Connect with us

እምባ ጠባቂ ዘንድሮ 4ሺ 456 አቤቱታዎች ቀረቡልኝ አለ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

ዜና

እምባ ጠባቂ ዘንድሮ 4ሺ 456 አቤቱታዎች ቀረቡልኝ አለ

እምባ ጠባቂ ዘንድሮ 4ሺ 456 አቤቱታዎች ቀረቡልኝ አለ

በ2013 በጀት ዓመት 3 ሺ 800 አቤቱታዎችን ለመቀበል አቅጄ 4 ሺ 456 አቤቱታዎችን አስተናግጃለሁ” ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ገለፀ፡፡

ተቋሙ አዲስ ያቋቋመዉ 7502 የጥሪ ማዕከል ስራ መጀመር የአቤቱታ አቅራቢዉን ቁጥር እንዲጨምር አድርጎታል ሲሉ በተቋሙ የህግና አስተዳደር በደል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ቀኘ በሪፖርታቸዉ ላይ ጠቁመዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቀረቡት አቤቱታዎች መካከል 2 ሺ 4 መቶ 3ቱ በተቋሙ ስልጣን ስር የማይወድቁ በመሆናቸዉ ተገቢዉ የሕግ ምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸዉ መሰናበታቸዉን፣1 ሺ 50ዎቹ አቤቱታዎች ደግሞ በተቋሙ ስልጣን ስር የሚወድቁ ቢሆኑም ደረጃቸዉን ጠብቀዉ ባለመቅረባቸዉ ደረጃቸዉን ጠብቀዉ እንዲቀርቡ መረጃ የተሰጠ መሆኑን እና 1ሺ 3ቱ አቤቱታዎች ብቻ በተቋሙ ስልጣን ስር የሚወድቁ በመሆናቸዉ ለምርመራ ክፍል የተመሩ መሆኑን ዳይሬክተሩ አያይዘዉ ገልፀዋል፡፡

አቤቱታዎቹ የቀረቡበት መንገድም 2ሺ 3መቶ 58ቱ በአካል፣3መቶ 95ቱ በስልክ፣78ቱ በፖስታ፣4ቱ በፋክስ፣1ሺ 6መቶ 16ቱ በነፃ ጥሪ ማዕከል እንዲሁም 5ቱ በኢ-ሜይል የቀረቡ መሆናቸዉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የአቤቱታዎች አይነትም ስራን፣ ጡረታን፣ ይዞታን፣ ፍትሐዊ አገልግሎት አለማግኘትን፣ ትምህርትን፣ ከመረጃ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ለተሰጠ አሉታዊ ምላሽን፣ የካሳ ጥያቄን እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮችን አስመልክቶ እንደቀረቡ ተገልጿል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top