Connect with us

ሂሳብ ማወራረድ ያለበት አማራው ነው!

social media

ነፃ ሃሳብ

ሂሳብ ማወራረድ ያለበት አማራው ነው!

ሂሳብ ማወራረድ ያለበት አማራው ነው!
(ኦሃድ ቤንዓሚ)

ዘይሃፍር ድሙ ገረማሪያም ሽሙ! (“አይን አውጣው ድመት ስሙ ገብረማሪያም ነው፤” ቃል በቃል ትርጉም)

አይኔን በጨው የሚል ሰው ሲገጥማቸው ሐማሲዬኖች “አይን አውጣው ድመት ስሙ ገረማሪያም ነው፤” ስም ሌላ ተግባር ሌላ ሲሆንባቸው፤ የሚጠቀሙበት አገላለጽ ነው፤ አባባሎች የየራሳቸው ታሪክ አላቸው፤ ሰሞኑን አቶ ደብረጺዮን “የአማራ ሕዝብ ወንድማችን ነው፤” ሲሉ የመጣልኝ ይህ አባባል ነው፤ አዎ ህወሓት ባለፉት 8 ወራት ታፍኖ እንደ ተቀጠቀጠ ድመት የፊት ቧጨራ ጦርነት ስትራቴጂ ተከትሎ ሲቪሎችን የማስጨረስ ታክቲክ መጠቀሙ ከመከላከያ ሞራላዊ ውትድርና ጋር ስለማይሄድ መንግስት በራሱ ተነሳሽነት ተኩስ አቁሞ “በደንብ አስብበት፤ መልካም የሱባኤና የጥሞና ጊዜ ይሁንልህ፤” ብሎ ራሱን እንዲፈልግ ትቶት ወጥቷል፤ ነገር ግን ወያኔ እንደለመደው ከድራማ በኋላ ስም የማውጣቱን አባዜ ተከትሎ “ዘመቻ አባ አሉላ” ብሎ ድምቀት የለሹን ጭፈራውን በቋጨ ማግስት መግለጫዎችን አንጋግቶልናል፤ በጣም የሚገርመው አይን አውጣነቱ ግን “የአማራ ሕዝብ ወንድማችን ነው፤” የሚለው አላጋጭነቱ ነው፤

ከሃምሳ አመታት ቅጥፈት እና ሸፍጥ በኋላ እንዲህ አይነት ስላቅ ከወያኔ የማይጠበቅ ባይሆንም አሁንም የአማራውን ሕዝብ ማንነት እና የፖለቲካ ባህሉን የአለማወቁን ደረጃ ማሳያ ነው፤ ላለፉት 47 አመታት “አማራ ጠላቴ ነው፤” እያለ ሲያላዝን እና የአማራን ሕዝብ ለጥላቻ ዘመቻ፣ ለተግባራዊ ጥቃቶች፣ ለታቀዱና ዘመናት ለሚሻገሩ ከክኅደት እስከ መብት ረገጣ፣ ከመብት ረገጣ እሰከ አስሩንም የዘር ማጽዳት እርምጃዎች ላካተቱ ጉዳቶች ዳርጎት የነበረው ድርጅት አሁንም የአማራውን ሕዝብ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ውጊያውን እያጧጧፈ ባለበት ሁኔታ “የአማራ ሕዝብ ወንድሜ ነው፤” ሲልህ “ከዚህ የባሰ የሚገርም አይን አውጣነት የት ነው ያለው?” ብለህ ራስህን ትጠይቃለህ፤ ስራ ሌላ ስም ሌላ፤
አይን አውጣው የመቀሌው ድመት ስምህን ጠርቶ እና ለይቶ ውጊያ ከፍቶብህ እንደገና ወንድሜ ነው ሲልህ እንኳንስ ልብህን ሊያለሰልሰው ቀርቶ እልኩን ይጨምርብሃል፤ አቶ ደብረጺዮን ይህን የማለት ድፍረቱን ከየት እንዳገኙት አላውቅም፤ ግን የሰሜን ዕዝ ጥቃት እንኳን የአማራ ክልል ተወላጅ የሆነውን መርጠው የፈጸሙበትን ሁኔታ ከምኔው እንደረሱት ይገርማል፡፡

የአማራ ሕዝብ በታሪክ ዘመኑ እንደወያኔ አይነት ከሃዲ፣ ምቀኛ እና የበታችነት ስሜት ሞራላዊ መርሁን ያጠፋበት እኩይ ጠላት ገጥሞት አያውቅም፤ ነገር ግን ምላሹ እንደ አማራ ሳይሆን ምላሹን እንደኢትዮጵያዊ ሁሌም የሚያመዛዝንበት መስፈርት “ኢትዮጵያን ይጠቅማል ወይ?” ሆኖ ቆይቷል፤ እንደ አማራ ሆኖ ተደራጅቶ ከማንም ጋር ለመዋጋት እና “እከሌ ጠላቴ ነው እከሌ ስጋቴ ነው፤” ብሎ ለዘመቻ ይቅርና ራሱን እና ስሙን ከወያኔ እና መሰሎቹ የጥላቻ ዘመቻ ለማጽዳት የተቀናጀበት አጋጣሚ እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ኖሮ አያውቅም፡፡ (ለዚህ እርምጃው 7 ምክንያቶች ቢኖሩም አንዱን ብቻ ላስቀምጥ ብዬ ነው፤) ከዚህ ሁሉ እኩይ ተግባራት እና ማይ ካድራ ላይ ዘር ለይቶ ጭፍጨፋ ካካሄደም በኋላ ዛሬም “የአማራ ህዝብ ወንድሜ ነው፤” በሚል ድፍረት ሲናገር መስማት ለጆሮ ከመሰቅጠጡም በላይ ቁጭት የሚሰንቅ ድፍረት ከመሆን ሌላ ትርጉም የለውም፤

ምን አልባት “የሱባዔው ጥሪ” ፍሬ አፍርቶ ወያኔ የልብ ለውጥ አድርጎ ከሆነ ደግሞ የሚቀድሙ በርካታ ጉዳዮች አሉ፤ የመጀመሪያው ወያኔ በአማራው ሕዝብ ላይ የደቀነውን አፈሙዝ መዘቅዘቅ ነው፤ እዚህ ጋ ምንም በማያውቁ ሕጻናት ፊት አውራሪነት የተደራጀ ጦር እየላከ እዚህ ጋ ወንድሜ ነው ማለት በጣም አሳፋሪ ወራዳ የፖለቲካ ብሂል ከመሆን አልፎ የትግራይን ሕዝብ ደረጃ የሚያዋርድ መግለጫ ነው፤

እራሱ ከአማራ ተወልዶ የአማራ ጠላት ሆኖ እርፍ ያለው ጌታቸው ረዳ እንኳን ትላንት “ከአማራው (ልሂቃን) ህዝብ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን፤” ባለበት ማግስት ደብረጺዮን እንዲህ ሲሉ መስማት የመቀሌውን ድመት አይን አውጣነት ቁልጭ አድርጎ ከማሳየት እና ቁጭት መግቦ የገጠመውን ጠላት ምንነት ከማረጋገጥ ውጭ ለአማራው ህዝብ የሚፈይደው ምንም አይነት ጥቅም የለውም፤ ወያኔ ብልጥ መሆኑ ነው ሰሞኑን “የአማራ ልሂቃን” የሚል አገላለጽ ደጋግሞ መጠቀሙ፤ ግን ምን አይነት የጭፍንነት ልክ እንደሆነ ማሳያው መሆኑን እንኳን የሚገነዘብበት ብስለት የለውም፤ እግዚኦ መሐረነ ከጭፍንነት ጠብቀነ፤ ያስብላል፤
ትላንት “የአማራው ገዢ መደብ” ዛሬ “የአማራው ልሂቃን”? በዚህም በዚያም አማራው ላይ መንጠላጠል የወያኔ መለያ ሆኖ መቅረቱ ያሳዝናል፤ እስካሁን አንተ ጠላቴ ነው ያልከው ሕዝብ መካከል ታግሶ ታግሶ “ከዚህ በኋላ የወገኔን ጥቃት ዝም ብዬ አላይም፤” ብሎ ሲነሳ ለይቶ “ልሂቃን”ብሎ መናገሩ የሚገርም ነው፤ አሁን የአማራ ልሂቃን እና የአማራ ህዝብ ልዩነት የላቸውም፤ ለመሆኑ “ወያኔ እንጂ የትግራይ ህዝብ ጠላታችን አይደለም፤” እያለ ከፊት ለፊት እሰጥ አገባ ሲሸሽ የነበረው የአማራው ህዝብ አባባል ስህተት ሆኖ ታይቶት ይሆን? አለቀ አሁን ምዕራፉ ሌላ ነው፤

የአማራው ልሂቃን ግብዣውን በመርህ ደረጃ ተቀብሎታል፤
ወደማይፈለገው እና ሲሸሸው ወደነበረው የፖለቲካ ምዕራፍ የአማራ ሕዝብ ከማይካድራውና ከሰሜን ዕዙ አማራን መርጦ ከተፈጸሙት ጥቃቶች በኋላ ግብዣውን በመርህ ደረጃ ተቀብሎታል፤ አሁን አማራው ጦርነት የታወጀበት ሕዝብ ሆኗል፤ ስለዚህ ከዘመናት ትዕግስት በኋላ የ47 አመቱን ሂሳብ ወደሚያወራርድበት ምዕራፍ ውስጥ ዘው ብሎ ገብቷል፤ ይህ ለወያኔ ሞት ቢሆንም ለድርጅቱ መሪዎች ግን ትልቅ ደስታ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ከተለያዩ መድረኮች ጀርባ በተደጋጋሚ እንደሚሉት “አማራው ብሔርተኛነትን ከተቀበለ የትግላችን አላማ ከፍተኛው ስኬት ላይ ደርሷል፤” ብለው ስለሚያምኑና ይህም የዘመናት የውስጥ ምኞታቸው የሆውን ኢትዮጵያን የማፍረስ የቤት ሥራቸውን ቀላል አድርጎ ስለሚያሳያቸው ነበር፡፡

ነገር ግን አማራው ከኢትዮጵያዊነቱ እና ከሌሎች (ትጋራዋዩን ጨምሮ) ወገኖቹ ጋር ሳይጣላ ከመቀሌው ድመት ጋር ሂሳብ የሚያወራርደበትን የፖለቲካ፣ እና ሌሎችም አስፈላጊ አቅሞችን ያዳበረ ሕዝብ ነው፤ ለወያኔ የሚያዋጣው “እውነተኛ ሱባዔና እውነተኛ ንስሃ” ነው፤ ጠበንጃ ደቅኖ የአማራ ሕዝብ ወንድሜ ነው የሚለውን አሳፋሪ እና ወራዳ መግለጫ የአማራውን ቁስል በእንጨት እንደመውጋት ይቆጠራል፡፡
በርግጥም አሁን ሂሳብ ማወራረድ ያለበት አማራው ነው፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top