Connect with us

የአውሮፓ ህብረት ምሳሌ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ውህደት…. 

የአውሮፓ ህብረት ምሳሌ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ውህደት….
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የአውሮፓ ህብረት ምሳሌ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ውህደት…. 

የአውሮፓ ህብረት ምሳሌ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ውህደት…. 

  (  እስክንድር ከበደ ~ ድሬቲዩብ)  

የአውሮፓ ህብረት በጦርነት ባደቀቀውና የተከፋፈለውን አህጉር ሰላምን ለማስፈን በተደረገ ጥረት የተፈጠረ ህብረት መሆኑ ይነገራል፡፡የሁለተኛው የአለም ጦርነት ካበቃ አምስት አመታት በኃላ ጀርመንና ፈረንሳይ በመቀራረብ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን ጦርነት ለማስቀረት ውጥን ያዙ፡፡ 

ውጤቱም ስድስት ሀገራት እ.አ.አ በ1950 ዓ.ም የድንጋይ ከሰል ና ብረት የተፈጥሮ ሀብቶቻቸውን በጋራ ለመጠቀም ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

 የአውሮፓ የዲንጋይ ከሰል ና ብረት ማህበረሰብ (European Coal and Steel Community- ECSC) ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ እ.አ.አ በ1951 ዓ.ም የፓሪስ ስምምነት በፈረሙ ሀገራት ማለትም ቤልጂየም ፣ምዕራብ ጀርመን ፣ጣሊያን ፣ኔዘርላንድ እና ሉክሰንበርግ የተመሰረተ ነበር፡፡ ይህ ማህበረሰብ የአውሮፓ ህብረትን የፈጠረ ስብስብ ነው፡፡ 

ሃሳቡ የተነሳው ከፈረንሳይ ሲሆን ፤ በ1950 ዓ.ም የፈረንሳይ የቀድሞ ውጭ ጉዳይና ጠቅላይ ሚንስተር ሮበርት ሹማን በወቅቱ በፈረንሳይና ጀርመን መካከል የነበረውን ጦርነት ለመከላከል ህብረቱን መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው ነበር፡፡ “ጦርነትን የማይታሰብ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በእጅጉ የማይቻል ያደርገዋል…” ብለው ሃሳቡን ይዘው ብቅ አሉ፡፡

ፈረንሳይና ጀርመን ይዋጉባቸው የነበሩትን በተፈጥሮ የበለጸጉ ቦታዎች በጋራ መጠቀም የሚያስችል ስምምነት በመፍጠር ረገድ አዲሱ ብልሃት ወሳኝ መፍትሄ እንደሆናቸው ይነገራል፡፡  

በአውሮፓ ሀገራት መካካል በየጊዜው የሚፈጠርን ጦርነት በዘላቂነት ለማስቀረት በቅድሚያ ታሪካዊ ጠላት ሀገራት ፈረንሳይና ጀርመን መስማማት ነበረባቸው፡፡በተለይ ለጦር መሳሪያዎች መስሪያነት የሚያገለግሉትን የዲንጋይ ከስልና ብረት የተፈጥሮ ሃብቶች መጋራት ወሳኝ ነበር። 

የአውሮፓ የዲንጋይ ከሰልና ብረት ህብረት በአውሮፓ ሀገራት መካከል የዲንጋይ ከሰል ና ብረት የተፈጥሮ ሀብቶችን በተመለከተ የጋራ ገበያ ለመፍጠርና በዘርፉ የገበያ ውድድርን ለማለዘብ ታስቦ መፈጠሩ ይነገራል፡፡ 

የዲንጋይና ከሰል ብረት ለጦር መሳሪያ ለማምረት ዋነኛ ጠቃሚ ግባቶች በመሆናቸው በዚህ ዙሪያ የተደረገው የፓሪሱ ስምምነት በአውሮፓ ሀገራት አህጉራዊ ኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር ጦርነትን ለማስቀረት ብርቱ ፋይዳ ነበረው፡፡  

የአውሮፓ የዲንጋይ ከስል ና ብረት ህብረት ከተመሳሳይ ህብረቶቹ ማለትም የአውሮፓ ምጣኔ ሀብት ህብረት(European Economic Community) ና የአውሮፓ አቶሚክ ሃይል ህብረት( European Atomic Energy Community) እ.አ.አ በ1957 ዓ.ም ጋር ተቀላቅሎ መስራት ጀመረ፡፡እ.አ.አ 1967 ከአውሮፓ ምጣኔ ሀብት ህብረት ጋር በመዋህድ ሲሰራ ከቆየ በኃላ የፓሪሱ ስምምነት ማብቃቱን ተከትሎ እ.አ.አ 2002 ዓ .ም ንብረቶቹ ሁሉ ወደ አውሮፓ ማህበረሰብ እንዲዛወሩ ሆነ፡፡ 

የአውሮፓ ህብረት በአለም የንግድ ድርጅት አባል ሀገራትን ወክሎ የሚሰራ ነው፡፡ የህብረቱ አባል ሀገራት የተጣራ ሀብት መጠናቸው አሜሪካን በሁለተኝነት የሚከተል ነው፡፡ ዩሮ በአለማችን ሁለተኛው የምንዛሬ ክምችት ያለውና ከአሜሪካው ዶላር ለጥቆ የአለም ሀገራት የሚጠቀሙበት ምንዛሬ ነው፡፡  

የአፍሪካ ቀንድ ከሱዳን እስከ ሶማሊያ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እስከ አሁኑ የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ቀውስ፣ የአሸባሪው አልሸባብ እንቅስቃሴ ፣ሄድ  መለስ የሚለው የሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች እንቅስቃሴ  በዚሁ የአፍሪካ ክፍል ነው። 

የአባል ሀገራቱ አልፎ አልፎ የሚታይ የጥርጣሬ ፖለቲካ እና  ለእጅ አዙር ጦርነቶች እና ግጭቶች መነሻ ሰበብ መፍጠር፤የድንበር ላይ ግጭቶች እና የደሴቶች እና የውሃማ አካባቢዎች የይገባኛል ጥያቄዎች እና እርኩቻዎች ለኢጋድ ፈተና እንደሆኑ ቀጥለዋል።  

ኢትዮጵያ  ጨምሮ አባል ሀገራቱ የተጠመዱት በቀጠናው የሚፈጠሩ ግጭቶች ማሸማገል ነው፡፡  የአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር  በኢትዮጵያ የሚገኙትን የመንግስት ልማት ድርጅቶችን ለውጭ ባለሀብቶች በዘፈቀደ ከመሸጥ፡ የጎረቤት ሀገራት መንግስታት የተወስነ ድርሻ እንዲገዙ ማደረግ ቢቀድም  ይጠቅማል፡፡ የጎረቤት ሀገራት የወደብ አገልግሎታቸውን  የጋራ  ገበያ   የሚጠቀሙበን  አካሄድ አጥንተው ቢተገብሩት ህዝቦቻቸው ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ ሀገራቱ ከመሰረተ ልማት ትስስሩ ጎን ለጎን በአየር ትራንስፖርት፣በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በባንክ ስርአትና የጋራ ገበያ መፍጠር እንዲሁም የጋራ ገንዘብ የሚጠቀሙበት ሁኔታዎችን አጥንተው ቢሰሩ  ለሀገራቱ  የጋራ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እድገት ብርቱ እገዛ ይኖረዋል፡፡ 

ከቻይና ይልቅ ጂቡቲ ፤ከአሜሪካ ኩባንያ ይልቅ ኤርትራ፤ ከቱርክ ይልቅ ለሱዳን ፤ሳኡዲ ይልቅ ደቡብ ሱዳን መንግስታት አንዱ ብሌላው ሀገር ድርሻ ቢኖራቸው የጋራ ትብብር ያጠናክራል፨ በአንድ ወቅት የአሰብ ነዳጅ ማጣሪያ የኤርትር ፔትሮሊም ኩባንያና የኢትዮጽያ መንግስት ባለድርሻ ሆነው ይሰሩ ነበር።አሁን ቀጠናው ብዙ የተማረበት ዘመን ነው። የጎረቤት ሀገራት መንግስታት የተመጠኑ ድርሻ በጋራ መስራት ከገንዘብ ይልቀ ኢኮኖሚያዊ፣የጋራ ደህንነት ማረጋገጥና የሰላም  ትርፉ ይበልጣል።  

ለአብነት ኢትዮቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ከምእራቡ አለም ማምጣት ይልቅ ከጎረቤት ሀገራት መንግስታት ጋር መስራት  ። ከጎረቤቶቻችን የምንገዛውም ፤የምንሸጥላቸውን በዙ ነገሮች አሉ። ይህውም የምንገዛው በዶላር የሚቆጠር ቁስ ሳይሆን ሰላምና መረጋጋት ብሎም የላቀ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይሆናል።

የአባል ሀገራቱ አልፎ አልፎ የሚታይ የጥርጣሬ ፖለቲካ እና  ለእጅ አዙር ጦርነቶች እና ግጭቶች መነሻ ሰበብ መፍጠር፤የድንበር ላይ ግጭቶች እና የደሴቶች እና የውሃማ አካባቢዎች የይገባኛል ጥያቄዎች እና መራኮቶች  የአፍሪካ ቀንድ ፈተናዎች እንደሆኑ ቀጥለዋል።  

የኢጋድ አብዛኛው የተጠመደበት ዋነኛ ስራ  በቀጠናው የሚፈጠሩ ግጭቶች ማሸማገል ነው፡፡  የአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር  በኢትዮጵያ የሚገኙትን የመንግስት ልማት ድርጅቶችን ለውጭ ባለሀብቶች በዘፈቀደ ከመሸጥ፡  የሀገር ውስጥ ባለሀብት የሚጠናከርበት ብሎም የጎረቤት ሀገራት መንግስታት የተወስነ ድርሻ እንዲገዙ ማደረግ ቢቀድም  ይጠቅማል፡፡ 

የጎረቤት ሀገራት የወደብ አገልግሎታቸውን  የጋራ  ገበያ   የሚጠቀሙበን  አካሄድ አጥንተው ቢተገብሩት ህዝቦቻቸው ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ ሀገራቱ ከመሰረተ ልማት ትስስሩ ጎን ለጎን በአየር ትራንስፖርት፣በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በባንክ ስርአትና የጋራ ገበያ መፍጠር እንዲሁም የጋራ ገንዘብ የሚጠቀሙበት ሁኔታዎችን አጥንተው ቢሰሩ  ለሀገራቱ  የጋራ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እድገት ብርቱ እገዛ ይኖረዋል፡፡ 

ከቻይና ይልቅ ጂቡቲ ከአሜሪካ ኩባንያ ይልቅ ኤርትራ ከቱርክ ይልቅ ሱዳን ሳኡዲ ይልቅ ደቡብ ሱዳን መንግስታት አንዱ ብሌላው ሀገር ድርሻ ቢኖራቸው የጋራ ትብብር ያጠናክራል፨ በአንድ ወቅት የአሰብ ነዳጅ ማጣሪያ የኤርትር ፔትሮሊም ኩባንያና የኢትዮጽያ መንግስት ባለድርሻ ሆነው ይሰሩ ነበር።አሁን ቀጠናው ብዙ የተማረበት ዘመን ነው። የጎረቤት ሀገራት መንግስታት የተመጠኑ ድርሻ በጋራ መስራት ከገንዘብ ይልቀ ኢኮኖሚያዊ ትርፉ ይበልጣል።  

ለአብነት ኢትዮቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ከምእራቡ አለም ማምጣት ይልቅ ከጎረቤት ሀገራት መንግስታት ጋር መስራት  ። ከጎረቤቶቻችን የምንገዛውም የምንሸጥላቸውን በዙ ነገሮች አሉ። ይህውም የምንገዛው በዶላር የሚቆጠር ቁስ ሳይሆን ሰላምና መረጋጋት ብሎም የላቀ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይሆናል።

 ከአህጉሩ ውጭ ለሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች ሀብትን በመቸብቸብ ዶላር ማግበስበስ ወይም የነጻ ገበያ አቀንቃኞችን ለማስደሰት የሚካሄድ የግብር ይውጣ ስራ እንዳይሆን፡፡ነባር የዘይት ፋብሪካዎች፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎችን፣ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎችና በርካታ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ወደ ግል በማዛወር ከተገኘው ትርፍ ይልቅ እነዛ አምራች ተቋማት ተንኮታኩተው የኑሮ ውድነት እንዲነግስ የተደረገበትን አካሄድ ወደ ኋላ በመቃኘት አዲስ አካሄድ መከተል ያስፈልጋል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top