Connect with us

አምራች ዘርፉን የሚደግፍ የታክስ ማሻሻያ ወጣ

የገንዘብ ሚኒስቴር

ኢኮኖሚ

አምራች ዘርፉን የሚደግፍ የታክስ ማሻሻያ ወጣ

አምራች ዘርፉን የሚደግፍ የታክስ ማሻሻያ ወጣ

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሚደረግ ጥረት ይበልጥ ለመደገፍና ለማሳካት የሚያስችል የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ።

የጉምሩክ ታሪፍ አወቃቀሩን በማሻሻል የግብርናና የአምራች ዘርፉን በመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት የሚያስችል የሸቀጦች አመዳደብ ሥርዓት እውን የሚያደርግ የጉምሩከረ ታሪፍ ማሻሻያ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ሲሰራ ቆይቶ ከሚመለከታቸው አማራች ዘርፈች ተደጋጋሚ ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ በአሁን ጊዜ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ይፋ ሆኗል፡፡

ማሻሻያው ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም ከጉምሩክ ኮሚሽን በተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተቋቋመ የታሪፍ ኮሚቴ የተዘጋጀ ሲሆን የቀረጥና ታክስ ማሻሻያው እስከ 8 ሺ የሚሆኑ የታሪፍ መስመሮች የሚያካትት ሲሆን ማሻሻያው ትኩረት ያደረገው በጥሬ እቃዎች፣ በከፊል የተመረቱ ግብአቶች፣ ካፒታል እቃዎች እንዲሁም መሰረታዊ የሚባል የፍጆታ እቃዎችን የሚያካትት ነው፡፡

የግብርናና የአምራች ዘርፉን በመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት የሚያስችልው የቀረጥና የታክስ ማሻሻያው ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት እንዲቻል የአገር ውስጥ አምራቾች ከታሪፍ አንፃር ከውጭ ከሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች አኳያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ሁለት ስልቶች ተነድፈዋል፡፡

አንደኛው የምርቱ ዓይነት በአገር ውስጥ በሚፈለገው መጠንና ጥራት የሚመረት ከሆነ ከውጭ በሚገባው ተመሳሳይ ምርት ላይ ከፍተኛ የታሪፍ መጣኔ በመጣል የአገር ውስጥ ምርት ይበልጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

ሁለተኛ ደግሞ ምርቱ በአገር ውስጥ በብቃት የማይመረት ከሆነ ከውጭ በሚገባው ተመሳሳይ ምርት ላይ ከፍተኛ የታሪፍ መጣኔ ቢጣል የምርት እጥረት በማስከተል የዋጋ ንረት የሚያስከትል በመሆኑ እነዚህን ምርቶች በአገር ውስጥ ለሚያመርቱ አምራቾች ምርት ለማምረት የሚጠቀሙባቸው በአገር ውስጥ የማይገኙ ግብአቶች በዝቅተኛ የታሪፍ መጣኔ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ ማድረግ ነው፡፡

ማሻሻያውን ተግባራዊ ለማድረግ እስከ 8 ሺ የታሪፍ መስመሮች የሸቀጥ አመዳደብ ስርአትን የያዘ የታሪፍ መለያ ዝርዝር ኮዶችን የያዘ የታሪፍ ጥራዝ (Tariff Book) የተዘጋጀ ሲሆን የቀረጥና ታክስ ማሻሻያው በሁሉም ዘርፎች በቀጣይ 10 ዓመታት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትና ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ታወቋል፡፡

ከዚህም በተጫማሪ ማሻሻያው አገራችን በንግድ ዘርፍ ለምታደርጋቸው ስምምነቶች መሰረት የሚጥል ይሆናል፡፡

ዝርዝሩ በመ/ቤቱ ድረ-ገፅ ይገኛል።
(የገንዘብ ሚኒስቴር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top