Connect with us

“መንግሥትን መዋጋቴን እቀጥላለሁ ግን ነዳጅና ብር አጥሮኛል” አለ አሉ፤ ሞልቃቃው አማጺ!!

"መንግሥትን መዋጋቴን እቀጥላለሁ ግን ነዳጅና ብር አጥሮኛል" አለ አሉ፤ ሞልቃቃው አማጺ!!

ነፃ ሃሳብ

“መንግሥትን መዋጋቴን እቀጥላለሁ ግን ነዳጅና ብር አጥሮኛል” አለ አሉ፤ ሞልቃቃው አማጺ!!

“መንግሥትን መዋጋቴን እቀጥላለሁ ግን ነዳጅና ብር አጥሮኛል” አለ አሉ፤ ሞልቃቃው አማጺ!!
(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
የትህነግ ዋናው ከባዱና ሲያስቸግረን የኖረው አመል አይን አውጣነቷ ነው፡፡ እፍረት የሚባል ነገር ለሰው የተሰጠ ጠባይ የላትም፡፡ ትግራይን ለመገንጠል እየተሞከረ ነው ብላ ስትከስ ትግራይን ለመገንጠል በርሃ መግባቷን፤ በህገ መንግስቷ መገንጠል ክብር ያለው ዓላማ አድርጋ መጻፏን ትረሳለች፡፡
ሰሞኑን የአንድ ወገን ተኩስ አቁሙ ዓለም ፊት ነጻ አውጪ ነኝ ባዩ ቡድን እንዴት ያለ አጥፊ እንደሆነ በአጭር ቀን ሲያጋልጠው የሚገባበት አጥቷል፡፡ ትህነግ በታሪኳ እውነት ተናግራ ባታውቅም ተራራና መሬት ዘራፊ፤ ሀገር በታኝ ብትሆንም የሚበልጠው ነውሯ ግን አይን አውጣነት ነው፡፡
ገና ትግራይ ሙሉ ለሙሉ በእጄ ነው ብላ ብልጽግና ላይ በምታሾፍበት ዘመን እኮ በትግራይ የህወሃት ሰው ሴት ደፍሮ ጨረሰ ተብሎ ሰልፍ ተደርጓል፡፡ ዛሬ በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች ሊሳበብ የተሞከረው ደፈራ እነሱ ወጥተውም ቀጥሏል፡፡ የመግደል ዜናም እየሰማን ነው፡፡
የትህነጉ ቃል አቀባይ ሰሞኑን የኢትዮጵያን መንግስት መዋጋት እንደሚቀጥሉና ተኩስ አቁም የሚለው ቀልድ እንደሆነ ገልጸውልናል፡፡ መልሰው ደግሞ ትግራይ ከቦ ማስራብ የሚል ድራማ ጀምረዋል፡፡
ነዳጅና የብር እጥረት ገጠመኝ የምትለው ትህነግ ኢትዮጵያን ለመውጋት የስንቅና ትጥቅ አቅርቦት ስላነሰብኝ ኢትዮጵያ ታሟላልኝ አይነት አይን ያወጣ ጥያቄ ይዛ አደባባይ ወጥታለች፡፡ እዚሁ ፌስ ቡክ መንደር ጋዜጠኛ ደረጃ ሀብተወልድ ለዚህ የትህነግ ጠባይ ጥሩ ስም ሰጥቷታል፡፡ ሞልቃቃዋ ነጻ አውጪ፤
ሞልቃቃዋ ነጻ አውጪ ኢትዮጵያ እየረዳቻት፣ ኢትዮጵያ እየደገፈቻት ኢትዮጵያን መውጋት የምትፈልግ ደፋር ናት፡፡
ጌታቸው ረዳ ዛሬም ከሚወጋት ሀገር እራትና መብራት ይፈልጋል፡፡ ዛሬም የኢትዮጵያን መሰረተ ልማት አውድሙ ብሎ ላቀረበው ጥሪ ጉንጩን የምትስመው ኢትዮጵያን ይናፍቃል፡፡ እንዲህ አይነት ሞልቃቃ ነጻ አውጪ ምናልባት የክፍለ ዘመን ክስተት ሳይሆን አይቀርም፡፡
በኢንተርኔት ሊያምሳት የፈለጋት ኢትዮጵያ ኔት ወርክ እንድታሟላለት የሚሻ ነጻ አውጪ ከድፍረት ያለፈ አይን አውጣነት የተሞላ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል?
አስተዳድረዋለሁ ያለውን ክልል ሃያ አራት ሰዓት ሰላም ማሳደር ያልቻለ ነጻ አውጪ ቀለብ ስፈሩልኝና እየተዋጋን እንቀጥል ሲል ከመስማት በላይስ ምን ቀልድ አለ፡፡
የትህነግ ስህተት የአሁኑ ይባስ እየተባለ እዚህ የደረሰ ነው፡፡ አንዱ ሲገርመን የሚቀጥለው ነውርና ስህተት ከቀድሞ የባሰ እንደሆነ እያየን መጥተናል፡፡ ዓለም ያላየው ወይም እያየ እንዳላየ የቆጠረው ነውር አሁን ገሃድ ወጥቷል፡፡
ኢትዮጵያን አመድ አደርጋታለሁ ያለ ዱቄት ቡድን ቀሪ እድሉን ለመጠቀም ግን እንደ ወራሪ አይቶ ምድሬን ይልቀቅልኝ ያለው መንግስት ድጋፍና እርዳታ መፈለጉ ያስቃል፡፡
በትግራይ ጉዳይ ዘለዓለማዊ ሀጢአቱን የሚወስደው ዘርፌ ካልበላሁ ድፍን ትግራዋይ ረሃብ ይለቅ ብሎ ዋሻ የገባው ዘራፊ ቡድን ነው፡፡ አመሉ እንደማይለቀው አይተናል፡፡ አለም አቀፍ ተቋም ሳይቀር ሲመሩ የሚጠረጠሩት በሌብነት ነው፡፡
ትህነግ ብሎ እምነት የለም፡፡ የህወሃት መሪዎች ባሉበት ቦታ ጥርጣሬና የዘረፋ ዜና እንደሚሰማ ከወደ አለም ጤና ድርጅት ያደመጥነው መረጃ ብቻ በቂ ነው፡፡
ግን እንዳንተዛዘብ፤ ቢያንስ ሳይሞላቀቁ ማመጽን ተማሩ እንጂ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top