

የደባርቅ ወጣቶች ከጎኔ ቆመው የተቻለንን ያህል እያደረግን እንገኛለን የምትለው ንግሥት ይሄን ድንቅ የእናት ደጀንነት የእህት አለኝታነት ተግባር በመደገፍ በኩል የደባርቅ ከተማ አስተዳደር በተለይም እንደ ከንቲባ ከተማ እየመሩ፣ እንደ ወታደር ነፍጥ ይዘው እየታገሉ እንደ ደጀን ግብአት እያቀረቡ ያለ እረፍት በመስራት ላይ የሚገኙት ከንቲባ አቶ ሰለሞን ተዘራን በፌስቡክ ገጿ አመስግናለች፡፡ “ምግቡን የምናዘጋጅበትን ቦታ ከመስጠት ጀምሮ የደባርቅ ከተማ ወጣቶችን በማስተባበር ላደረጉልን እገዛ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን! ይህ ስራ እንዲሳካ እና ሰራዊታችን ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ እንጀራ በልቶ እንዲዋጋ በማድረግ” ስትል በምስጋና ገልጻለች፡፡

ንግሥት በፌስቡክ ገጿ ላይ ባቀረበችው ምስጋናም ለዚህ ዓላማ ስኬት በአቶ ሰረበ ሙሉ አማካኝነት በሀገረ እንግሊዝ ማንችስተር ከተማ የሚኖሩ የአማራ ወጣቶች፣ በቃን የአማራ የአደጋ ጊዜ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ማህበር ከሀገረ አሜሪካን፣ በመሳፍንት ካሰኝ እና በካሳው ዘውዴ አስተባባሪነት በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ የጎንደር ከተማ ወጣቶች፣ አቶ ሀብታሙ አዱኛ የአማራ ዲያስፖራዎች ማህበር ፕሬዚዳንት፣ አቶ አስረስ ይርጋ ከካናዳ ቶሮንቶ፣ ወጣት ቢኒያም ታደሰ ከባህር ዳር፣ የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና እና ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለምን ጨምሮ ለዓላማው መሳካት ድጋፍ ያደረጉ ሀገር ወዳዶችን ከነድርሻቸው አመስግናለች፡፡

ይህ የሀገር ፍቅር ዛሬም ሰው በሚያስፈልግበት ቀን ከነ ሙሉ ክብሩ ተገልጾ ስላየሁት ደስ ብሎኛል፡፡ እሷም እንዲህ ያለው ተግባር “ይህ ጦርነት እስኪያልቅ ድረስ ጦርነቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቅርበት እየተገኝን እና ጊዚያዊ ሚንስ ቤት እያቋቋምን ሰራዊታችንን እንመግባለች!” ብላለች፡፡
ሀገር የምትኖረው በሚወዷት ልጆቿ ቁርጠኝነት ነው፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top