Connect with us

እስከአሁን ከተሰራው የዓለም የጦር ወንጀል አያትና የልጅ ልጅን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም አልተመዘገበም!

Social media

ነፃ ሃሳብ

እስከአሁን ከተሰራው የዓለም የጦር ወንጀል አያትና የልጅ ልጅን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም አልተመዘገበም!

እስከአሁን ከተሰራው የዓለም የጦር ወንጀል አያትና የልጅ ልጅን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም አልተመዘገበም!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

የትግራይ ህዝብ የዛሬ ምርጫ ምንም ይሁን ምን በዓለም ላይ ግን እንደ ትህነግ ጠላት እንደሌለው ነገ ፍንትው ብሎ ይታየዋል፡፡ አሁን እየሆነ ባለው ዘርፎ ገድሎ ባዶዬን ከምቀር ወገኔን ባዶ ላስቀር በሚል የወሰነው ጁንታ የሌላው ኢትዮጵያዊን ያህል ለትግራይ እንደማያስብ ታውቋል፡፡

በዓለም ታሪክ ብዙ የጦር ወንጀል ተግባራት ተመዝግበዋል፡፡ ዓለም እነኛን ኮንኗል፤ በቻይና አፍሪካ ሴራና በግድቡ ስውር ደባ ሳቢያ ወንጀሏን ደብቀው ምዕራባውያን ነውሯን ያላወጡባት ትህነግ የፈጸመችው የጦር ወንጀል ግን የትም እና መቼም አልሆነም፡፡

ሰው እንዴት ምን ቢጨክን አያቱን ለጦርነት ይማግዳል፡፡ አያት እንደ ሞርታር የምትማረክ የምትገደል የምትወድም መሳሪያ ናት ብሎስ ያምናል፡፡ ጦርነት ሲከፋ አያቱ ቀሚስ ስር ተሸጉጦ ንጹሃን አለቁ ለሚል ድራማስ እንዴት በገዛ ወገን ላይ በዚህ ደረጃ ይጨከናል፡፡

የጁንታው ጠባይ እንደሆነ ታሪኩም ቀድሞ ይነግረናል፡፡ የዛሬም አይደለም ያኔ ገና ትጥቅ ትግሉ ሲጀመር ሀውዜን ፊት ነሳችን ተብሎ በምሬት የሠራዊቱን ቁጥር ለማብዛት ሀውዜን ገበያ ላይ የተሰራው ሴራና ያለቀው ህዝብ ስውር አይደለም፡፡

የራስን ልጅ ጉያ አቅፎ እና የሰለጠነ ዓለም ልኮ የደሃ ልጅ እያፈሱ ጦርነት መማገድስ ምን ማለት ነው? ምን ቢጨከንስ እንዴት የልጅ ልጅን እንደ መትረየስ እና እንደ መድፍ ቆጥሮ ሲፈልግ ይደምሰስ ሲፈልግ ይማረክ በሚል ውጊያ ይገባል፡፡

ይህ የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ያለው ትግራይን ለማዳን በሚል ስውር ሴራ ቢሆንም በየቀኑ የምናየው ግን በንጹሃን ህይወት ላይ የጁንታውን ቁማር እና የትግራይን ጥፋት ነው፡፡ የእርዳታ እህል ጎዳናዎችን የጦርነት ቀጠና እያደረጉ ትግራይን ማዳን በምን መልኩ እንደሚቻል እንኳን መጠየቅ የቻለ አካል የለም፡፡

አዲስ አበባ እንገባለን ብሎ ህጻናትን ለጦርነት መመልመል ጥቅሙስ ምንድን ነው? ከዚህ ቀደም ወንድሞቻቸውና አባቶቻቸው በየበርሃው ወድቀው አዲስ አበባ የገባችው ትህነግ ከገቡበት ድህነት መች አወጣቻቸው፡፡ ሃያ ሰባት አመት በትህነግ አዲስ አበባ መኖርና ቤተ መንግስትን መቆጣጠር እውነት የትግራይ ደሃው ልጅ ተጠቃሚ ነበር?

የጦር ወንጀሉ ታሪክ ያወጣዋል፡፡ ለትግራይ ህዝብ ግን ዛሬም የተሰወረ አይደለም፡፡ የካናቢስ ጦርነት እናት ሀገር ታውጆባታል፡፡ የትግራይ እናት ራሱን የማያውቅ በሀሺሽ እንዲደነዝዝና እንዲያልቅ የተፈረደባት ልጇን ከጉያዋ እየተነጠቀች ነው፡፡ እንዲህ ያለ ነውረኛ ታሪክ ረዥም ጊዜ በፈጀ እና ሀቅ አንግቧል በተባለው የጸረ ደርግ ትግል እንኳን አልገጠመም፡፡ እኮ ለምን? የሚል የለም፡፡ 

በአፋር ግንባር የዘመቱት የትህነግ ሠራዊቶች ህጻናት ናቸው፡፡ ዓለም ምን አገባኝ ብሎ እንደ ትህነግ ትግራይ ላይ ጨክኗል፡፡ የጥቂት ስግብግብ ፖለቲከኞች ቁማር እያንዳንዱን የትግራይ ደጃፍ ሲያንኳኳና በመካከለኛ አፍሪቃ የማዕድን ጦርነት እንኳን ያልታየ ይሄን መሳይ የጦር ወንጀል ሲፈጸም ዝም ማለት ያሳዝናል፡፡

ጦርነት አንዴ ገጥመናል የሚባልለት ነው፡፡ በዚህ ብዙ ብሶት ባቃጠለው እና በደሉ በበዛ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፊት ህጻናቱን ግጠሙ ብሎ መላክ ውጤቱ ይታወቃል፡፡ እድሜያቸው ገና ቢሆንም እየሞተ አሳድጎ ትምህርት ቤት የሚያስገባቸው አካል አይደለም ፊት ለፊት የሚያገኛቸው፡፡ ጦርነት ነው የገቡት፤ ሲሞቱ ወይም ሲማረኩ ነው ጉዱ የሚታየው፡፡ እናም የጦር ወንጀለኛውን ትህነግ የትግራይ ህዝብ ስለ ኢትዮጵያ እንኳን ባይሆን ስለ ለጋ ልጆቹ ሲል አደብ ቢያስገዛቸው እላለሁ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top