Connect with us

ጎንደር ዛሬም መላቋን አሳየች፤ አማራ ክልሉን መምራት አቅቶታል ሊያስብል የተደገሰው ድግስም ከሽፏል

ጎንደር ዛሬም መላቋን አሳየች፤ አማራ ክልሉን መምራት አቅቶታል ሊያስብል የተደገሰው ድግስም ከሽፏል
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጎንደር ዛሬም መላቋን አሳየች፤ አማራ ክልሉን መምራት አቅቶታል ሊያስብል የተደገሰው ድግስም ከሽፏል

ጎንደር ዛሬም መላቋን አሳየች፤ አማራ ክልሉን መምራት አቅቶታል ሊያስብል የተደገሰው ድግስም ከሽፏል

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ ድሬቲዩብ)

ጎንደር ሀሳቧ ሁሌም ምጡቅ መሆኑን ዛሬም አሳይታለች፡፡ የጎንደር ሀሳቦች ድራማ እና ወቅት የሚዘውራቸው አለመሆናቸውን ዛሬ በሰልፉ ላይ ከታዩት መፈክሮች መረዳት ይቻላል፡፡ አንዲት ቃል ያወዛገበቻቸው ትርጉም ሰንጣቂዎች እንዲህ ከፍ ባለ ጎንደር በታየው አይነት የአማራ መንፈስ ስሜታቸው ይረበሻል፡፡ 

ለጥላቻ ንግግራቸው ጥላቻን መስማት ከሚሹት ጋር የፋሲል ከተማ ህብረት እንደሌላት አሳይታለች፡፡ የጎንደር ሰልፈኞች ከወንድማቸው የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻም ቂምም ነገርም እንደሌላቸው ዛሬም አረጋግጠዋል፡፡

የአማራ ክልል ከተሞች አማራ በማንነቱ ለምን ይሞታል ብለው ይበቃ በማለት የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ድምጽ አስተናግደዋል፡፡ ደብረ ብርሃን ሀዘን ለብሳ ሀዘኗን ገልጻለች፡፡ ጠንካራ አስተባባሪ ያላቸው ሰልፎች ከሰልፉ ማብቂያ ለአጣዬ ወገኖቻቸው ድጋፍ አሰባስበዋል፡፡

በባህር ዳር የተደገሰው ጥፋትም ከሽፏል፡፡ አማራ ብልጽግና ክልሉን እየመራ አይደለም፡፡ የአማራ ልዩ ሃይል ገዳይ ነው ለማስባል ከተማ አተራምሶ ሰላማዊውን ትግል መልኩን እንዲቀይር የተደገሰው ጥፋትም ከሽፏል፡፡

የትም እየተጎዳ ነው ለሚባለው አማራ አሁንም በክልሉ መንግስትና በህዝቡ መካከል መደማመጥ መመካከርና አብሮ መቆም እንጂ ልዩነትና ሰዶ ማሳደድ አይጠቅመውም፡፡ ዳሩም መሃሉም መተራመስ የለበትም፡፡ የአማራ ልዩ ሃይል ለክልሉም ሆነ ለሀገሩ ሰላም ብዙ ቦታ ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ በአማራ ክልል ከተሞች ቢያንስ ጸጥታውን ህዝቡ ራሱ ሊያግዘው ይገባል፡፡

የባህር ዳር ወጣቶች ሰላምን ቢፈልጉም የሚበጠብጣቸውን ግራና ቀኝ አይተው አጋልጠው ከተማቸውን ካልጠበቁ ዋጋ የለውም፡፡ ሰላም በመፈለግ ብቻ አትገኘም ሰላም እንዲሆን ከጸጥታው አካል ጋር አብሮ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ብልጽግናና ዛሬውኑ ካልጣልኩ የሚለው አጀንዳ ጀርባው ሌላ መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

የአማራ ብልጽግና አሁን ክልሉን የሚመራ የክልሉን ሃላፊነት የተሸከመ ነው፡፡ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ ሀገር የመምራት ሃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ ችግሩን አርሞ ቢያንስ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲወርድ ማድረግ እንጂ ከምርጫና ከሰላም ውጪ ብልጽግናን አልየው ማለት ሰላም አጣሁ ከሚል ሀሳብ ጋር የሚጋጭ ሌላ አጀንዳ ነው፡፡

ህዝባዊ ሰልፎች የሚመራቸው አካል ሊታወቅ ይገባል፡፡ መሪው የማይታወቅ ሰልፍ ለጠላት ሰርግ ነው፡፡ ከካይሮ እስከ ተከዜ በርሃ፣ ከወለጋ እስከ ከሚሴ ሀገር አተራምሶ ህዝብ ማጫረስ የፈለገ ሃይል እንዲህ ያለውን እድል ሰርጉ ሆኖለት ይጠቅምበታል፡፡

ያለ ሰላም ያለ መረጋጋትና የለመደማመጥ የሚመጣ ምንም ነገር የለም ህዝብን ሊጠቅም ስለሚችል ትግል የሚያስብ ወገን ህዝብን በሚጠል አጀንዳ እንዳይጠለፍ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሀገሩን የሚመራውም ሆነ ክልሉን የሚመራው መንግስት መንግስት ናቸው፡፡ ችግራቸውን እንዲያርሙ፣ ሀገር እንዲጠብቁ፣ ፍትህ እንዲያሰፍኑ በጥፋታቸው እንዲጠየቁ ማድረግ እንጂ አሁኑኑ አንያችሁ ማለት ለህዝብ የሚጠቅም መርህ አለኝ ከሚል ወገን አይጠበቅም፡፡

 ምናልባት የተጠለፈ አጀንዳም ካለ አንገትን አዙሮ ማየት ነው፡፡ መንግስትን አክብሮ መንግስትን መጠየቅ ካልተቻለ መንግስት የጠፋበት ቦታ ምን መልክ እንዳለው በሚሆነው ማየቱ መልካም ይመስለኛል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top