Connect with us

ሐምሌ 5 የፌዴራሊዝሟ ጠበቃ ነኝ ባይ ትህነግ ጎንደርን ለማስገበር ገብታ ኢትዮጵያን ያጣችበት ቀን 

ሐምሌ 5 የፌዴራሊዝሟ ጠበቃ ነኝ ባይ ትህነግ ጎንደርን ለማስገበር ገብታ ኢትዮጵያን ያጣችበት ቀን
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሐምሌ 5 የፌዴራሊዝሟ ጠበቃ ነኝ ባይ ትህነግ ጎንደርን ለማስገበር ገብታ ኢትዮጵያን ያጣችበት ቀን 

ሐምሌ 5 የፌዴራሊዝሟ ጠበቃ ነኝ ባይ ትህነግ ጎንደርን ለማስገበር ገብታ ኢትዮጵያን ያጣችበት ቀን 

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)

ሐምሌ አምስት ትህነግ በአማራ ክልል የመጨረሻው የመሰናበቻ ፊሽካዋ የተነፋበት ቀን ነበር፡፡ ቀኑ ዛሬ በጎንደር ድርብ በዓል ሆኖ ይከበራል፡፡ የወልቃይት የማንነት ኮሚቴን ከምድሩ አሳድዳ፣ ዘር ማጥፋት ፈጽማ ጎንደር ድረስ ገብታ ልትገድል የወጠነችው ደባ ከአሳደገችው ከብአዴን ጋር ጭምር ለዘለዓለም ያለያያት ጉዳይ ሆነ፡፡

ዛሬ ግማሹ የገባበት የማይታወቅ፣ ግማሹ ወህኒ የሚማቅቅ ግማሹ ተሸማቆ አንገት የደፋ የብአዴን ካድሬ ትናንት ኮለኔሉን አሳልፈን አንሰጥም ያሉትን ጀግና አመራሮች ቁም ስቅል አሳይቶ ነበር፡፡ አሰላለፉን መቀሌ ያደረገው አድርባይና ሆዳም የብአዴን አመራር የትህነግ ሰራዊት ጎንደርን እንዲያፈርስ ፈቅዶም ነበር፡፡

ክልሉን ይመሩ የነበሩት አቶ ገዱና ጓዶቻቸው እንዲሁም አቶ ደመቀ መኮንን በቃ አሉ፡፡ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ቆራጡ አቶ ተቀባ ተባባልም እንቢኝ አለ፡፡ ሐምሌ አምስት ጎንደር ከዳር ዳር እሳቱን ለኮሰችው፡፡

መንግስታዊ ሽፋን የነበረው ሃይል ብቃት አለኝ ብሎ ቢገባም ከጎንደር የወጣው ሬሳው ነበር፡፡ ያ አብዮት ድፍን አማራን ከዳር ዳር አቀጣጠለ፡፡ የኮለኔሉን ክንድ የማበርከክ ሙከራ የኦሮሞው ደም የኔ ነው የሚሉ የጎንደር ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ስሜታቸውን እንዲገልጹ እድል ፈጠረ፡፡ ታሪክ ሌላ ምዕራፍ ያዘ፡፡ በህወሃት ጥይት በገዛ ምድራቸው የረገፉት የባህር ዳር ሰማዕታት ሞታቸው ሀገር አፈራ፡፡ አምባገነነት ተገረሰሰ፡፡

ትህነግ የፌዴራሊዝም ጠበቃ ነኝ ትበል እንጂ የፈለገችው ክልል ገብታ የፈለገችውን ስታደርግ የኖረች የኢትዮጵያ ነቀርሳ ነበረች፡፡ አማር በተባበረ ክንድ ሐምሌ አምስት በለኮሰው መራር ትግል ድል አደረጋት፡፡ ተቀበረች፡፡

የአማራና የትግራይን ህዝብ አንድነትና አብሮነት በምዘርፈው መሬት፣ በምገድለው ንጹህ ነፍስ ዝምታ ላይ ካልተመሰረተ በሚል ብዙ ዜጎች ለመከራ ለስቃይና ለስደት እንዲበቁ ተደረገ፡፡

ትህነግ እስክትፈርስ አላረፈችም፡፡ የተጋባውንና የተዋለደውን አንድ ህዝብ ሁለት ቦታ ለመክፈል ጥቂት ቅጥረኞችን ገዝታ ቅማንት አማራ በሚል ድራማ አጫረሰች፡፡ በኦሮሚያ፣ በሱማሌ፣ በደቡብ ብቻ የሐምሌ አምስት ኪሳራዋን ለማወራረድ ድፍን ኢትዮጵያን አመሰችው፡፡ ሁሉም አልፎ ዛሬ ሌላ ቀን መጣ፡፡

ጎንደር የኮሎኔል ደመቅን ቤት ሙዚየም አድርጋዋለች፡፡ ሐምሌ አምስትን ሲዘክር የሚኖረው ሙዚየም መሬቱን ተነጥቆ ለምን ያለን ህዝብ አሳድዶ መጨረስ እንደማይቻል ማሳያ ሆኖ የሚኖር ቅርስ ነው፡፡ የተደራጀው ከመቀሌ የመጣ ሸማቂ በአንድ ጀግና ኮሌኔል ጥይት ተለቅሞ ድራሹ ጠፋ፡፡ ትህነግም የምትጠፋበት ምዕራፍ ገዝፎ አንድ ብሎ ጀመረ፡፡

ሐምሌ አምስት ጎንደር በቃኝ ብላ አማራ ከዳር ዳር እንቢኝ ያለበት አብዮት ቀን ነው፡፡ በዚያ ከባድ ወቅት መንግስትም መሳሪያም ገንዘብም ለያዘው ሽፍታ ያልተንበረከኩት ጀግኖች ህያው የሀገር ባለውለታዎች ናቸው፡፡ ነጻ ወጥተው የነጻነትን ምልክት አስተጋብተዋል፡፡

ዛሬ ጎንደር ሐምሌ አምስትን የምታከብረው በሌላ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ሆና ነው፡፡ ከተማዋን የሚረብሸው አማጺ የራሱን ከተማ አፍርሶ የእኔ ያለውን ህዝብ ለመከራ ዳርጎ የተመካበትን ሁሉ አጥቶ ዳግም አማጺ የሆነበት ሌላ ታሪክ ተከስቷል፡፡ ከታሪክ ካልተማርን ታሪክ ምንም አይጠቅምም፡፡ ዘለዓለማዊ ክብር በመላ ኢትዮጵያ ጭቆናን እንቢኝ ብለው ሰማዕት ለሆኑ ኢትዮጵያውያን 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top