Connect with us

አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የእንጦጦ የሥነጥበባት ማዕከልን በይፋ ተረከበ

አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የእንጦጦ የሥነጥበባት ማዕከልን በይፋ ተረከበ
ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና፣ አቶ አገኘሁ አዳነ፣ ዶ/ር እዝራ አባተ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የእንጦጦ የሥነጥበባት ማዕከልን በይፋ ተረከበ

አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የእንጦጦ የሥነጥበባት ማዕከልን በይፋ ተረከበ

በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የቅርብ ድጋፍና ክትትል በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ  የተገነባው የሥነጥበባት ማዕከል በይፋ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ተረክቦ እንዲያስተዳድረው ተወሰነ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይህንኑ በማስመልከት ባለፈው እሁድ ሐምሌ 18 ቀን 2013 ዓ.ም አንድ የምሥጋና ሥነሥርዓት አከናውኗል፡፡

አቶ አገኘሁ አዳነ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳይሬክተር ለድሬቲዩብ እንደተናገሩት የእንጦጦ የሥነጥበብ ማዕከል ጠ/ሚኒስት ዐብይ አሕመድ ለት/ቤቱ በገቡት ቃል መሰረት ከተመረቀበት መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ሥር ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው በአሁን ሰዓት ዩኒቨርሲቲው በይፋ ተረክቦ እንዲያስተዳድር በተወሰነው መሰረት ተፈጻሚ ሆኗል፡፡ የእሁድ ዕለቱም ፕሮግራም የምሥጋናና የርክክብ ሥነሥርዓት የተከናወነበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር “ይህ በዛሬው ቀን የዩኒቨርስቲአችን አንድ አካል እንዲሆን የምንረከበው የሥነ ጥበባት ማዕከል በሀገራችን ውስጥ ለሚገኙ የጥበብ ባለሞያዎችና ተመራማሪዎች የጥበብ ሥራዎቻቸውንና የምርምር ውጤታቸውን ወደ ህዝብ የሚያቀርቡበት ወይም የሚያስተዋውቁበት አንድ ትልቅ የመገናኛ ድልድይ ሆኖ ሊያገለግል የሚችል ተቋም ነው፡፡

የእንጦጦ የሥነ ጥበባት ማዕከል ሁለገብ የሆነና የተለያዩ የጥበብ ዘርፎች የጥበብ ውጤታቸውን የሚያቀርቡበት፣ ተመራማሪዎች በዘርፍ የሠሩትን የምርምር ሥራዎች በውይይት የሚያዳብሩበት በተጨማሪም ማዕከሉ በተለያዩ ዘመን የተሠሩ የዕይታና የድምፅ የጥበብ ሥራዎችን (ባህላዊና ዘመናዊ) ለተመራማሪዎችና ለጎብኚዎች አመቺ በሆነ መንገድ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ሊሠራ የሚችል የጥበብ ማዕከል ይሆናል የሚል ሙሉ እምነት አለን፡፡

የጥበቡ ዓለም የሰው ልጅን በተለየ መንገድ ማሰብ እንዲችል በማድረግ የአእምሮ አድማሱን ያሰፋለታል፤ በተለመደው የሰዎች ተግባቦት ሊገለፁ የማይችሉ ኃሳቦችን ተጠባቢው በቀለማት፣ በድምፅና በተለያዩ የጥበብ መገለጫዎች ሐሳቡን እንዲገልፁ ያስችሉታል፡፡

በመሆኑም መንግስት፤ በተለይም ደግሞ የሀገር መሪዎች ይህን ከግንዛቤ ወስደው ለጥበቡ ዓለምና ለጥበቡ ሰዎች ሊጠቅም የሚችል ግን ደግሞ የዚህን ዓይነት የጥበብ ማዕከል መገንባት ለሞያውና ለሞያተኞቹ ብቻ ሳይሆን ለሚታሰበው ሁለተናዊ ሀገራዊ እድገት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተረድተው ይህን የመሰለ ውብ የሥነ ጥበባት ማዕከል ሠርተው ስላበረከቱልን እጅግ የከበረ አድናቆቴንና ምስጋናዬን በአዲስ አበበ ዩኒቨርስቲና በተለይም ደግሞ በሥነ ጥበባት ኮሌጅ ስም ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

በተጨማሪም፤ ይህ የጥበብ ማዕከል ከመሠረቱ ጀምሮ ሲሰራ በየጊዜው በኃላፊነት ስሜት በራሱ ወጪ በመመላለስ በሥነ ጥበባት ኮሌጅ ከተሰጠው ኃላፊነት ጋር ደርቦ የሠራውን አቶ አገኘሁ አዳነንና እንዲሁም በዚህ ሥራ ውስጥ የተሳተፉትን ባለሞያዎች በተጨማሪም የዛሬውን ፕሮግራም በማስተባበር የሠሩትን ናቲንና ቲሙን በእጅጉ አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡

ዶ/ር እዝራ አባተ የኮሌጁ ዲን በበኩላቸው እንጦጦ የሥነጥበባት ማዕከሉ ሕዝቡንና የሥነጥበባት ተቋማትን በማቀራረብ ረገድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የስነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት  ከተቆረቆረበት ከ1950 ጀምሮ  በትንሽ ቤት አለፈለገ ሰላም በሚል ስያሜ አንድ ቦታ በሁለት የትምህርት ዓይነት ተማሪዎችን እያስተማረ ያስመርቅ ነበር። በአሁን ወቅት ት/ቤቱ በሰባት የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀበሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

ፎቶግራፍ፡- ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና፣ ዶ/ር እዝራ አባተ

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top