Connect with us

ከጋሳይ እስከ ደብረ ዘቢጥ

ከጋሳይ እስከ ደብረ ዘቢጥ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ከጋሳይ እስከ ደብረ ዘቢጥ

ከጋሳይ እስከ ደብረ ዘቢጥ

ከማዕከላዊ መንግሥቱ ያፈነገጠዉ እና መቀሌ የመሸገዉ የአሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ኀይል የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ አጣ:: ‘ሀገሪቱን እኛ ካልመራናት ብትንትኗ ይውጣ’ ብሎ የጅል ምክር መከረ:: ሀገሪቱ ትበታተን ያለበት ምክንያት አንድም አባላቱ ለስልጣን ካላቸዉ የስግብግብነት ባህሪ ሲሆን ሁለትም ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል የሠሩት ዓይን ያወጣ ወንጀል ሲከተላቸዉና እንቅልፍ ሲነሳቸዉ ስለሚኖር ነው::

እናም ለዘመናት የፈፀሙት ወንጀል በየሰከንዱ እያባተታቸዉ ጭንቀት ውስጥ ገቡ:: ጭንቀታቸዉ ሲደጋገም ማቃዠት ጀመራቸው:: ንግግራቸውና ድርጊታቸው ሁሉ የእብድ እንጂ የጤነኛ ሰው አልመስል አለ:: በትግራይ ምርጫ እናካሂዳለን ብለው ተናገሩ:: ተናግረውም አልቀሩ ከማን ጋር እንደተፎካከሩ ሳይገባን ምርጫዉ ተካሄደ አሉ:: እንደልማዳቸዉ ክልላቸዉ ላይም መቶ በመቶ አሸነፍን አሉን:: ‘ድርጊታችሁ ሕገወጥ ነው! በማለት መንግሥት የ‘ጨረቃ ምርጫ’ ሲል ከንቱ ድካም መሆኑን በሚገባቸዉ ቋንቋ ነገራቸዉ::

የእብድነት ደረጃቸዉ እየጨመረ ሄደ:: ልብሳቸዉን ማውለቅ ብቻ ነበር የቀራቸዉ:: በክልላቸዉ ቴሌቪዥን ብቅ ብለው ‘ከመስከረም በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት አይኖርም’ አሉን:: ምን ዓይነት ጠንቋይ ቀልበዉ ነው መስከረም ላይ መንግሥት እንደማይኖር የነገሩን? ብለን እንደ ሞኝ ሳቅን:: እነዚህን ወንጀለኞች አስሮ ወደ ፀበል የሚወስዳቸዉ ጠፋ ማለት ነው? እያልን በእብደታቸዉ ደረጃ ማደግ ተገረምን::

መስከረምም ጊዜውን ጠብቆ መጣ:: እኛም ከ2012 ወደ 2013 ዓ.ም በሠላም ተሸጋገርን፤ መስከረም አልቆ ጥቅምት ላይም መንግሥት አለ፤ በሥልጣኑ እንደቀጠለ ነው:: አስረዉ የሚቀልቡት ጠንቋይ የትኛውን መስከረም ነው ያላቸዉ? ብለን ኑሯችንን ቀጠልን:: ሕግን የማያከብር አሸባሪ ቡድን ሕገ መንግሥቱን፣ ሕገ ሥርዓቱን ማብጠልጠሉን ማጣጣሉን ሥራዬ ብሎ ተያያዘዉ::

‘መስከረም ላይ መንግሥት አይኖርም’ ብለው የተነበዩት ዲያቢሎሳዊ እሳቤ ከንቱ መቅረቱና መሳቂያ መሆናቸዉ የበለጠ በእብደታቸዉ እንዲገፉበት ምክንያት ሆናቸዉ:: መስከረምም ግዳጁን ጨርሶ ለጥቅምት አስረከበ:: ይሄኔ ለጦርነት መዘጋጀታቸዉንና ማንኛውንም አካል መመከት እንደሚችሉ በጃጄ አንደበታቸዉ ሊነግሩን ሞከሩ::

ለዘመናት ከሀገሪቱና ከሕዝቡ የዘረፉትን ሀብት የጦር መሣሪያ ገዝተዉ ከዝነውበታል:: ከታንክ እስከ መድፍ፣ ከሞርታር እስከ ቢኤም፣ ከሮኬት እስከ ሚሳኤል ታቅፈዋል:: የትግራይን የደሃ ልጆች በመመልመል ወታደራዊ ስልጠና ሰጥተናል ብለዋል:: ይሄኔ በኀይል ሥርዓቱን እንደሚያፈርሱት እርግጠኛ ሆነዋል::

አንድ ነገር እያሰጋቸዉ ነበር:: የመከላከያ ሠራዊቱ ጠንቅ ሊሆነን ይችላል ብለዉ ሐሳብ ሰነዘሩ:: ከላያቸዉ ላይ ለዘመናት የሰፈረዉ እርኩስ መንፈስ ሹክ አላቸዉ ሠራዊቱን አዘናግቶ መጨፍጨፍና የታጠቀውን የጦር መሣሪያ መዝረፍ’ የሚል::

ከላያቸዉ ላይ ያለዉ የሁለም እርኩስ መንፈስ ይህን ዕኩይ ተግባር እንዲስማሙ ሹክ አላቸዉ በሙሉ ድምጽ አፀደቁት:: ጥቅምት አንድ ሁለት እያለ ሃያ አራተኛዉ ቀን ላይ ደርሷል:: ለሀገር ዘብ የቆመን፣ ለሀገር መከታና ጋሻ የሆነን፣ ለሀገር ሲል ራሱን ለሞት ያዘጋጀ ሠራዊት ላይ የሞት ድግስ አወጁ:: በተጠናና በታቀደ መልኩ የጥፋት እጃቸዉን ዘረጉ:: ጥቅምት 24 ምሽት አራት ሰዓት ላይ ሀገር ሠላም ብሎ ሠራዊቱ ተኝቷል:: በተኛበት ጭፍጨፋውን ተያያዙት:: የታጠቀውን ከቀላል እስከ ከባድ መሣሪያ ዘረፉ::

ቀድመው ካዘጋጁት የጦር መሣሪያ በተጨማሪ ሠራዊቱን  ጨፍጭፈዉ ያገኙትን መሣሪያ መለቃቀም ያዙ:: ትዕቢታቸዉም እብደታቸዉም ቅጥ አጣ:: አጉል እብሪት ወጣጠራቸዉ መስከረም 30 ብለው የቃዡት ከንቱ ትንቢት ትዝ አላቸዉ:: መንግሥት አይኖርም ያሉትን ቃል ለመፈፀም በደመ ነፍስ መንግሥትን ሊጥሉ፣ ሥርዓቱን ሊያፈርሱ ጥድፊያ ውስጥ ገቡ::

‘አጁሃ፣ አጁሃ…’ እየተባባሉ ሀሳባቸውን ሊያሳኩ ጉዞ ጀመሩ:: በአማራና በአፋር ክልል አቆራርጠዉ ወደ መሀል አገር በአጭር ቀን ለመግባት መከሩ:: አራት ኪሎ ለመድረስ ጓጉ:: ‘አጁሃ…’ እያሉ በአማራና በአፋር ክልል ወረራቸዉን ሲጀምሩ መንግሥት ‘ዘራፍ አካኪ ዘራፍ’ አለ፤ ፎክሮም አልቀረም በሕግ ማስከበር ዘመቻ ሕገ ወጦችን አደባቸዉን ሊያስገዛ ቆርጦ ተነሳ:: ከእኩይ ድርጊታቸዉ ያመለጠውና የተረፈዉ የመከላከያ ሠራዊት እልህ ውስጥ ገብቶ ትጥቁን አነሳ:: የአማራና የአፋር ልዩ ኀይል ሽብርተኛዉን ለመምታት ወፍ አልቀደማቸዉም::

የየአካባቢው ሚሊሻና ፋኖ ነፍጡን አንስቶ ‘አካኪ ዘራፍ እያለ’ ግንባር ደረሰ:: ግንባር ደርሶም የጠላቱን ግንባር እያፈረሰ፣ የጠላቱን ምሽግ እየደረማመሰ፣ የወራሪውን ቡድን አባላት አስክሬን እየከመረ፣ በጥይት አረር እያረገፈ… ወደ ፊት ገሰገሰ:: መስከረም 30 ባይሳካም ጥቅምት 30 ቤተመንግሥት ለመግባት የቋመጠው ዘራፊው ቡድን ጥቅምት 30 ከአብደራፊ ከማይካድራ፣ ከራውያን ከሁመራ ተጠራርጐ፣ ተደምስሶ የቀረዉ በአዲጐሹ አቋርጦ ሽራሮ ገባ::

በሁሉም አቅጣጫ ሽንፈትን የተከናነበዉ ይህ ቡድን መከላከያው ትግራይ ድረስ ዘልቆ በመግባት እያሳደደዉ መሆኑን ሲረዳ ፍርጠጣውን ወደ ተንቤን አደረገ:: ሲመኩባቸዉ የነበሩና የላቀ የውጊያ ልምድ አላቸዉ ብለው ሲተማመኑባቸዉ የነበሩ የጃጁ፣ የጨረጨሱ አዋጊዎች ቀሚስ ለብሰው ተገኙ:: እጃቸው በካቴና ተቆልፎ ዓለም እየሳቀባቸዉ እነሱ ግን እያለቀሱ ወደ ዘብጥያ ወረዱ::

የቀሩት ጀግና ነን ባየ የወራሪዉ ቡድን ቀንደኛ መሪዎች ግንባራቸውን እየተፈረከሱ ከተደበቁበት ዋሻ ውስጥ እየተደራረቡ ተዘረሩ:: ምላሳቸዉ ብቻ የቀረ ጥቂት የቡድኑ አመራሮች በተንቤን ሸለቆ፣ ዋሻ፣ ጥሻና ጉድጓድ ውስጥ እንደ ቅንቡርስ እየተሳበ በጭንቀት ተጎሳቁለው መኖር ጀመሩ::

ወራዳ ተግባር የፈፀሙት እኒህ የእፉኝት ልጆች ተዋርደው መሳቂያ መሳለቂያ ሆኑ:: ‘ኢትዮጵያን እንበታትናታለን ባሉበት አንደበታቸው ራሳቸው ተበታተኑ:: መንግሥትም በአሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ሀይል ለችግር ለተዳረገው የትግራይ ሕዝብ እና ለራሱ ለሽብርተኛው ቡድን የማሰቢያ ጊዜ ሰጣቸዉ:: የትግራይ አርሶ አደር ያለዉን መሬትም ቢሆን ጭሮ እንዲያድር… በሚል የጽሞና ጊዜ ፈቀደላቸዉ:: ሠራዊቱም ከትግራይ ክልል እንዲወጣ ሆነ፤ ሰኔ 2013 ዓ/ም:: 

መከላከያዉ ከትግራይ ክልል ሲወጣ፣ ሽብርተኛውና የተዋረደዉ የትሕነግ ወራሪ ኀይል ከተንቤን ዋሻ ወጣ:: መቀሌ ውስጥ በጽሞና ሊያስቡ ነው ብለን ገመትን:: ግምታችን ግን ስህተት ነበር:: ከእኩይ ተግባራቸው ጋር የቆረቡት የአሸባሪው ትሕነግ ወራሪዉ ኀይል አመራሮች እና አባላት አሁንም ‘ኢትዮጵያ ካልተበታተነች አንተኛም’ አሉ:: ዘላለማዊ ጠላታችን ነው ብለው በፍኖተ መርሃቸው የፈረጁት የአማራ ሕዝብ ላይ ልዩ ጥላቻ እንዳላቸዉ በአንደበታቸዉ ነገሩን:: “ከአማራ ሕዝብ ጋር የምናወራርደዉ ሒሳብ አለን” አሉ::

የትላንቱን ውርደታቸዉን ረስተውታል:: በእርግጥ  እብድ ያለፈውንም ሆነ የሚመጣውን ሊያስብና ሊያገናዝብ አይችልም:: የአሸባሪው ትሕነግ ወራሪ ኀይል ስለሚደርስበት ኪሳራ እና ውርደት ማሰብ ተስኖታል:: ብቻ በደመ ነፍስ ወደ መሀል አገር መግባትን እና አራት ኪሎን መርገጥ እንዳለበት በቅዠት መልኩ እየታየው ነው:: ለእነርሱ ክብርና ስልጣን ሲባል የትግራይ የደሀ ልጆችን መስዋዕት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:: 

ከገጠር እስከ ከተማ ከሕፃን እስከ ሴት በየቤቱ እየዞሩ አስገድደው መመልመል ጀመሩ::

ክላሽ መተኮስ ይቅርና ክላሽ መሸከም የማይችሉ ሴቶችንና ሕፃናትን አሰልፎ ከመቀሌ ወደ ደቡቡ ትግራይ ጉዞውን ጀመረ:: አሸባሪው እና ወራሪዉ ሀይል ለምልምል አባሎች የሦስት እና የአራት ቀን ወታደራዊ ስልጠና መሰል እንዲወስዱ አደረገ:: አንድ ክላሽ ለአምስትና ለስድስት በማስታጠቅ ወረራውን በኮረም በኩል አንድ ብሎ ጀመረ::

ከክላሽ እስከ ታንክ፣ ከመድፍ እስከ ሞርታር ከቢኤም እስከ ሚሳየልና ሮኬት ታጥቆ ማሸነፍ ያልቻለውን፤ ውርደትን ተከናንቦ የተደመሰሰና የፈረጠጠ ኀይል ወደ ግጭትና ወረራ መልሶ መግባቱ የለየለት እብደት ውስጥ መሆኑን አረጋገጠልን:: ከኮረም በኋላ አላማጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ ድረስ እንደ ቅጠል እየረገፉ ደረሱ:: በአማራ ክልል በተለያዩ አቅጣጫዎች የወረራ አድማሳቸውን ማስፋት ጀመሩ:: በአፋር ክልልም ንፁሀንን እየገደሉ ወረራውን ተያያዙት::

ወልድያ ላይ ለቀናት ያህል የቆየዉ ወራሪው ኀይል በየከተሞች ከዱቄት እስከ ከብት፣ ከካልስ እስከ ቀሚስ… እየዘረፈ ንፁሃንን እየገደለ የዘረፈዉን ሀብትና ንብረት ወደ ትግራይ ማጓጓዝ ጀመረ:: የሰረቀዉ ዱቄትና ሊጥ፣ ሽሮና በርበሬ ጣፈጠዉ መሰል ዝርፊያውንና ወረራዉን ማስቀጠል እንዳለበት አመነ::

ከወልድያ፣ ጋሸና፣ ገረገራ፣ መቄት፣ ጋይንት፣ ክምር ድንጋይ፣ ጋሳይ እየወረረ፣ እየሰረቀ፣ እያወደመ፣ እየደፈረ፣ እየገደለ… መጣ:: ጋሳይ መድረሱ ደግሞ የልብ ልብ ሰጥቶታል:: ደብረታቦር፣ ወረታ ጐንደር፣ ባሕር ዳር … እያለ ወደ መሀል አገር ለመገስገስ ቋመጠ::

የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት በሕግ ማስከበሩ የፈፀሙትን አኩሪ ታሪካዊ ጀግንነት መድገም እንዳለባቸዉ ወሰኑ:: ትላንት የተዋረደዉ ወራሪዉ ኀይል ዳግም ውርደት ውስጥ መግባት እንዳለበት መከሩ:: ከጋሳይ በኋላ አንድ ስንዝር መሬት ወደ ፊት መሄድ የለበትም ተብሎ ተወሰነ:: የደብረታቦር ወጣቶች አፍንጫቸዉ ሥር የደረሰዉን ወራሪ ኀይል ለመደምሰስ ከፀጥታ አባላት ጋር በቅንጅት መሥራት ጀመሩ::

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖና የየአካባቢዉ ማኅበረሰብ ጠላትን ለመደምሰስ ዝግጅታቸዉን እያጠናቀቁ ነው:: የሠራዊቱ አባላት ቦታ ቦታቸዉን ይዘዋል:: ክላሻቸዉን፣ መትረየሳቸዉን፣ ዲሽቃቸዉን፣ ስናይፐራቸዉን ወልውለው፣ አቀባብለው፣ ቃታቸዉን ከፍተዉ ትዕዛዝ እየጠበቁ ናቸው:: የመከላከያ ሠራዊት የሜካናይዝድ ጦር መድፉን፣ ቢኤሙን፣ ሞርታሩን፣ ተወንጫፊ ‘107’ ሮኬቱን ጠምዶ በጋሳይ ግንባር ቅንቡላዉን በጠላት ላይ ሊያዘንቡ ተዘጋጁ::

አሁን የቀረዉ ‘በለው…’ የሚል የጦር መኮንኖች ትዕዛዝ ብቻ ነው:: ነሐሴ 14 ቀን ቀጥቅጠው የሚል የጄኔራሎች ፊሽካ ተነፋ:: በጋሳይ ሰማይ ላይ ሞርታሮች፣ መድፎች፣ ቢኤሞች፣… እያገሱ፣ እየጮሁ እሳት ማዝነብ ጀመሩ:: ኢላማቸዉንም በተሳካ ሁኔታ እየመቱ ነው:: የጠላት ጦር መግቢያ መድረሻዉ ጠፋው::

እግረኛዉ ጦር የሜካናይዝዱን ድብደባ ሽፋን ተከትሎ ዲሽቃዉን፣ መትረየሱን፣ ስናይፐሩን እያንጣጣ፤ የጥይት አረሩን በወራሪዉ ኀይል ላይ ያዘንብበት ጀመር:: የጋሳይ ቀበሌ፣ የሳህርና ቀበሌ ሜዳውና ጫካው በጠላት አስከሬን ተሸፈነ:: ወደ ደብረታቦርና ባሕር ዳር ለመግባት የቋመጠዉ አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኀይል ወደ መጣበት ዙሮ የተረፈዉ ኀይሉ ይዞ ፈረጠጠ:: ግማሹን የየአካባቢው አርሶ አደሮች እና ነዋሪዎች በአብራራዉና በበዲሞትፈር እየቀሉ በየመንገዱ ጣሉት፤ መከላከያዉ፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ጠላትን እያሳደዱ ክምር ድንጋይ ገቡ::

የግለሰብንና የመንግሥትን ተቋማት ዘርፎና አውድሞ ርዝራዡ ቡድን ፍርጠጣዉን እየገፋበት ነው:: ጠላት ጊዜ ሳያገኝ መደምሰስ አለበት ብለው የፀጥታ አካላቱ ጉዟቸዉን ወደ ፊት እያደረጉ ነው:: አሸባሪዉ የትሕነግ ወራሪ ኀይል ደግሞ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ኋላ ለሀጩን እያዝረከረከ እየሮጠ ነው:: የራሱን ቁስለኞች ምስጢር ያወጡብኛል በማለት በተኙበት እየረሸናቸዉ፣ እየጨረሳቸዉ ነው የሄደው::

ከጋሳይ የፈረጠጠው ወራሪው ቡድን ክምር ድንጋይን፣ ሳሊን፣ ጐብጐብን ወደ ኋላው እየተወ ነፋስ መውጫ ወርዶ ከደቡብ ጐንደር ተጠራርጐ ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ደብረ ዘቢጥ ተራራማ ቦታ ላይ ከሞት የተረፉትን ሕፃናት፣ ሽማግሌዎች እና ሴቶችን ለቃቅሞ ቦታ ይዞ ተቀመጠ::

መግቢያ መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶበታል:: በሌላ አቅጣጫ የመከላከያ ሠራዊት መንገድ ዘግቶ እየጠበቀዉ ነው:: ከኋላው ሲያሳድደውና እንደከብት ሲነዳው የዋለው የመከላከያ ሠራዊት እና ልዩ ኀይል  መጥቶበታል:: በሁለት አቅጣጫ የተከበበዉ ወራሪዉ ኀይል እየተቁለጨለጨ ደብረዘቢጥ ላይ አደፈጠ::

ወራሪዉ የትግራይ ኀይል ወረራ ባካሄደበት ጊዜ ከደብረ ዘቢጥ ጋሳይ ለመድረስ አስራ አንድ ቀን ወስዶበት ነበር:: የጥቃት እርምጃ ሲወሰድበት እና ሲቀጠቀጥ ተመልሶ ደብረ ዘቢጥ ለመግባት ግን አንድ ቀን አልወሰደበትም:: ዘጠና ኪሎ ሜትር ያህል በአንድ ጀንበር ፈርጥጦ ደብረ ዘቢጥ እንዲገባ ተገደደ:: ትላንት በሕግ ማስከበሩ የተከናነበውን ውርደት ዛሬም ዳግም ተከናንቦ ከሞት የተረፉትን አባላቱን ታቅፎ ጉድጓድ ውስጥ እንደቀበሮ እንዲኖር ተፈርዶበታል:: 

አሁን አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኀይል ከባሕር የወጣ ዓሣ ሆኗል:: ትርጉም የሌለው ህይወት ውስጥ ተዘፍቋል:: ከሕዝቡ የዘረፈዉን ዱቄትና በርበሬ እየበጠበጠም ቢሆን ለጊዜዉ ሊበላ ይችላል:: የሚተኩሰዉ ጥይት ግን ከየትም አቅጣጫ አያገኝም:: ምክንያቱም በሁሉም መሿለኪያዉ ተዘግቶ ወጥመድ ውስጥ የገባች አይጥ ሆኗል::

ዳግም ውርደትን ተከናንቦ ነፍስ ውጪ፣ ነፍስ ግቢ አጣብቂኝ ውስጥ ወድቋል:: መከላከያ ሠራዊቱ አሁንም ይህን አገር አፍራሽ ቡድን እስከ መጨረሻዉ ለመደምሰስ ቦታ ቦታቸዉን ይዘዉ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ:: መድፎች ማርታሮች፣ ቢኤሞች፣ ታንኮችና ተወንጫፊ ሮኬቶች ቁንቡላቸዉን ወልውለው ጠላትን አፈር ድሜ ሊያስግጡ የተጠና ቀጠናቸዉን ይዘዋል::

ጠላትን በከባድ መሣሪያ መበታተን፣ ምሽጉን መደርመስ፣ አለኝ የሚለዉን ትጥቅ እና ስንቅ ባከማቸበት መምታት ተቀዳሚዉ ሥራቸዉ ነው:: የተጠኑ  ኢላማዎች ላይ ድብደባ እንዲካሄድ ተወስኗል:: ነሐሴ 21 ቀን መድፎችና ቢኤሞች እሳት እየተፉ የጠላትን ወሳኝ ቦታዎች ዶግ አመድ አደረጉት:: ድብደባዉ እንደቀጠለ ነው:: ጠላት ውርደቱን ተከናንቦ ሥራው ሁሉ አባሉን መቅበር ሆኗል:: ያለዉ አማራጭ ሁለት ብቻ ነው:: ከመሸገበት ከደብረዘቢጥ ተራራ ወጥቶ እጅ መስጠት ወይም ከመሸገበት ጉድጓድ ውስጥ መቀበር::

ቅንቡላዉ እየጮኸ ነው:: መድፍና ታንኩ እያጓራ ነው:: የደብረዘቢጥ ሰማይ ጀግኖቹ የላኩለከትን እሳት ተቀብሎ ወደ ምድር እያዘነበ ነው:: ጠላት ደግሞ ውጥረት እና ውርደት ውስጥ ወድቋል:: የመከላከያ ሰራዊት፣ የልዩ ኀይል፣ ፋኖ እና ሚሊሺያ ጥምር የእግረኛ ጦር እያሟሟቀ ነው:: ዲሽቃውን፣ ሞርተሩን፣ መትረየሱን፣ ስናይፐሩን እና ክላሹን ጥይት አጉርሶ፣ እሳት ለብሶ እሳት ጐርሶ ፊሽካውን እየተጠባበቀ ነው:: 

…. ፊሽካው በጦር መኮንኖች በኩል ተነፋ። “የጠላትን ምሽግ በከባድ መሣሪያ እረሠው፣ አፍርሰው” የሚል ነበር።

ነሐሴ 21 ቀን የጀመረዉ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ለአምስት ቀን ያህል የደብረዘቢጥን ተራራ ይንደዉ ጀመር። ይህን ተስፋ የቆረጠዉን ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ አምስት ቀን የሚወስድ አልነበረም:: ነገር ግን አካባቢዉ በደመና እና በጉም እየተሸፈነ ተፈጥሮ መከራቸዉን እንዲጨምር አደረገባቸዉ። ነሐሴ 25 የደብረ ዘቢጥ ተራራ ፍንትው ብሎ ለውጊያ የተመቻቸ ሆነ። 

የከባድ መሣሪያ የዘመነ የውጊያ ልምድ ያላቸዉ ጦረኞች ቁንቡላቸዉን እያስወነጨፉ የጠላት ምሽግ ላይ በተሳካ ሁኔታ ይቀረቅሩት ጀመር። የደብረ ዘቢጥ ተራራ በደም ጨቀየ። ጋራዉ ሸንተረሩ በሬሳ ቁልል ተሸፈነ። የወገን እግረኛ ጦር እየፎከራ ተራራዉን ተጠጋ። የደነገጠዉ የጠላት ጦር መፈርጠጥ ጀመረ። እግረኛዉ በክላሽ፣ በዲሽቃ፣ በመትረየስ… እየተከተለ በጥይት ይለቅመዉ ጀመር። ጦርነት ባህላችን ነው ሲል የከረመዉ ወራሪ ቡድን ፍርጠጣ፣ ሩጫ ባህላቸዉ ሆኖ አገኘነው። 

ደብረ ዘቢጥ ከአምስት ቀን የጥይት አረር፣ ጩኸት… በኋላ ጸጥታ ነግሶባታል። ነሐሴ 26 ቀን ተጠራርጎ የተረፈዉ ርዝራዥ ወደ ፍላቂት እግሬ አውጭኝ ብሎ የአማራን ክልል የወረረበትን ቀን እየረገመ ለሃጩን እያዝረከረከ እየሮጠ ነው። እኛም መከተላችንን ቀጥለናል።

(ሱራፌል ስንታየሁ)

በኲር ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ዕትም

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top