Connect with us

አቅዱ እንጂ አትጨነቁ!

አቅዱ እንጂ አትጨነቁ!
Photo: Social media

ማህበራዊ

አቅዱ እንጂ አትጨነቁ!

አቅዱ እንጂ አትጨነቁ!

(ዶ/ር እዮብ ማሞ)

አንድ ስለነገ በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ዛሬን ማጣጣምና መኖር ያቃተውና የተጨናነቀ ሰው ወደ አንድ ጠቢብ ሰው ሄደና እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- “ስለነገየ በጣም ከመጨነቄ የተነሳ መማር፣ ስራ መስራት፣ ማፍቀርና የመሳሰሉትን ነገሮች ማድረግ አልቻልኩም፡፡ 

እንዲያውም ሌሎች ሰዎች እነዚህን አስጨናቂ የሕይወት ዘርፎች ዘና ብለው ሲሰማሩባቸው አይና, `ነገ ምን ይገጥማቸው ይሆን?’ በማለት ለእነሱም ሳይቀር እጨነቃለሁ፡፡ እባክዎትን ከነገ ጀምሮ በየእለቱ በሕይወቴ የሚከናወነውን ቀደም ብዬ እንዳውቀው አንድ በአንድ የሚነግረኝን ሰው ካለ አገናኙኝ”፡፡

የጠቢቡ መልስ፡- “በሕይወትህ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በየዓመቱ ወይም በየእድሜ ደረጃህ የሚገጥምህን በሙሉ አስቀድሞ የሚነግርህ ሰው የምታገኝ አይመስለኝም፣ ብታገኝም ይቅርብህ፡፡ ምክንያቱም የሚገጥምህን ነገር ሁሉ “ያወክ” ጊዜ ተስፋ ትቆርጣለህ፣ ለለውጥ መስራት ታቆማለህ፣ የየእለቱ አዳዲስ የሕይወት ምእራፍ የሚያቀብልህን አዳዲስ ተግዳሮት ለመጋፈጥ የሚኖርህን ሁለ-ግብ ዝግጅት ታቆማለህ፡፡ 

አየህ፣ ሕይወት የተፈጠረችው ሊመጣ ያለውን አስቀድሞ በማወቅ የሚሆነውን ቁጭ ብሎ ለመጠበቅ ሳይሆን ለመለወጥ የምትችለውን ለመለወጥ ለመስራት፣ መለወጥ የማትችለው ነገር ሲመጣ ደግሞ ፈጣሪህን ታምነህ በመቀበል ለመሻገር ነው”፡፡

አትጨነቁ! ተረጋጉ! አቅዱ! ስሩ! ችግር ሲመጣ አልፎ ለመሄድ የቆረጠ ልብ ይኑራችሁ! መልካም ገጠመኝ ሲከሰት ደግሞ ሁኔታውን በደስታ በመቀበል ለእድገት ተጠቀሙበት!

ሕይወት ማለት እኮ ካለፈው ታሪክ ልምድን ማዳበር፣ በዛሬው ሕይወት መደሰትና እንዲሁም ስለነገ በማቀድ ዝግጅት በማድረግ ቀና ብሎ መኖር ማለት ነው፡፡

 

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top