Connect with us

ሄፓታይተስን መከላከል እና ክትባት

Social media

ጤና

ሄፓታይተስን መከላከል እና ክትባት

ሄፓታይተስን መከላከል እና ክትባት

ሄፓታይተስ ቢ በደም ውስጥ በሚሰራጭ ቫይረስ አማካይነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፍባቸው ዋና ዋና መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
• በቫይረሱ ከተያዘ ደም አሊያም የሰውነት ፈሳሽ ጋር በሚደረግ የቀጥታ ግንኙነት
• በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ከተያዘች እናት ወደ ሚወለደው ልጅዋ
• ከተያዘ ሰው ጋር በሚደረግ ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ
• መርፌዎችን በመጋራት ወይም ድጋሚ በመጠቀም (ለምሳሌ ያህል ለህገ ወጥ መድሀኒቶች መርፌ መጋራት ወይም በአግባቡ ያልተቀቀሉ መርፌዎችን ለመድሀኒት፣ ለአኩፓንቸር ለንቅሳት፣ ወይም ጆሮንና ሌላ የሰውነት ክፍልን ለመብሳት መጠቀም)
• በአግባቡ ያልተቀቀሉ የህክምና እቃዎች ወይም መርፌዎች ፡ የመንደር መርፊ ወጊዎች እቃዎች፣ የጥርስ ሀኪሞች ወይም የፀጉር አስተካካዮች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡

ሄፓታይተስ ቢ የማይተላለፍበት ሁኔታ
ሄፓታይተስ ቢ በአየር፣ በመተቃቀፍ፣ በመነካካት፣ በማስነጠስ፣ በማሳል፣ መፀዳጃ ቤት በመጋራትና በበር እጀታን በመንካት አይተላለፍም፡፡
በሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት አሊያም ቫይረሱ ያለበት ሰው ያዘጋጀውን ምግብ መመገብ በሽታውን አያስተላልፍም፡፡
በሄፓታይተስ ቢ የበለጠ ሊጠቃ የሚችለው ማነው?
ምንም እንኳን ሁሉም በሄፓታይተስ ቢ የመያዝ የተወሰነ እድል ቢኖረውም፣ የበለጠ የመያዝ እድል ያላቸው ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡ ስራቸዎ፣ የአኗኗር ዘይቤያቸው ወይም ሄፓታይተስ ቢ ካለባቸው ቤተሰብ መወለድ በቫይረሱ የመያዝ እድልን ከፍ ያደርጋል፡፡ እነዚህ በብዛት የተለመዱና “ከፍተኛ ስጋት” ያለባቸው ብለን ልንመድባቸው አንችላለለን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ግን ሁሉም አለመሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል፡፡
• ያገቡ ወይም ሄፓታይተስ ቢ ካለበት ሰው ጋር በቅርበት የሚኖሩ፤ ይህ አዋቂዎችን እና ህፃናትንም ይጨምራል፡፡
• ሄፓታይተስ ቢ በብዛት ባለባቸው ሀገሮች የተወለዱ ሰዎች ወይም ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚስተዋልባቸው አገሮች (ኤሽያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ፣ እና መካከለኛው ምስራቅ) የተወለዱ ወላጆች፡፡
• ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚታይባቸው ሀገራት (ኤሽያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ፣ እና መካከለኛው ምስራቅ) የሚኖሩ አሊያም ወደዛ የሄዱ ሰዎች፡፡
• ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ የሚፈፅሙ ጎልማሶች እና ወጣቶች
• ከተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲብ የሚፈፅም ወንድ
• ከተያዘች እናት የተወለደ ህጻን
• የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ሰራተኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ በሚገጥማቸው የደም ንክኪ፡፡
• ኤመርጀንሲ ፐርሶኔል
• አደገኛ እፅ ተጠቃሚዎች በሚወጉት መርፌ
• የሚነቀሱ እና ሰውነታቸውን የሚበሱ ሰዎች
• ተጠጋግተው ባሉ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ ተቋማት ወይም በጋራ በሚጠቀሙባቸው ነገሮች፡፡
የሄፓታይተስ ቢ ክትባት
የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ለሁሉም ጨቅላ ህፃናትና እድሜያቸው እስከ 18 ዓመት ለሆናቸው የሚመከር መሆኑን አለም አቀፉ የጤና ድርጅትእና በአሜሪካ ያለው በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር ማዕከል አሳውቀዋል፡፡ በአሜሪካ ያለው በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር ማዕከል ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ቡድኖች ውስጥ ያሉ ጎልማሶች መከተብ እዳለባቸው ይመክረል፡፡
የሄፓታይተስ ቢ ክትባት አስተማማኝና ውጤታማ ሲሆን ይህም ለተወለዱ ጨቅላ ህፃናት በሙሉ እና አድሜያቸው እስከ 18 ኣመት ለሆናቸው ልጆች ይሆናል፡፡ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ስኳር ላለባቸው ጎልማሶች እና ከስራ ባህሪያቸው ጋር በተያያዘ፣ የአኗኗር ዘይቤያቸው፣ የኑሮ ሁኔታቸው፣ እና በተወለዱበት አገር የመያዝ እድላቸው ከፍ የሚል ከሆነ ይመከራል፡፡
ሁሉም የመያዝ ስጋት ቢኖርበትም፣ ሁሉም ጎልማሶች አደገኛ የሆነውን የጉበት በሽታ በዘላቂነት ለመከላከል የሄፓታይተስ ቢ ን ክትባት መውሰድ አለባቸው፡፡ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት አስተማማኝ እና ውጤታማ ነው፡፡

ማስታወስ ያለብን ነገር በቫይረሱ ከተያዘች እናት የተወለደ ህፃን በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ የመጀመሪያውን ክትባት ማግኘት አለበት፡፡
• 1ኛው ክትባት- የተወለደው ህፃን በተወለደበት ክፍል እንዳለ ሊሰጠው ይገባል
• 2ኛው ክትባት- 1ኛው ክትባት ከተሰጠው ከአንድ ወር (28 ቀናት) በኋላ
• 3ኛው ክትባት- ከስድስት ወራት በኋላ የመጀመሪያው ክትባት ከተሰጠው (ወይም ቢያንስ ከ2 ወራት በኋላ 2ኛው ክትባት ከተሰጠው)
የግዴታ 16 ሳምንታት መኖር የግድ ነው፣ በ1ኛውእና በ3ኛውክትባት፡፡ የክትባት መርሀ ግብሩ ከተቋረጠ፣ ከታዘዘው በላይ መውሰድ ተገቢ አይደለም፡፡ ካቆሙበት መጀመር ይቻላል፤ ምንም እንኳን በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም፡፡
ከሄፓታይተስ ቢ ራስዎን የጠበቁ ስለመሆንዎ እርግጠኛ ለመሆን ቀላል የደም ምርመራ በማድረግ “የሄፓታይተስ ቢ አንቲቦዲ ምርመራ” (HBsAb) ክትባቱ ስኬታማ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት ይቻላል፡፡

ከሄፓታይተስ ቢ ራሴን ለመጠበቅ ሌላ ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?
ሄፓታይተስ ቢ የሚተላለፈው በተበከለ ደምና በተበከለ የሰውነት ፈሳሽ ስለሆነ፤ ክትባቱ እስከሚያልቅ ድረስ ሊከሰቱ ከሚችሉ መያዞች ራስዎን ለመጠበቅ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ቀላል ተግባራት አሉ፡፡
• በቀጥታ ደምንም ሆነ የሰውነት ፈሳሽን ከመንካት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡
• ከወሲብ አጋርዎ ጋር ኮንዶም ይጠቀሙ፡፡
• ህገ ወጥ የሆኑ መድሀኒቶችን እና የተሳሳተ የመድሀኒት ትዕዛዝን ከመጠቀም እንዲሀም ከመወጋት መቆጠብ ያስፈልጋል
• ስለታም የሆኑ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ምላጭ፣ የጥርስ ቡርሽ፣ የጆሮ ኩክ ማፅጃ፣ እና የጥፍር መቁረጫ በጋራ መጠቀምን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
• ለህክምና፣ ለጥርስ ህክምና፣ ለደረቅ መርፌ ህክምና፣ ለንቅሳት፣ እንዲሁም ጆሮን እና ሌላውን የሰውነት ክፍል ለመብሳት የተቀቀሉ መርፌዎችንና ሌሎች መገልገያዎችን መጠቀማችንን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡
• የፈሰሰ ደምን ለማፅዳት ጓንት ማድረግ እንዲሁም ያልቆየና ንፁህ ውሀ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
• ደም ከነኩ ወይም ካፀዱ በኋላ እጅን በውሀና በሳሙና በሚገባ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡
• ከምንም በላይ የሄፓታይተስ ቢ ን ክትባት መውሰድዎን እርግጠኛ ይሁኑ!(ቅዱስ ጻውሎስ ሆ/ል)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top