Connect with us

ትግራይንና ትግራዋይን ትህነግ ዘር ማጥፋት አውጆባቸዋል፡፡

ትግራይንና ትግራዋይን ትህነግ ዘር ማጥፋት አውጆባቸዋል፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ትግራይንና ትግራዋይን ትህነግ ዘር ማጥፋት አውጆባቸዋል፡፡

ትግራይንና ትግራዋይን ትህነግ ዘር ማጥፋት አውጆባቸዋል፡፡

ለሌቦች የወንጀል ፖለቲካ ሕጻናት ተገደው በውጊያ ይሞታሉ!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

እንዲህ ያለ ታሪክ በኢትዮጵያ የረዥም ዘመን ታሪክ ውስጥም ተመዝግቦ አያውቅም፡፡ የትህነግ ነውር እጅግ የከፋና እጅ እግር የሌለው ነው፡፡ ብርቱ ነኝ ብሎ ትንኮሳ መፈጸም እና ወረራ ማድረግን ከሽንፈት በኋላ የኡኡታ ምክንያት ያደርጋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱን አስቀድሞ አልቀበልም አለ፡፡

እንዲሁ የተለቀቀን ከተማ ድል አድራጊ ነኝ እያለ በክንደ ብርቱነት አሸነፍኩ ሲል ተሳለቀ፡፡ ገና የማወራርደው ሂሳብ አለ ብሎ በረሃብ ለሚረግፈው ህዝብ ከመድረስ ይልቅ ተጨማሪ ቂምና ጥላቻን ለኮሰ፡፡ ፋኖበት ወረራ ጀመረ፡፡ የሚሆነው እየሆነ ነው፡፡

ትህነግ ትግራይና ትግራዋይ ላይ ዘር ማጥፋት አውጇል፡፡ የእርዳታው እህል እንዳይገባ የእርዳታውን ቀጠናና መስመር የጦርነት አውድ አድርጎታል፡፡ ነጋሪት ጎስሞ መሳሪያ አንስቶ ኢትዮጵያን አጠፋለሁ ብሏል፡፡ ውጤቱን እያየነው ነው፡፡

ግን በዚህ ሰዓት ዓለም እንኳን እርዳታው እንዲደርስ እንቅፋት አትሁኑብኝ ብሎ በተማጸነበት ጊዜ ሰው እንዴት በራሱ እናት አባት ላይ ላይ ይጨክናል? የትግራይስ ህዝብ እንደምን ያለ ፍቅር ይዞት ነው የጥሞና ጊዜ አልፈልግም ልጆቼን በሀሸሽ አደንዝዤ ብማግድ እመርጣለሁ ያለው፡፡

ጦርነት ላይ የሚታዩት ህጻናት ናቸው፡፡ በዓለም የጦር ህግ ወንጀል የሆነው የእድሜ ክልል ታልፏል፡፡ ህግ ተጥሶ ህጻናትን ሊያውም በሀሺሽ እያሰከሩ ከፊት በማስቀደም የጥይት እራት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በህጻናት ላይ አልተኩስም ብሎ የሚሸሸው የሀገር መከላከያና የአማራ ልዩ ሃይል እንኳን ጥረቱ አልሰራም፡፡ የተኩስ አቁሙን የአጣጣለው ሸማቂ አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ገብቶ ግንቦት ሃያ ማለት ፈልጓል፡፡ ሀሺሽ ላደነዘዘው እንዴት ይሄንን ታስባለህ ባይባልም ስካሩ ግን ከሌላው ኢትዮጵያዊ በላይ ትግራዋዩን እየጎዳው ነው፡፡

አሁን የትግራይ ቀጠና ለግብረ ሰናይ ተቋማት እንዳይመች በትህነግ ጦርነት ተጀምሮበታል፡፡ የነጠላ ተኩስ አቁም ስምምነቱ ቀልድ ነው ያለችው ትህነግ እንዳለችው ለምን የትግራይ ህዝብ አይረግፍም የሚል ታሪካዊ ድምዳሜ ላይ ደርሳለች፡፡

ለትግራይ ህዝብ አውቅልሃለሁ የሚለው አይሰራም፡፡ የሚበጀው ግን ሌላው ኢትዮጵያዊ ሀገሩን በጥላቻ ከሰከሩ በሀሺሽ ከተማመኑ፣ ሰላም ከማይፈልጉ ሀይሎች ነጻ ትሆን ዘንድ ማስቻል ነው፡፡ ለዚህ የሚከፈለውን ዋጋ ይከፈል የሚሉ ወገኖች አሁን ትዕግስቱ ማለቁን አውጀዋል፡፡

አማራ ክልል ማምሻውን ነገሩ እንዳበቃና ህልውናዬ አሳስቦኛልና በመሽኮርመም አላልፈውም ሲል ይፋ አድርጓል፡፡ ሲዳማ ደቡብና ኦሮሚያ ጉዳዩ የአማራ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህልውና ነው ብለዋል፡፡ ቀጣይ ቀናት የደስታው አስረሽ ምቺውና ዳንኪራው ይቀርና ደግሞ በየኢምባሲው ለቅሶውና ኡኡታው ይቀጥላል፡፡

እንዲህ ያለ የትግል ስልት ከማንም በላይ የትግራይን ህዝብ ይጎዳልም ያከስራልም፡፡ በዚህ የእርሻ ወቅት እረስ የተባለ ገበሬ እንቢ ብሎ ልዝመትና ከእናት ሀገሬ ልግጠም ካለ ውጤቱን መገመት ነው፡፡ አሁንም እድል አለ፡፡ ሰክኖ ማሰብና ሩቅ ማየትን የሚፈልግ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ለቆመው የትግራይ ህዝብ ከሰከሩት ልጆቹ የስካር ምክር ወጥቶ ምን ቢሆን ይሻላል ማለት አለበት፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top