Connect with us

 አገር የሚያተራምሰው የህወሀት ፅንፈኛ አስተሳሳብ  መምከን አለበት!! 

አገር የሚያተራምሰው የህወሀት ፅንፈኛ አስተሳሳብ መምከን አለበት!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

 አገር የሚያተራምሰው የህወሀት ፅንፈኛ አስተሳሳብ  መምከን አለበት!! 

 አገር የሚያተራምሰው የህወሀት ፅንፈኛ አስተሳሳብ  መምከን አለበት!! 

(ገለታ ገ/ወልድ- ድሬቲዩብ  )

       በአገራችን ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከፍተኛ የብሄር ፖለቲካ ንትርክና የጥላቻ ትርክት ተዘርቷል ፡፡ የዚህ እሳቤ ዳራው የቆየ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፣ ከለውጥ በኋላም ቁስሉ መሻር ያልቻለው የአገር ባለንጣዎች ተቀናጅው የዘመቱበት እኩይ ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ በመሰረቱ ፅንፈኝነትም ሆነ ወደ ግብረ ሽበራ የሚያመራ የጥፋት ወንጀል የሚጠነሰሰው በብሄር ፣ በፖለቲካ ፅንፈኝነት ፣ በመደብ ትግል በተሰለፉና መደማማጥ በተሳናቸው አክራሪዎች ወይም በቆዳ ቀለምና በዘር ልዩነት በሚታምሱ ፅንፈኞች  ነው ፡፡ ህወሀት ከነዚህ አንዱ ነው፡፡

     የሁሉም ፅንፈኞች የጋራ መገለጫቸው  ግን ሰላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊና የሰከነ ትግል  አልቦዎች መሆናቸው ነው ፡፡ በቂም በቀልና ጥላቻ የተረገዘ ፣ በተዛባ ትርክትና በግፍ ጥቃት ተቦክቶ የተጋገረ ብሎም ዘግናኝና ለንፁሃን እልቂት መንስኤ የሚሆን ስጋት መፍጠርም  ነው አላማቸው ፡፡ ለዚህ ደግሞ ዘመን አመጣሹ  የኢንተርኔትና ማህበራዊ  ድረገፅ አሉባልታና ውዥንብር ከፍተኛ እገዛ  ያደርግላቸዋል ፡፡     

      በአገራችን የብሄር ፅንፈኞች አባት የሆነው የህወሀት ሃይልና ግብረ አበሮቹ አካሄድም  ከዚህ የቆሸሸ አስተሳሳብ የተለዬ አይደለም ፡፡ እነዚህ ግፈኛ ሃይሎች “የፖለቲካ አላማቸውን” ለማሳካት በሚል  ከሰበአዊነት ውጭ ዘር እየመረጡ ፈጅተዋል ፡፡ አንዳንዶቹ የእናትን ሆድ ቀደው የተረገዘ ህፃንን አውጥተው በመጣል ፣ አለፍ ሲልም የከብት ስጋና አጥንት እየቆራራጡ አሰቃቂ ቪዲዮ በመልቀቅ ህዝብ ለማሸበር ኳትነዋል ፡፡ ብሄራዊውን ጦር አጥቅተው ትጥቅ ለማስፈታት፣ የአገሪቱን መሪዎች ገድለው ደም ለማፋሰስ አቅደው ሞክረዋል ፡፡ 

 

የተተፋውን  አስተሳሳባቸው በህዝብ ላይ ለመጫን ባያችሉም !! 

      አለምአቀፍ ጽንፈኛና  አሸባሪ ቡድኖች የሚወስዷቸው ዘግናኝ ኢሰብአዊ እርምጃዎች ይታወቃሉ ፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በቅርባችንና በራሳችን ፅንፈኛ የፖለቲካ ወፈፌዎች ሲደገም ማየታችን ነው የሚያሳዛነው ፡፡ ህወሀት የራሱን ህፃናትና ወጣቶች ሳይቀር በጦርነት ውስጥ እየማገደ ፣ አገርን በቻለው አቅም እያወከ ፣ “ኢትዮጵያ ትፍረስ!! ” የሚል ግልፅ መፈክር አንስቶ ፣ በህልም እሩጫ የሚባዝነው ከፅንፈኛና  ግትር ባህሪው በመነሳት ነው፡፡ ታዲያ ይህን አይን ያወጣ ወንጀል ማንና እንዴት ለመታገስ ይቻለዋል !!?

        ሽብርተኝነት ከላይ ከላይ ሲመለከቱት የፖለቲካ ግብ ያለው ይመስላል ፡፡ ነገር ግን ጉልበትና አጉራ ዘለልነትን የሚያስቀደም ፣ መደማማጥና ጥሞናን  የማይወድ ውዳቂ አስተሳሳብ ነው ፡፡ ማንም ሆነ መቼም ቢያንቆለባብሰው ፣ ያውም በዚህ ዘመን የህወሀት መንገድ ግቡን መምታት  የማይችለውም ለዚሁ ነው ፡፡” የዘረፋና የኢፍትሃዊነት መሳሪዬ የሆነውን ስልጣን ደግሜ ልጨብጥ ” ብሎ ህዝብ ለማንበርከክ የተነሳው ህወሀት፣ ነገም ቢሆን የሰላም አማራጭን ሊመለከት አይችልም ፡፡ እየሞተም በጦርነት ትንፋሹ እንዲቆም ነው የሚመኘው ፡፡

   እናም መፍትሄውም የፖለቲካ ቀለም እየቀቡ ፅንፈኞች፣ በንፁሃን ደም እንዲጨቀዩ አለመፍቀድ ብቻ ነው ፡፡ ስለሆነም ሽብርተኞችን የገቡበት እየገቡ ጠራርጎ ማጥፋትና የሰው ልጅን በሰላም የመኖር መብት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ፡፡ ካልሆነ ግን የህግ የበላይነት እየደከመ ፣አጉራ ዘለሎች ያሻቸውን እያደረጉ ከቀጠሉ እጅን አጣጥፎ በአክራሪ ብሄርተኞችና ፅንፈኞች በየተራ መጠቃት ነው እጣ ፋንታችን ፡፡

            በመሰረቱ ሰላምም ሆነ የህዝብ ደህንነት ባልተረጋጋጠበት ሁኔታ ፣ ወይም ጉልበትና ሽብር የበላይነት ይዘው እንኳንስ ዲሞክራሲ አገርም እንደ አገር መቆም አትችልም ፡፡ ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ድርጅቶቹም ሆነ ለተከታዮቻቸው በግልፅ መታወቅ ያለበትና ሊታገሉለት የሚገባ አላማ መሆን አለበት ፡፡ መላው የፀጥታና የፍትህ አካላት ፣ የመከላከያ ሰራዊታችንና የየክልል ልዩ ሃይሎች እንዲሁም ህዝቡ ከዚህ በላይ ከባድ ተግባርና አገራዊ ሃላፊነት እንደሌለባቸውም መታወቅ አለበት ፡፡ በተቻለ መጠን ንፁሃንን በመነጠል ሽብርተኞቸችን ማንበርከክና አሸናፊ መሆን  ታሪካዊ የትውልድ ሃላፊነት ነውና !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top