Connect with us

ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚያስፈልገው ወሬ ሳይሆን ስንቅና ሎጀስቲክስ ነው!

ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚያስፈልገው ወሬ ሳይሆን ስንቅና ሎጀስቲክስ ነው!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚያስፈልገው ወሬ ሳይሆን ስንቅና ሎጀስቲክስ ነው!

ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚያስፈልገው ወሬ ሳይሆን ስንቅና ሎጀስቲክስ ነው!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)

ጸረ ትህነግን ዘመቻ መደገፍ በምንም መልኩ ጦርነትን መውደድ ተደርጎ መቆጠር የለበትም፡፡ የጌታቸው ረዳና የደብረ ጽዮን ምኞት የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ቤት የሚያተራምስ ጥፋትን እውን ማድረግ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ውድቀት የሚመኝ ሃይል ለምን አደብ ይገዛል? ማለት መመጻደቅ ይመስለኛል፡፡

እዚህ መንደር አንዱ ችግር ሀገርን የመውደድ ማሳያው ሀገር የሚጎዳ ተግባር መሆኑ ነው፡፡ የፌስ ቡክ ላይክ ለአንድ ወታደር አንድ ኮዳ ውሃ መሆን እንደማይችል እየታወቀ ሀገር የሚጎዳ ወሬ ማቀበል እና መቀባበል ፋሽን ሆኗል፡፡

እየተዋደቀ ላለ ሀገሩን አፍቃሪ ሰራዊት ሲሆን አብሮ ዘምቶ ከጎኑ በመውደቅ ኢትዮጵያን ማንሳት ነው፡፡ ካልሆነ ደግሞ ሎጀስቲክስ የሚፈልግ ዘመቻ ነውና ከሠራዊቱ ጎን ለመቆም ስንቅና ትጥቅ ማቅረብ ነው፡፡ ይሄንን ያልቻለ ዝምም ቢል ለድሉ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይቆጠራል፡፡

ህዝቡንና መከላከያን ለመከፋፈል የሚሰራ የትህነግን ሴራ ያለማገናዘብ በመቀበል እንዲህ ሆነ እያለ የፌስ ቡክ መንደር ላይ ማግለብለብ መጨረሻው የራስን እጅ በራስ እጅ መቁረጥ ነው፡፡ እርግጥ ነው የጥቂት የፌስ ቡክ ሠራዊት ያለ እውቀት የሚደረግ ጫጫታ የትም የሚደርስ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ግንባር እየተፋለመ ያለን ወገን ስሜት የሚጎዳ ስለመሆኑ ግን ደጋግሞ መንገር ያስፈልጋል፡፡

እንደ ብዙ ኢትዮጵያውያን ዳቦ መቁረጥ እየተቻለ በቆርጦ ቀጥል ወሬ እዚህና እዚያ እያምታቱ ማመስ አይጠቅምም፡፡ እስከአሁን ያሰበውን ለማሳከት እጅ ሳይሰጥ እየተፋለመ ያለው የትህነግ የዲጂታል ሚዲያ ሠራዊት ነው፡፡ እስከአሁን በአገኘው አጋጣሚ እጁን የሚሰጠው ደግሞ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ነኝ የሚለው ወገን የዲጂታል ሚዲያ ሠራዊት ነው፡፡

ተጽእኖ ቢኖረውም እንዲህ ያለው ተገላቢጦሽ ውጤት አልቀየረም፡፡ ከራያና ከማይጸብሪ የሸሸችው ትህነግ በዲጂታል ሚዲያዋ ወልዲያና ደሴን ብትቆጣጠርም መሬት ያለው ውጤት ሌላ ነው፡፡ እርግጥ ነው፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል ሰራዊት ነኝ ብሎ የሚያስበው ወገን ዲጂታል ወያኔ ሲያስለቅቀው እየፈረጠጠ ተማርኳል፡፡ እውነትን መቀየር የማይችለው ወሬ ግን በተቃራኒው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት ሀገር አፈርሳለሁ ያለውን አፍርሶታል፡፡

ሰዎቹ ያጡትን ሲያስቡት የትግራይን ህዝብ ሁሉን አሳጥተን በዓለም አቀፍ ጫና ተያይዘን እንወድቃለን እንጂ ዝም አንልም ብለዋል፡፡ እንዲህ ያለው ቁርጠኛ የጥፋት ተልእኮ ውሸት አያሳፍረውም፤ ዋሻ ገብቶ፣ ቄስ መስሎ፣ ከሰል ለብሶ አዲስ አበባን ልቆጣጠር ነው እያለ ይደሰኩራል፡፡

በተቃራኒው ፌስ ቡኩ ከእነሱ በስውር ያገኘውን የውሸት መረጃ ለሀገር ይጠቅም መስሎት ሲቀባበለው ይውላል፡፡ ማሸነፍን እየተመኘ ለመሸነፍ ይሰራል፡፡ እውነት ነው አፍቃሪ ኢትዮጵያው የፌስ ቡክ ሰራዊት በዲጂታል ወያኔው ተሸንፏል፡፡ እውነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት አስተማማኝ ክንድና ሀገሩን መታደግ የሚችል ሃይል ነው፡፡

እናም ስንቅና ትጥቅ ያቀበለ እየመሰለው ወሬ ሲያመላልስ የሚውለውና ወታደራዊ መረጃዎችን ጭምር ፌስ ቡክ ላይ የሚቀባበለው ሀገር አፍቃሪ ነኝ ባይ ሀገሩን ሊያጠቃ ከመጣው ጎን ቢሰለፍም ቁጥሩ ከእናት ሀገር ሠራዊት አይበልጥምና ከነወሬው ይቀራል፡፡ ወሬ ስንቅ አይሆንም፤

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top