Connect with us

የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው

የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

ዜና

የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው

የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የሚያካሄደውን ስብሰባ በመቃወም በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በኒው ዮርክ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ ግብጽ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ስብሰባ ያደርጋል።

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተገኝተው የጸጥታው ምክር ቤት በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያደርገውን ስብሰባ ይቃወማሉ።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ስብሰባውን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የሰላምና አንድነት ግብረ ሃይል ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ጣሰው መልዐከ ሕይወት ለኢዜአ ገልጸዋል።

“የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የሕልውና ጉዳይ ነው። ግድቡን አስመልክቶ የአረብ ሊግና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የለውም” ይህንንም እንቃወማለን ብለዋል አስተባባሪው።

የሶስትዮሽ ውይይቱ በአፍሪካ ሕብረት አዳራዳሪነት መቀጠልና መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ተናግረዋል።

ከዚህም አኳያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በግድቡ ዙሪያ የሚያደርገው ስብሰባ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ዳያስፖራዎች ስብሰባውን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያከናውኑ አመልክተዋል።

የሰልፈኞቹ ተወካዮች በስብሰባው ላይ ለሚሳተፉ ዲፕሎማቶችና በተመድ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች የተቃውሞውን መልዕክቶች የሚገልጽ ደብዳቤ እንደሚያስገቡና በራሪ ወረቀቶችን እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በኒው ዮርክ፣ ኒው ጀርሲ፣ ቦስተን፣ ኮኔቲከት፣ ቨርጂኒያ፣ ዴልዌር፣ ፔንሲልቫኒያ ፣ ዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድና በሌሎች አካበቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየደረሰባት ያለውን ጫና በመቃወምና በመመከት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ለአገሩ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝና የሐሙሱ ሰልፍም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

የተቃውሞ ሰልፉ በአሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር 1:00 pm ወይም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንደሚጀመር ጠቁመዋል።

ሰልፉን በዋሺንግተን ዲሲ የሰላምና አንድነት ግብረ ሃይል ኢትዮጵያ፣ በኒው ዮርክ ከተማ የሚገኘው ተስፋ በኢትዮጵያ ቡድን አባላትና ሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዳስተባበሩት አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተግባር ምክር ቤት ጊዜያዊ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አለማየሁ ስለሺ ÷ በአሜሪካ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የፊታችን ሐሙስ በሚካሄደው ሰልፍ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዳያስፖራው በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በገንዘብ፣ በጉልበትና በእውቀት የሚያደርገውን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላልም ብለዋል።(FBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top