Connect with us

“በሸማኔ ላብ ቀልድ የለም” የሚለው የአርባ ምንጭ አዲሱ የሸማ ፓርክ

"በሸማኔ ላብ ቀልድ የለም" የሚለው የአርባ ምንጭ አዲሱ የሸማ ፓርክ
ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

“በሸማኔ ላብ ቀልድ የለም” የሚለው የአርባ ምንጭ አዲሱ የሸማ ፓርክ

“በሸማኔ ላብ ቀልድ የለም” የሚለው የአርባ ምንጭ አዲሱ የሸማ ፓርክ

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የጥበበኞች መናገሻ በሆነችው አርባ ምንጭ ከተማ በነበረው ቆይታ ወደ አንድ የእደ ጥበብ ፓርክ ጎራ ብሏል፡፡ ልበታቸው ተበዝብዞ ህይወታቸው ያልተቀየረውን የሽመና ባለሙያዎች አዲስ ተስፋ ስለሰነቀው ፕሮጀክት እንዲህ ያወጋናል፡፡)

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

ከጥለት የሚበልጥ ጥበብ ከወዴት አለ? እኔ የጥበበኞቹ መናገሻ ነኝ፡፡ ከውብ ምድራቸው ማግን ውብ አድርገው ሰውን ሞገስ ያጎናጸፉ ጥበበኞች ከሚፈልቁበት ምድር፡፡ አርባ ምንጭን በብሔራዊ ፓርኳ ታውቋታላችሁ፤ አሁን ደግሞ የሸማ ፓርክ እውን ሊሆንባት አዲስ የጥበበ ዕድ ፕሮጀክት ፈልቆባታል፡፡

የሽመና ባለሙያዎች ጥበበኛ ቢሆኑም ያ ጥበበኛነታቸው ተጠቃሚነታቸው ላይ ድርሻ የለውም፡፡ ብዙ ደክመው ያው በገሌ አይነት ህይወት ይኖራሉ፡፡ በቀላል ገንዘብ የተረከባቸው አካል አየር ላይ በብዙ ሺህ የሚሸጣቸውን ምርቶች በቀላል ዋጋ አስረክበው እንደውም ይሄ ሙያ አያዋጣም እያሉ ጥበበኛነትን የራቁ ብዙ ናቸው፡፡

አምራችን እንጂ ጥቅም ተጋሪ አይደሉም፡፡ ኬኩ ሲወደስ ጋጋሪነታቸው አይታወስም፡፡ እንዲህ ያለው አሰራር በኢትዮጵያ የጥበብ እድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሳንካ ሆኖ ሙያው እልፍ እንዳያፈራ እንቅፋት ሆኗል፡፡

አርባ ምንጭ ስደርስ ግን ወደ አንድ ስፍራ ወሰዱኝ፡፡ ገና ወራት ያስቆጠረ ነው የሚለውን ለማመን ከብዶኛል፡፡ ሸማ ፓርክ ነው፡፡ ያመርታልም፤ ያቀርባልም፡፡ ዓላማው የሸማ ምርቶችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አዘጋጅቶ ለገበያ ማቅረብ ነው፡፡

የሀሳቡ መነሻ የሸማኔው ጉዳት ነው፡፡ ሀሳቡን ያመነጩት ሰው ሸማኔ ነበሩ፤ ሽመናን ጥለው የኮሌጅ ባለቤት ሆኑ፡፡ ያ የጥበበኛ አለመጠቀምና ተጎጂ መሆን ይሄን ራዕይ እንዲያስቡ አደረጋቸው፡፡ ግዙፍን የሸማ ፓርክ እውን አደረጉ፡፡ አሁን ለውጪ ገበያ ሳይቀር በሳይንሳዊ መልኩ አምርተው ማዘጋጀት ጀምረዋል፡፡

ዓላማው ሸመኔውን በበቂ ሁኔታ የሙያው አውራና የጥቅሙ ተካፋይ ማድረግ ነው፡፡ ማቅመስ ሳይሆን ማብላት፡፡ ድርሻውን በአግባቡ መስጠት፡፡ ሙያው አልጠቀመኝም ከሚል ምሬት ባለሙያውን ስለማውጣት የሚያስበው ሸማ ፓርክ፣ የሥራ ማዕከል፣ የጉብኝት ቦታ፣ የሽያጭ ስፍራ ነው፡፡ ሁሉም አንድ ቦታ ይከናወንበታል፡፡

የተሰሩት ስራዎች ጎበኘሁ፡፡ እርግጥ ነው የሀገር ባህል አልባሳት ዋጋ ጣራ ነክቷል፡፡ ግን ዛሬም ጥበበኛው ሸማኔ ልጁን ጥሩ ትምህርት ቤት ማስተማር አልቻለም፡፡ የገነነ ሙያው ያመጣውን የጥቅም በረከት ለመቁጠር አልታደለም፡፡ ያልረባ ስራን ጭምር መሸሻና አማራጭ አድርጎ ይዞታል፡፡ ያ ምዕራፍ እንዲህ ባሉ ራዕዮች እልባት ካላገኘ ነገ ያለንን ነበረን የምንልበት ችግር አፍጥጦ ይመጣል፡፡

ከጥበበኛው ጥቅም፣ ከገበያ ትስስሩ፣ ከምርት ጥራትና ሳይንሳዊ ከሆነ አቅርቦቱ ጋር አብሮ የሚቆም፣ አብሮ የሚጠቀም ራዕይ ያስፈልጋል፡፡ ሸማ ፓርክ ብዙ ወጥኗል፡፡ መነሻው ቁጭት ነው፡፡ ሽመናን ጥሎ ባለ ኮሌጅ ሆኖ የጣለውን ሊያነሳ የመጣ ባለ ራዕይ ቁጭት ስለሆነ ጅምሩ ብዙ የተጓዘ አስመስሎታል፡፡

ተቋማት ወደ ሸማ ፓርክ ጎራ ብለዋል፡፡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከፓርኩ ጋር በፈጠሩት ቤተሰባዊ የገበያ ትስስር ገና በሙሉ አቅሙ ስራ ላይ ያልገባውን የጥበብ ማዕከል ተስፋ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ በቅርቡ ይሄንን መሰል ፓርክ እንደሚኖራት የሥራ ሃላፊዎቹ ገልጸውልኛል፡፡ እናም እንደ ሸማ ፓርክ መሪዎች ገለጻ ከዚህ በኋላ በሸማኔ ላብ ቀልድ የለም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top