Connect with us

በሰዎች የመነገድ ወንጀል የፈጸመው ኪዳኔ ዘካሪያስ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

በሰዎች የመነገድ ወንጀል የፈጸመው ኪዳኔ ዘካሪያስ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ
ፌ/ጠ/ዐቃቤ ህግ

ዜና

በሰዎች የመነገድ ወንጀል የፈጸመው ኪዳኔ ዘካሪያስ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

በሰዎች የመነገድ ወንጀል የፈጸመው ኪዳኔ ዘካሪያስ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

ተከሳሽ ኪዳኔ ዘካሪያስ በአጠቃላይ በ8 ክሶች ተከስሶ የነበረ ሲሆን ክስ 1 እና ክስ 2 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ስደተኞችን በህገ-ወጥ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 909 (አሁን በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 የተተካው) አንቀጽ 3/1/ሐ፣ 3/2/ሐ እና 6 ስር ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን ከክስ 3-8 ባለው ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 909 አንቀጽ 3/1/ እና 3/2/ሐ ተከሶ ጥፋተኛ ሊባል ችሏል፡፡

የክስ 1 እና 2 ክስ ላይ ዐቃቤ ሕግ ባሰፈረው ዝርዝር ተከሳሹ ኑሯቸውን ለመቀየር ከኢትዮጵያ ተነስተው በሱዳን በኩል አቋርጠው ሊቢያ ቢንወለድ በሚባል ቦታ ደርሰው የነበሩትን ሟች ዳንኤል ጥላሁን እና ሟች መሀመድ አለሙ በጦር መሳሪያ ታግዞ በማገት እኔ ገዝቻችኋለሁ እያንዳንዳችሁ 5 ሺ 500 ዶላር ካልከፈላችሁ እዚሁ ትሞታላችሁ በማለት እጅና እግራቸውን በገመድ በማሰር በኤሌክትሪክ ገመድ በመግረፍና በማስገረፍ፣ ላስቲክ በእሳት አቅልጦ በሰውነታቸው ላይ በማንጠባጠብ፤ በመያዣነት በመያዝ ከሟች መሀመድ አለሙ ቤተሰቦች በፌቨን ከበደ ስም 155,000 ብር ገቢ ያስደረገ ሲሆን በአባሪው በ2ኛ ተከሳሽ አካውንት ላይ ደግሞ ብር 30 ሺ  ገቢ እንዲደረግለት አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ ከሟች ዳንኤል ጥላሁን ቤተቦችም 187 ሺ ብር በ1ኛ ተከሳሽ አካውንት ገቢ አድርገዋል፡፡

ሆኖም ሟቾች በደረሰባቸው ድብደባ፣ እንግልት፣ ያለ በቂ ምግብና ውሃ፣ ንጽህናቸው ባልተጠበቁ ቦታዎች ተይዘው በመቆየታቸው ለቲቪ እና አካኪ ለተባለ የቆዳ በሽታ በመጋለጣቸው በ2011 ዓ.ም ሁለቱም ሟቾች ህይወታቸው አልፏል፡፡

ከ3ኛ-8ኛ የቀረቡት ክሶች ዝርዝርን ስንመለከለት ቁጥራቸው ስድስት የሚሆኑ የግል ተበዳዮች በ2009 ዓ.ም ኑሯቸውን ለመቀየር ከሚኖሩበት ኢትዮጵያ በመነሳት በደላላዎች በመታገዝ ሱዳን ካርቱም ከገቡ በኋላ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ደላላዎች ተጭነው ለ1ኛ ተከሳሽ ተላልፈው የተሰጡ ሲሆን ተከሳሽም በጦር መሳሪያ ታግዞ በማገት 1ኛ እና 2ኛ ክስ ላይ ከሰፈረው ጋር ተመሳሳይ በሆነ ንግግር “ገዝቻችኋለሁ እያንዳንዳችሁ 5 ሺ 500 ዶላር ክፈሉ ካልከፈላችሁ እዚሁ ትሞታላችሁ“ በማለት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እንዲመገቡ፣ ኳርትሽ በተባለ መግረፊያ ጧት እና ማታ በመግረፍ እና በማስገረፍ፣ በሰውነታቸው ላይ ውሃ በማርከፍከፍ፣ የተበዳዮችን የስቃይ ድምጽ ለቤተሰብ በማሰማት በአጠቃላይ ከ1 ሚልየን 155 ሺ ብር በላይ የገንዘብ ጥቅም አግኝቷል፡፡

የ2ኛ ተከሳሽን ክስ በተመለከተ በአንድ ክስ በወንጀል ህግ አንቀጽ 37/1/ እና አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 3/1/ እና 6 ስር ክስ ቀርቦባታል፡፡ ተከሳሽም በግል ተበደዮች ዳንኤል ያኖ እና መሀመድ አለሙ/ሟች/ ቤተሰቦች አማካኝነት የገባውን 230 ሺ ብር ወደ አካውንቷ እንዲገባ አድርጋለች፡፡

በስተመጨረሻም በተከናወነው የወንጀል ምርመራ ስራ የተሰበሰቡትን ማስረጃ መሰረት አድርጎ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ለሁለቱ ተከሳሾች እንዲደርስ ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን አልፈጸምንም ብለው ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ ካሰማ በኋላ በበቂ ሁኔታ በማስረዳቱ ተከላከሉ ተብለዋል፡፡

ነገር ግን 1ኛ/ ተከሳሽ ከዛሬ ነገ መከላከያ ምስክሮቼን አቀርባለሁ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው በማድረግ እና ክርክሩን በማዘግየት በመሃል ከእስር ያመለጠ ሲሆን ዐቃቤ ህግም ተከሳሽ በሌለበት ፍርድ እንዲሰጥ አሳስቦ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን አስተያየት ተቀብሎ ተከሳሽን በተከሰሰበት የወንጀል ድንጋጌዎች ስር ጥፋተኛ ብሎታል ወስኖበታል፡፡

2ኛ/ ተከሳሽ በበኩሏ አምስት መከላከያ ምስክሮች አቅርባ ያሰማች ቢሆንም የዐቃቤ ህግን ክስና ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሏ ጥፋተኛ ተብላለች፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ፡-

1ኛ ተከሳሽን በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እና በ1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ እንዲሁም

2ኛ ተከሳሽን ደግሞ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እና 75 ሺ ብር እንድትቀጣ ወስኗል፡፡(የፌ/ጠ/ዐቃቤ ህግ)

 

Click to comment

More in ዜና

To Top