Connect with us

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚሰራ ገለጸ

በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ኢኮኖሚ

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚሰራ ገለጸ

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚሰራ ገለጸ
~ ተቋሙ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቢሾፍቱ የምክክር መድረክ አካሂዷል
(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዘርፎች በማሻሻል እና በማስፋፋት ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ እድል ለመፍጠር እና በድርጅቱ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንደሚሰራ አስታወቀ ፡፡
ከኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር እየሰጣቸው ባሉ የአገልግሎት መስኮች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትላንትናው ዕለት በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
የድርጅቱ ዳይሬክተር ጀነራል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ በምክክር መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ እና ተቋማዊ አቋሙንም እያሳደገ የመጣ ድርጂት ነው ብለዋል፡፡
ድርጅቱ የተቋቋመበትን የንግድ ዓላማ ለማሳካት 13 የሚጠጉ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ በማሰማራት ከንግድ ባንክ እና ከአምስት ከሚበልጡ የግል ባንኮች፣ ከኢትዮጰያ ጂቡቲ ምድር ባቡር ፣ከኢትዮጰያ መንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም ከበርካታ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡
ድርጅቱ በጋራ ከሚሰራቸው በነዚህም ተቋማት ውስጥም ከ 35 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩንም ዳይሬክተረ ጀነራሉ አስረድተዋል፡፡
ድርጅቱ በቀጣይም አሁን እየሰጣችው ካሉ 13 የአገልግሎት ዘርፎች በተጨማሪ አዳዲስ የስራ መስኮች በመፍጠርና ያሉትንም በማሻሻል ለዜጎች ተጨማሪ የስራ አድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ኮማንደር ጥላሁን ገልጸዋል ፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ የሚነሱ ክፍተቶችን ለማረም ፣ያሉንን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ ለማጎልበት እንድንስራ ከተሳታፊው ግብአቶች እናገኛለን ብለን እናምናለን ሲሉ ዳይሬክተር ጀነራሉ ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ተናግረዋል ።
በምክክር መድረኩ ላይ ለዉይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የድርጅቱ ቢዝነስ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ገብረ ሕይወት ጌታሁን የኮሜርሻል ኖሚኒስ ከምስረታው እስከ አሁን ባለው ሂደት ያሳለፉቸውን ውጣ ውረዶች ለተሳታፊዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
የቀረበውን የውይይት መነሻ ሐሳብ ተከትሎ ተሳታፊዎቹ በርከታ ሐሳብና አስተያየቶችን ጨምሮ ሊሻሻሉ ይገባል ያላቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁን እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ የሚሰጣቸወን አገልግሎቶችና ያለበትን አደረጃጀት በግልጽ ባለማሳወቁ ምክንያት እኔን ጨምሮ በርካቶችን ስለ ድርጅቱ የግንዛቤ እጥረት እንዲኖራቸው አድርጓል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ድርጅቱ ራሱን በሚገባ በማስተዋወቅና አሰራሩን በማዘመን ሊሰራ ይገባዋል ያሉት ሰብሳቢዋ፤ እየሰጣቸው ያሉ የአገልግሎት ዘርፎች ለመሰል ተቋማት አርአያ ሊሆኑ ስለሚገባቸወ ልምዱን ለሌሎች ማካፍል ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ከሚርሻል ኖሚኒስ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ በመምጣቱ ሊመሰገን ይገባል ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማኀበራት ኮን ፌዴሬሽን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ድሪብሳ ለገሰ ናቸው፡፡
ኃላፊው እነደገለጹት፤ ድርጅቱ በኛ በኩል የተሰጠውን የሰራተኞች መብት አጠባበቅና አያያዝ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየፈታ መሆኑን ከድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት መገንዘባቸውን ጠቁመው፤ ኮሜረሻል ኖሚኒስን ከሌሎች አጀንሲዎች ጋር ደምሮ መፈረጅ አግባብ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሰራተኞች ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ካሳ ስዩም በበኩላቸው፤ ከሜርሻል ኖሚኒስን በቅርበት እንደምናውቀው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠሩና ማኀበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ በመወጣቱ ነው ብለዋል፡፡
ከሰራተኞቹ የሚነሱበትንም አንዳንድ ቅሬታዎች እየፈታ እንደሚገኝ እየተከታተልን ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ለውይይት ያቀረበውን የአሠራር ሂደቱን የሚያመለክተውን ሰነድ መሬት ላይ እየተሰራበት ስለመሆኑ ለሌሎች ማሳየት ይገባዋል ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ሰራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሰብሩ በበኩላቸው፤ በድርጅቱ ላይ በከልሉ ከዚህ በፊት የሚነሱ ቅሬታዎች አሁን ላይ እየተፈቱ እንደሚገኙ ተናግረው፤ አሁን በክልሉ ከኮሜርሻል ኖሚኒስ ጋር በመግባባት እየሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
የአማራ ክልል ሰራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጀ አበጀ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ ኮሜርሻል ኖሚኒስ በርከታ ሰራተኞች ቀጥሮ እያስተዳደረ እንደሚገኝ ገልጸው፤ አሰራሩም ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡
ይሁን እንጂ ድርጅቱ በክልሉ ያለው ተደራሽነት ውስን በመሆኑና በሽፍት ኃላፊዎች በኩል በሰራተኞች ላይ ይደርሳሉ ያሉትን አንዳንድ ችግሮች ጠቁመው፤ በሰራተኞችና በአሰሪዎች የሚነሱ አለመግባባቶችን በኅብረት ስምምነት መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ኮሜርሻል ኖሚኒስ አሰራሩን እያሻሻለ ቢመጣም ራሱን በሚገባ ባለማስተዋወቁ ለተሳሳተ ግምት እንዳጋለጠ ገልጸው፤ ከሰራተኞች የሚነሱበትን የጥቅማጥቅምና መብት አጠባበቅ ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡
ከተሳታፊዎች ለተነሱት አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የኮሜርሻል ኖሚኒስ ዳይሬክተር ጀነራል ኮማነደር ጥላሁን ፀጋዬ፤ ድርጅታቸው ከሰራተኞች የሚነሱበትን ጥያቄዎች ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ አንዳንዶቹንም ጥያቄዎች መፍታት መጀመራቸውን፤ አንዳንዶቹንም ለመፍታት በሂደት ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
የሀገር ውስጥ የሰው ሃይል አቅርቦትና አስተዳደር ሥራው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ከሚሰራቸው 13 የሚጠጉ ሥራዎች አንዱ ዘርፍ ብቻ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተር ጀነራሉ፤ በዚህም ሥራ ላይ ለሚቀጥሯቸው ሰራተኞች ከመሰል ኤጀንሲዎች የተሻለ ክፍያና ጥቅማጥቅም ኮሜርሻል ኖሚኒስ እንደሚሰጥ አስረድተዋል፡፡
ከተሳታፊዎች የተሰጡት አስተያየቶችን ሙሉ ለሙሉ መቀበላቸውን የተናገሩተ ኮማንደር ጥላሁን፤ የተነሱትንም ገንቢ ሐሳቦች ድርጅቱን ለማጠናከር በግብዓትነት እንደሚወሰዱትና ይሻሻሉ የተባሉትንም ነጥቦች ለማሻሻል እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴን ጨምሮ፤ ከፌዴራል ሰራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ፣ ከኦሮሚያና አመራ ክልል ሰራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፣ ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስና ኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ከኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን እና ፌዴሬሽን ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲና ከተቋሙ አገልግሎት ተቀባዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top