Connect with us

ዓለም ከሌላ ጋር ቆሞ፤ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ከሆነስ?

Social media

ነፃ ሃሳብ

ዓለም ከሌላ ጋር ቆሞ፤ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ከሆነስ?

ዓለም ከሌላ ጋር ቆሞ፤ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ከሆነስ?
ኢትዮጵያ የተዘረፈች፣ የተበደለች፣ የተገደለች ሀገር እንጂ በዳይ አይደለችም!

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)
አሜሪካዊቷ ወይዘሮ ሊመጡ ነው የሚለው ዜና ከዳር ዳር እንዲህ ብናደርግስ? እንዲህ ብናደርግስ? እያባባለን ነው፡፡ ሴትየዋ ብቅ አሉ ማለት ጉዳዩ እንደ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ የመን መሆን ነው የሚለው ስጋት አንዳንዶች ጋርም ተደምጧል፡፡

ኢትዮጵያን እንደፈረሱ ሀገራት ለማድረግ ያልተሞከረ ሙከራ መች አለና? ትህነግ ገና ትግራይን ነጻ አወጣለሁ እና እገነጥላለሁ ብላ በርሃ ስትገባ እኮ ጡጦ እያጠባች፣ አንቀልባ ይዞ አይዞሽ ያለችው አሜሪካ ነበረች፡፡

እንድንለያይ ያልሞከሩበት ጊዜ ያለ ይመስል አዲስ ሙከራ የሚጀመር ይመስል መጠርጠሩ የዋህነት ነው፡፡ እየሆነ ካለው ሁሉ ማለፍ የቻልነው የተገፋን እንጂ የገፋን ህዝቦች ስላልሆንን ነው፡፡ ብዙ ዋጋ ከፍለናል፡፡ በየቦታው የገጠመን ስደት ሞትና መፈናቀል ስውር እጁ ኢትዮጵያን ማድከም ነው፡፡ ውጤቱ ግን እንዳየነው ውሎ አድሮ አጋመደን፤
ኢትዮጵያ አልገፋችም ተገፋች እንጂ፡፡ አልገዛም አላለችም፤ እየተገደለች እየተዘረፈች፣ እየተሰደበች፣ ታሪኳ እየተንቋሸሸ ዝምታን የመረጠች ሀገር ናት፡፡ ውሎ አድሮ የበደሉ ጽዋ ሲሞላ የሆነው ከፈጣሪ እንጂ ከሰው አይደለም፡፡

ዓለም ተረድቶን አብሮን ቢቆም መልካም ነው፡፡ ግን ዓለም አብሮን ቆሞ ፈጣሪ ፊቱን ቢያዞርብን የመሳሪያው ብዛት፣ የገንዘቡ መጠን፣ የደጋፊው ቁጥር ለድልም ለፍትህም አያበቃንም፡፡ በተቃራኒው ዓለም ፊቱን አዙሮብን እና አድሞብን ፈጣሪ ከእኛ ጋር ከሆነ የትኛው ሃይል እንደሚቋቋመን ማሰብ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የታወጀው የመጨረሻው ግርግር ነው፡፡ ምናልባት ምጡ እየገፋው ተስፋ እና አዲስ ምዕራፍ የሚወለድበት ዋዜማ ላይ ሆነንም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው፤ በዳዮች ሳይሆን ተበዳዮች ሆነን ተገፍተናልና፤
ያመጹብን፤ ለምን ሰረቃችሁን ብለናቸው አይደለም፤ ከዚህ በኋላ አትሰርቁንም ስንል ሌቦች ዘርን መደበቂያ አደረጉ፤ የተገደልነውን አልቆጠርንም አሁን ግን አትግደሉን ስንል ግፈኞች ወደ ዘር ወሰዱት፤ እንዲህ ያለ ስበብ ዛሬ ለዚህ አደረሰን፡፡

አሁንም ቢሆን ሰላም እጅግ ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ የሰላምን አዋጪነት የሚክድም ሆነ የሚረሳ አልያም ጦርነት የተሻለ ጥቅም አለው ብሎ የሚያስብ ሰው የለም፡፡ ግን የሰላም ፍላጎታችን ዳግም ከጦርነት ይልቅ ግደሉን፣ ከግጭት ይልቅ ዝረፉን፣ ከትግል ይልቅ በድሉን የሚያስብል ምርጫ ይዞ አይመጣም፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ለጁንታው ሰላም የሚፈጥርለት ምንም ጥቅም የለም፡፡
ጥቅምን ፍለጋ ሊያውም አላግባብ ጥቅምን ለማስከበር የሚደረግ ጦርነት ለንጹሃን ነፍስ አይራራም፡፡ ንጹሃን ደህና መሆን አለመሆናቸውም ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡

እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል መርህ የእርዳታ እህል ሳይቀር እየሸጠ ትጥቅ ገዝቶ መንግስት የሆነ እና መንግስት ሆነ ሀገር የሸጠ ፓርቲ ከዚህ ያለፈ ሊያሳስበው የሚችል ነገር እንደማይኖር ግልጽ ነው፡፡

አሁን ዓለም እንዲህ ካለው ቡድን ጎን ሲቆም አላማው የቡድኑን አላማ ቅድስና የሚያሳየን ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚደረገው ሴራ ነው፡፡ ያ ሴራ አብሮን በቆመ ፈጣሪ እርዳታ ተረት ሆኖ የሚቀርበትና ትውልድ እየተረከ ዛሬን የሚታዘብበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top