Connect with us

ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ
የባህርዳር ከተማ ኮምኒኬሽን

ዜና

ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

ለከተማችን ሰላምና ደህንነት ጠንቅ የሆኑ አፍራሽና ሰርጎ ገብ ኃይሎችን መላው የከተማችንና አካባቢው ነዋሪ ከአመራሩ ፣የፀጥታ ኃይሉና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀት የመጠበቅ እንዲሁም ግንባር ድረስ የህይወት መስዋዕት እየከፈለ ላለው ሰራዊት በስንቅ አቅርቦትና የኃይል ደጀንነት በማሳየት በኩል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

ይህን አስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ እየተደረገ ለሚገኘው የህልውና ትግል ውጤታማነት ዙሪያ ስላለው የማህበረሰብና መሰል አካላት አደረጃጀትና የአካባቢ ጥበቃን አስመልክቶ ዛሬ በ11/12/2013 መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሀገራችን አብልጦም ክልላችን ጦር ጠማኝ በሆነው የትህነግ አሸባሪ ኃይል ሀገር የማፍረስ እኩይ ሴራ ሳንወድ በግድ ወደ ጦርነት መገባቱን በማንሳት ለዚህም ስኬታማነት በከተማችን ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡

በዋናነት ለልዩ ኃይል ፣ሚሊሻና መከላከያ ደጀን የሚሆን ኃይል ከመመልመል እስከ አሰልጥኖ እስከመላክ ፣በገንዘብ አሰባሰብ ፣በስንቅ ዝግጅትና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከከተማ እስከ ቀበሌ ተዋረዳዊ አደረጃጀት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም የአሸባሪው ቡድን ሀገር የማፈራረስ ተልዕኮ በውስጥ ሰርጎ ገቦች እና በውጭ ኢትዮጵያ ጠል ኃይሎች ድጋፍ የትግሉን ውጤታማነት ውስብስብ እያደረገው ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህን በሰላማዊ ህዝብ ላይ ዘግናኝና አረመኔያዊ ተግባር እየፈፀመ ያለው ሽፍታ ህገ-ወጥና ሰርጎ-ገብ አካላትን እየተጠቀመ እንደሆነ በከተማችን ባህርዳር በተደረገው ጥብቅ ክትትል መረጃዎች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ ከተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ከማህበረሰቡ እና ፀጥታ ኃይሉ ጋር እያደረገ ላለው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንቅፋት እየሆነ የመጣውን የሌሊት የሰው፣ ተሸከርካሪም ሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ከተፈቀደላቸው 120 ባጃጆችና ውስን የመንግስት ተቋማት እንደ ሆስፒታል ካሉት በስተቀር በሌሎች ላይ ከምሽት 2፡00 ሰዓት እስከ ንጋት 12፡00 ሰዓት ገደብ መቀመጡን ገልፀዋል፡፡

ሆኖም ግን ብለዋል ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ይህ የሰዓት ገደብ መወሰን ያልተመቻቸው የጠላት ተባባሪ የሚመስሉ አካላት የተለያዩ አሉባልታዎችን በማሰራጨት ላይ በመሆናቸው መላው የከተማችንና አካባቢው ህዝብ ለሰላምና ደህንነታችን ሲባል የተወሰደ እርምጃ መሆኑን በመገንዘብ እና አሁን ያለውን የጠላት የኃይል አሰላለፍ ስልት አደገኛነት በመረዳት ለጠላት በማይመች መልኩ  በየአካባቢው ከሚገኝ የመንግስት መዋቅር ጋር ወጥ በሆነ አደረጃጀት አካባቢውን መቆጣጠር ፀጉረ ልውጥ የሆነ አካል ሲገኝም ለሚመለከተው የፀጥታ ኃይል ማስረከብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ከተፈቀደላቸው የግልና የመንግስት የጦር መሳሪያዎች ውጭ ህጋዊ ያልሆነ የጦር መሳሪያ መያዝ እንደማይቻልና ያልተመዘገበ መሳሪያ ያለው በአካባቢው ለሚገኝ ሰላምና ደህንነት ተቋም አሳውቆ ጊዜአዊ ፍቃድ መያዝ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

እኒህንና መሰል የተላለፉ እገዳዎችን የሚጥስ አካል ቢኖር ለህዝብ ደህንነትና ሰላም ሲባል መንግስት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ የትግሉን ውጤታማነት እና የማህበረሰቡን አንድነት የሚፈታተኑ አሉባልታ ወሬዎችን ወደ ጎን በመተው በትክክለኛ ምንጭ ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን መቀበል እንጂ ተጨባጭነት የሌላቸውና የጁንታው ፕሮፓጋንዳ ማስፈፀሚያ ለሆኑ አጀንዳዎች እጅ ባለመስጠት ይህን ክፉ የፈተና ጊዜ በተባበረ የአንድነት መንፈስ በንቃት ፣በብልሃት ልንወጣው እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአንድነት ተደራጅተን አማራን ህዝብ ህልውና የሚፈታተኑ ጥቃቶችን በመከላከል የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት እናረጋግጣለን!!!

ድል ለመላው ህዝብ!!

(የባህርዳር ከተማ ኮምኒኬሽን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top