Connect with us

የሚገርመኝ ሴትየዋ ያለ ልኩ ጠቅላያችንን ማግኘት አለመቻላቸው ሳይሆን ፤ አሜሪካ በአግባቡ እኛን ማወቅ አለመቻሏ ነው!

ፎቶ:- ሳማንታ ፓወር እና የሱዳኑ ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ

ነፃ ሃሳብ

የሚገርመኝ ሴትየዋ ያለ ልኩ ጠቅላያችንን ማግኘት አለመቻላቸው ሳይሆን ፤ አሜሪካ በአግባቡ እኛን ማወቅ አለመቻሏ ነው!

የሚገርመኝ ሴትየዋ ያለ ልኩ ጠቅላያችንን ማግኘት አለመቻላቸው ሳይሆን ፤ አሜሪካ በአግባቡ እኛን ማወቅ አለመቻሏ ነው!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ስሪታችን ከአሜሪካ ይልቅ ለአውሮፓ በቅጡ የሚገባ ይመስለኛል፡፡ ቢያንስ አሜሪካ ስለሚባል ሀገር መንግስትና ህዝብ አንድም የዓለም ክፍል ሳይሰማ፣ ሳያውቅ ወይም እነሱ እንደሚያምኑት በኮሎምቦስ ሳትገኝ እኛና አውሮፓ ባህር ተሻጋሪ ትውውቅ ነበረን፡፡

ሳማንታ ፓወር ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ዓላማቸው ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ዓላማቸው ማለት ግን ስውሩ ሳይሆን ገሃዱ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ስውሩ ዓላማቸው ገሃድ፣ ገሃዱ ዓላማቸው ስውር ሆነ፡፡

አንድ ስንዴ ቀቅሎ ከሸር ጋር ላፈረሰው ሀገር እደርሳለሁ እያለ በስውር ዓለምን የሚያምስ ተቋም መሪ ወደ አንድ ጦርነት ገጥሟታል ወደተባለች ሀገር ሲመጣ ቢያንስ ገሃድ የወጣ ዓላማው ስንት ኩንታል ስንዴ እናምጣ ማለት ይመስለኛል፡፡

እኛ ሀገር ስንት ኩንታል ስንዴ እንደሚያስፈልገን ጠንቅቆ የሚያውቀው አቶ ምትኩ ከሳ የሚባሉት የአደጋ ስጋት ኮሚሽነሩ የሚመሩት ተቋም ነው፡፡ እዚያ ደርሰው እዚያ አውርተው እዚያ ሰጥተው መመለስ ይችሉ ነበር፡፡

ስውሩ ዓላማቸውን አስመልክቶ ከሃገራቸው እግራቸውን ሳያነሱ እኛ አውቀነው ነበር፤ ገሃድ በወጣውም ዓላማቸው ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል፡፡ ወይዘሮዋ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርን ለማግኘት ሞክረው እንደነበረና እንዳልተሳካላቸውም ገልጸዋል፡፡

ሀገር ነንና፣ ሊያምው የሺህ አመት የዲፕሎማሲና የውጪ ግንኙነት ታሪክ ያለን ሀገር እልፍኙ ማን ማንን ማናገር እንዳለበት በቅጡ ይታወቃል፡፡ እሱ ሳይሳካላቸው መቅረታቸው ብዙም አይደንቀኝም፤ ይልቁንም እኛ አሜሪካን በቅጡ ሳታውቀን መቅረቷ ግን ይቆጨኛል፡፡

አሜሪካ ብዙ የሞከረቻቸው የጣልቃ ገብነት ሙከራዎች አሉ፤ የራሷ ያልነበሩ ሉዓላዊ ሀገራትን አፍርሳ የራሷ ማድረግን ግን አሳክታው አታውቅም፡፡ ከዚያም ሲያልፍ ዘመኗን ሙሉ ስትሞክር የኖረችው ሙከራ ዛሬም ድረስ ሳይሳካ አዲሱ የዓለም ትውልድ እኩይ ሀሳቧን በቅጡ የተገነዘበበትም አውድ አለ፡፡

አንድ ነገር መታወቅ ያለበት አሜሪካ ከግዛቶቿ በአንዱ የማትፈጽመውን አንዳች መብት ሳይኖራት በታላቅ ሀገር ሉዓላዊነት የውስጥ ጉዳይ ከአሸማጋይነትም ከመካሪነትም በዘለለ አለንጋ ይዤ ልቁም ብላለች፡፡

ያላትን ሁሉ እናውቃለን፡፡ ያለንን ሁሉ አታውቅም፡፡ እንደ አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ብራችን ላይ በፈጣሪ እንታመናለን ብለን ልባችን ላይ ግን በጉልበታችን መታመንን ያላተምን ነን፡፡ በፈጣሪ የምንታመን ህዝቦች ነን፡፡

በጉዳይ የማንገባውን ያህል በእኛ ጉዳይ ማንም መብት እንዳለው አስበንም አምነንም አውቀንም አናውቅም፡፡ ያንን አሜሪካንን ታህል ሀገር ሳታውቅ መኖሯ ይቀጨናል፡፡

ይህ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ወዳጅነት ላይ አንድ ታሪክ የማይረሳው ጠባሳ ሆኖ ይኖራል፡፡ የተሞከረው ሙከራ መልኩን እየቀያየረ የኢትዮጵያን ጥቅም ክብርና አንድነት እንደሚጎዳም አይተናል፡፡ ማን ያውቃል? የምንታመንበት ፈጣሪ የሚያሳየን ይኖራል፡፡

አሜሪካኖቹ ጣልቃ በገቡባቸው ብዙ ሀገራት ብዙ ነገር ገጥሟቸው እንደነበር እናውቃለን፡፡ በኢትዮጵያ የሚሆነው ግን የተለየ ነው፤ ጣልቃ መግባት በራሱ የሚቻልባት ሀገር አይደለችም፡፡ ያንን ዓለም የሚያይበት ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ደርሰናል፡፡

የኢትዮጵያውያን ልቦች የሚማረኩት በዘዴና በፍቅር ነው፡፡ ዘዴና ፍቅርን አሽቀንጥሮ በጫና ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን አንገት ለማስደፋት የቀጠለው ጥረት ኢትዮጵያውያንን ቀና ወደሚያደርገት የታሪክ ምዕራፍ እንደሚያሻግረን እምነቴ ነው፡፡
ፎቶ:- ሳማንታ ፓወር እና የሱዳኑ ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top