Connect with us

አገር ሲዘርፍ የነበረው ጥገኛ፣ ዱቄት ሲልስ ሊያከትምለት ይገባል !!

Social media

ነፃ ሃሳብ

አገር ሲዘርፍ የነበረው ጥገኛ፣ ዱቄት ሲልስ ሊያከትምለት ይገባል !!

አገር ሲዘርፍ የነበረው ጥገኛ፣ ዱቄት ሲልስ ሊያከትምለት ይገባል !!
( ገለታ ገ/ወልድ- ድሬቲዩብ )

ህወሀትና የአላማው ተጋሪ የሆኑ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ባለፉት 30 አመታትም ሆነ ዛሬም ቢሆን በዘረፋና ቅሚያ ስነልቦና የተካኑ ናቸው ፡፡

ይቅርታ ይደረግልኝና የእኛ ህዝብ ይቅርባይ ስለሆነ እንጂ፣ወያኔ ይህን ህዝብና አገር አጭበርብሮም በግላጭም የጋጠውን ያህል ማንም አልበዘበዘውም ፡፡ ለዚህም የትሪሊዮን ብሩን ከአገር መውጣት ብቻ ማንሳት በቂ ነው፡፡

ለዚህ ፅሁፍ መንደርደሪያ ግን ሜቴክ ሲባል በነበረው የቀድሞ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የነበረውን ገበና መንደርደሪያ ማደረግ ወደድኩ ፡፡የዛሬዎቹ ጁንታዎችና የሽብር ቡድኑ ብዙዎቹ ተዋጊዎች መሪዎች ያኔ ፣ ደላላና አቀባባይ የሚሽቆጠቆጥላቸው ወታደራዊ አምባጋነነትን እየተላበሱ የመጡ ቡርዣዎች ነበሩ፡፡

እነዚያ ባለጌዎች በአገሪቱ ገጠር ከተማ ሳይባል ያሻቸውን ሀብት ሲያከማቹ ኖረው ፣ በንፋስ አመጣሽ የሀብት ማሸሸ መንገድ ህዝብን አቆርቁዘዋል ፡፡

ተደራጅተውም ሆነ በተናጠል የዘረፋው አካል የነበሩ ብዙዎቹ የኮርፖሬሽኑ የዘረፋ ቡድን አባላት ዛሬ የአሸባሪዉ ድርጅት ተዋጊዎች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ፣ንፁሃን የሚደፍሩ፣ዱቄትና ሊጥ የሚሰርቁ ግሪሳዎች ሆነዋል ፡፡ ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል እንደሚባለው!!

በመሰረቱ ህወሀት ከቀደመው ጊዜ አንስቶ የዘረጋው ስርአት ለዘረፋ እንዲመቸው ነበር ፡፡ “የወዳጅና ጠላት” ፣ “ የማህበራዊ መሰረቴና የስርዓታችን ፀር“ የፍረጃ ፖለቲካ አካሄዱ የራሱን በዝባዥች ለማበልፀግ ነበር ፡እሱ ብቻ ሳይሆን ስልጣኑ እንኳን ቢር በሃይልም ሆነ በሌላ መንገድ ሌላውን ህዝብ ለማራቆት እንደነበር የዛሬ ድርጊታቸው በግላጭ አሳይቷል ፡፡

አብዛኛዉ ዜጋ እንደሚያስታዉሰው ይህ (ሜቴክ) ሀገራዊ መስሪያ ቤት ህጋዊ ጨረታና ዉድድርን እየተከተለ አልነበረም ሲዘርፍ የኖረው ፡፡ በአብዛኛዉ በብሄር ማንነት ፤ በነባር ታጋይነት ወይም በማስመሰልም ሆነ እዉነተኛ የድርጅት ደጋፊነት ቁና እየሰፈረ ፣ አገር ሳትሆን ግለሰቦች ዘርፈው እንዲበለፅጉ ነበር ምኞቱ፡፡

የዛሬው የሊጥ ሌባ ስብስብ ያኔም ቢሆን እንደግሪሳ እየተቦደነ ፣ በማንአለብኝትና በአሻጥር የጥቅም አጋሮቹን እየመለመለ የሚያደረጅ ፣ገበያ የሚያመቻች ፣ ብድር የሚሰጥ ፣ህገወጥ ግዥ የሚፈፅም ፣ ለኮንትሮባንድ የሚያመቻቻ….አገር ያቆረቆዘ ጥገና ነበር፡፡

ዛሬ ደግሞ ያ ጥቅም ሲቀርበት አገር ለማፍረስ ተነስቶ፣ ሰማይ ምድሩን ለመቧጠጥ ይኳትናል ፡፡ ምንም ሊሳካላት ባይችልም !!

የዛሬው ጁንታና ያ ጥገኛ ቡድን አገር ያሳዘነውን መድሎ ሲፈፅም የነበረው ፣ ላይበላው የአገር ሀብትን ዘርፎ ለማሸሽ ብቻ ሳይሆን ፣አሁን እየፈፀመው እንዳለው አገርን በመካድ ያሻውን ወንጀል ለመፈፀምና ካልበላሁት ልድፋው ለማለት ነው፡፡

እንደፈለገ የሚያሽከረክረውና ለብዝበዛ የሚመቸው አሻንጉሊት ስርአት በማስቀመጥ አገርን ለማራኮትም ነበር ፡፡ ግን በፍፁም አይሳካለትም !!

ያኔ በሜቴክ የግፍ አሰራር በብዙዎቹ ኢንደስትሪዎችና ወርክሾፖች የሚቀጠሩና ክህሎት የተፈጠርላቸዉ፣አነስተኛና መካካለኝ የግብአት አምራቾችና አቅራቢዎች ዛሬ ተዋጊዎች ወይም የዲጂታል ወያኔዎች ሆነዋል ፡፡

ያልሆኑ ጥቂት ቀሩ ቢባሉም በኢኮኖሚ አሻጥርና በውስጥ ቦርቧሪነት እንደማይመለሱ ነው የደህንነት መረጃዎች የሚያመለክቱት ፡፡

በህዳሴ ግድብ ሳይቀር ደን ጠራጊዎች (እስከ 2 ቢሊዮን ብር የፈሰሰበት) ባለ ግዙፍ ሀብት ዓብይና ንኡስ ኮንትራክተሮች፣ የማሽነሪና የግልበጣ ተሽከርካሪ አከራዮች (በኦሞ ኩራዝ ከ60 በላይ ሲኖትራኮችን ያከራይ የነበረውን ኮሎኔል ተክላይ ጨምሮ) ብዙዎቹ እግር እየጎተቱና እየተንፏቀቁም ቢሆን ለአሸባሪው ሃይል እየተዋጉና እየወጉ ነው፡፡

ህወሀት በአገዛዝ ዘመኑ በዘረፋና ምዝበራ ሀገር መራቆቷ፣ የህዝቦች ችግርና ቁስቁልና መባባሱ አንሶት ፡፡ ዛሬ በአፋርና አማራ ክልሎች የመንግስት ንብረት ብቻ አይሉት የድሃ ከብት ፣እህልና የበሰለ እንጀራ ሳይቀር መዝረፉ ከመነሻው አፈጣጣሩን ገፅታ ያሳያል ፡፡

በሂሳብ እናወራርዳለን ድንፋታ ንፁሃንን መግደሉና መጥቃቱም እስከመቼውም የማይታዘንለት ጥላትነቱን ያረጋግጣል ፡፡

ምንም ተባለ ምን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ የሜቴክና የአገር ሌቦችም ሆነ በየመዋቅሩ ተስግስገው አገር ሲዘረፉ የነበሩትም ሆኑ ህዝብ የበደሉ ለፍርድ የሚቀርቡበት ቀን ሩቅ አይሆኑም ፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን በጁንታ መልክ ተደራጅተው አገር ለማፍረስና ስረአተ መንግስቱን ለመናድ ያሴሩ፣ጦርነት የመሩና የተዋጉ ሁሉ መቀጣጫ የሚሆኑበትን ቅጣት ሊያገኙ ግድ ነው ፡፡

ለዚህ ደግሞ በአንድ በኩል ይህ ሃይል በህጋዊው ምክር ቤት በሽብርተኝነት መፈረጁ ፣ ምልአተ ህዝቡ የቡድኑን ግፍና ውንብድና ተረድቶ ለመፋለም መሰለፉ፣አለምም ቢሆን በሂደት የቡድኑን ፅንፈኛ አካሄድ እየነቃበት መምጣቱ የድሉን ጊዜ ያቀርበዋል ፡፡

አገር የጋጠው ጥገኛ ፣ዱቄት የሚሰርቅ ሌባ እንደሆነ ሊያክትምለትም ግድ ነው!!

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top