Connect with us

የውሸት ጸሐይ ጠልቃለች፤ የሤረኞችም ወጥመድ ሊበጠስ ተወጥሯል፡፡

የውሸት ጸሐይ ጠልቃለች፤ የሤረኞችም ወጥመድ ሊበጠስ ተወጥሯል፡፡ ዓለም በደገፈው አረመኔ ሀገር አፍራሽ ቡድን ነውር ያፍራል!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የውሸት ጸሐይ ጠልቃለች፤ የሤረኞችም ወጥመድ ሊበጠስ ተወጥሯል፡፡

የውሸት ጸሐይ ጠልቃለች፤ የሤረኞችም ወጥመድ ሊበጠስ ተወጥሯል፡፡ ዓለም በደገፈው አረመኔ ሀገር አፍራሽ ቡድን ነውር ያፍራል!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የልደታቸው ቀን መልዕክት የውሸት ጸሐይ ስትጠልቅ የሚል ቃል አለው፡፡ እውነት ለመናገር የትህነግ የውሸት ጸሐይ ጠልቃ በነውር ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ናት፡፡ ዓለም ገበናዋን ማየት ጀምሯል፡፡ ዱቄትና ቡኮ ከደሃ ገበሬ ጓዳ ለመዝረፍ ያሰፈሰፈ ሠራዊት በማሰማራት በህጻናት ነፍስ ቂምና ስልጣንን እውን ለማድረግ የሚባትሉ ጥቂት ሰዎች እየፈጸሙ ያሉትን አረመኔያዊ ድርጊት አይተናል፡፡

የቢቢሲው የሀርድ ቶክ አዘጋጅ ከጌታቸው ረዳ ጋር በነበረው ቆይታ በደሃ ልጅ ህይወት የሚጫወቱትን ቁማር ፍንትው አድርጎ ያሳየ አረመኔያዊ እቅዳቸውን አጋልጧል፡፡ ከዚህ በላይ የውሸት ጸሐይ መጥለቅ የለም፡፡ ሌላው ቢቀር ለቢቢሲ አስቀድመው በሰጡት መግለጫ በአፋር ንጹሃን ሞት መፈጠር የሌለበት ነው አዝናለሁ ብለው ያመኑት ሰው ለሀርድ ቶኩ አዘጋጅ ደግሞ ራሱ የአፋር የጸጥታ ሃይል የፈጠረው ግድያ እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል፡፡

የውሸትን ጸሐይ በአደባባይ ስትጠልቅ ብቻ ሳይሆን ሲያጠልቋትም እያየን ነው፡፡ ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው ብለው ሲያሸማቅቁ የኖሩት ትህነጎች ለኦነግ ያላቸው ጥላቻ ድፍን የኦሮሞ ህዝብን የመከራ ኑሮ እንዲገፋ ሲያደርገው አይተናል፡፡ ያ በቀን በብርሃን የተፈጸመ ጀብዳቸው ነው፡፡ ትናንት ሃይላንድ አንጠልጥለው ያሰቃዩዋቸው የፖለቲካ መሪዎችንና ሰው መሆናቸውን ጭምር ይኑቁዋቸው የነበሩ የኦነግ ሃይሎች ዛሬ አጋር ነን ሲሉና ፍቅራቸውን ሊያስረዱን ሲሞክሩ የውሸት ጸሐይ ጠልቃ የእውነት ጸሐይ በመውጣት አጋልጣቸዋለች፡፡

የቀረው ይልቅስ የሤረኞቹ ወጥመድ መበጠስ ነው እሱም ቢሆን አሁን በከፍተኛ ደረጃ ከሯል፡፡ ዳርና ዳር ተወጥሮ ሊበጠስ ነው፡፡ ያንን ኢትዮጵያ ከዳር ዳር እበጥሰዋለሁ ብላ ሆ ብላለች፡፡ በተጋድሎ ሲበጠስ ያኔ ነውረኞቹን የደገፈው ዓለም ከነውራቸው ብዛት የተነሳ ያፍራል፡፡

ትህነግ ከአንድ ትልቅ ሀገር አንድ መለኪያ ውስኪ የሚበልጥባቸው መሪዎች እጅ ገብታለች፡፡ በራሳቸው ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋትን ፈርደው ህጻናትን ከሞት ጋር አጋፍጠዋል፡፡ ብዙዎችን እንደ ቅጠል አርግፈዋል፡፡ በፊት የሞትነው መሬታችን ላይ መጥተው ነው ያሉትና ዓለም የተቆረቆረላቸው አማጺዎች አሁን ሞት ፍለጋ ሌላ ሰፈር ሌላ ምድር ገብተው ሲያልቁ ምላሹን ዓለም ባላየ ዝም ብሎታል፡፡

ይሄ ስቆቃ መጨረሻው ነው እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል አሁን ሁሉም ነገር ነበር ይሆናል፡፡ ትህነግን ነበረች ለማስባል ከገበሬ እስከ ወጣት ከሀገር መከላከያ እስከ ክልሎች ልዩ ሃይል ሆ ብሎ ተነስቷል፡፡

ዓለም ፊት እጅ እግር የሌለው ሀሳብ እንዳላቸው ያሳዩት የትህነግ መሪዎች ራበው ላሉት ወገናቸው ሞት ጋብዘውታል፤ ጦርነትን እንደ ቀለብ እያረቡለት ነው፡፡ እንደ ድሮው ዘመን እቃ በእቃ እስኪገበያይ አድርሰውታል፡፡ በራሱ ልጆች ሁለት ሞት የሞተ ህዝብ አድርገውታል፡፡

ጦርነቱ ከአብይ ጋር እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር አይደለም የሚለው የሞኝ ሀሳብ በኢትዮጵያ ምድር ቦታ የለውም፤ ኢትዮጵያ መሪዋ ችግር ካለበት ትቀጣለች እንጂ ሀገር ላፍርስ ብሎ በቅጥር ለመጣ የሀገሯን ምልክት አሳልፋ አትሰጥም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top