Connect with us

በትግራይ ካህናት ላይ ሞት የፈረዱት የትህነጉ ምሁር ዶክተር ክንደያ

በትግራይ ካህናት ላይ ሞት የፈረዱት የትህነጉ ምሁር ዶክተር ክንደያ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

በትግራይ ካህናት ላይ ሞት የፈረዱት የትህነጉ ምሁር ዶክተር ክንደያ

በትግራይ ካህናት ላይ ሞት የፈረዱት የትህነጉ ምሁር ዶክተር ክንደያ

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ባስተማሩት ልጅ ህይወት ሲመሳቀል፣ ኑሮ ሲዛባ፣ ነፍስ ሲጠፋና ተስፋ ሲጨልም ከመመልከት በላይ ምንም ነገር የለም፡፡ ትህነግ ያበላትንና ያጠጣትን እጅ ከመንከስ አልፋ መቆርጠምና ማላመጥ ጀምራለች፡፡ ያው እየዋጠችው እንደሆነ ስራዋ ምስክር ነው፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት ያወጀው ትህነግ ዓለም ዝም ያለው የጦር ወንጀለኛ ሆኖ እልቂቱን ቀጥሏል፡፡ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር ክንድያ የትግራይ ካህናትን የጦር ሠራዊታቸው እና የጥፋታቸው አካል አድርገው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ምሁሩ በቲውተር ገጻቸው ከምስል ጋር ይፋ ባደረጉት መረጃ የትግራይ ካህናት ውጊያ ላይ መሆናቸውና ኢትዮጵያን ለመታገል እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ እንደማወደስ የሚያደርገው ሀሳብ ነው ያስቀመጡት፡፡

እኔ ያሳሰበኝ ግን ወዲህ ነው፤ ሰውዬው በካህናቱ ነፍስ መጫወት የፈለጉት ቁማር ምን አይነት ነው? እርግጥ ነው ቁጥሩ ቀላል የማይባል ቄስ ትህነግን አይደለም ዛሬ ትናንት በትጥቅ ትግሉ ወቅት የአባቶቹን የወርቅ መስቀል ከገዳም እያወጣ እያቀበለ ቅርስ አውድሞ መሳሪያ መግዣ ሲያዋጣ ነበር፡፡

አሁንም ከዝርፊያው ተጠቃሚ የሆነና በትህነግ መዋቅር የቤተ ክህነቱ ጁንታ የነበረ ቁጥሩ የማይናቅ ሀይማኖት መሪ ነኝ ባይ ታጋይ እንዳለ እናውቃለን፡፡ መስቀል እፈልጋለሁ በሚል ሽጉጥ ስቦ ያስፈራራው ቄስ ማን እንደሆነ ታውቁታላችሁ፤

ይሄም ሆኖ ግን በትግራይ ብዙ ንጹህ ቄስ አለ፡፡ ፈጣሪውን ብቻ ከማገልገል ውጪ ከጁንታው ዝምድና የሌለው ካህን ብዙ ነው፡፡ የዶክተር ክንደያ አባባል ግን ህወሃትን ለመደምሰስ ከፈለግህ ቄሱን ሁሉ በለው ዓይነት የጅምላ ሞት አዋጅ ነው፡፡

ዶክተሩ በቲውተራቸው አንድ ቄስ ጠላት ያሏትን ሀገር የኢትዮጵያን ሠራዊት ዲሽቃ ጀግና ላሉት የትግራይ ሠራዊት ሲያስረክቡ ከምስል ጋር አስፍረው እንዲህ ነው ጀግና ይላሉ፡፡

እንግዲህ በጦርነት የእኛ ካህናት የተኩሱ አካል፣ የሠራዊቱ አባል ናቸው ብሎ በካህናቱ ላይ በዚህ ደረጃ ምስክርነት መስጠት ውጤቱ ምን እንደሆነ መተንበይ አያቅትም፤ ዶክተሩ ይሄንን ማድረግ ለምን እንደፈለጉ ግልጽ አይደለም፡፡ 

የትኛውም ትህነግን መደምሰስ የሚፈልግ ሃይል የትግራይ ካህናትን እንዲጠራጠርና እንዲያጠቃ ግን ተጨባጭ ምስክርነት የሰጡ ሰው ናቸው፡፡

በገዛ ልጆቹ ሞት የታወጀበት የትግራይ ህዝብ ያለ ወንድና ያለ ተተኪ ወጣት እንዲቀር ማድረጋቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ በይፋ አረጋውያኑና ካህናቱ በጥቂት ተባባሪዎቻቸው ሳቢያ ስም ተሰጥቷቸው መጠቀሚያ መሆናቸው ያሳዝናል፡፡

ሰዎቹ እንዴት ለትግራይ ቄስ ሳይራሩ ለሌላው ቋንቋ ቄስ ርህራሄ ይኖራቸዋል፡፡ እንዳሉት ያደረገውን ቄስ አደባባይ አውጥተው በአንድ ቄስ በአስርና በመቶ ቄስ ሳቢያ ሁሉንም ጥርጣሬ የሚከት ቅስቀሳ ማድረግስ ሌላው ዘንድ የሚፈጥረው ቁጭትና ጥቃት ምን እንደሚሆን ጠፍቷቸው ነው፡፡ መማርስ የራስን ወገን ከጥፋትና ከእልቂት ካልታደገ ምን ረብ አለው?

ለማንኛውም ግን ጨካኙ ዶክተር ጨካኝ ሀሳብ አስፍረው ብዙ ኪሳራ እንደሚያደርሱ ሳስብ አሁንም ያ ምስኪን ህዝብ ያሳዝነኛል፡፡ በሀገር ብር ውስኪ አትጠጡም ሲባሉ ደሙን ጠጡት፡፡  

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top