Connect with us

ሹመኛ ሁሉ- ቢሮህን  ክፈት፣ ወደ ህዝብ ውረድ !

ሹመኛ ሁሉ- ቢሮህን ክፈት፣ ወደ ህዝብ ውረድ !
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሹመኛ ሁሉ- ቢሮህን  ክፈት፣ ወደ ህዝብ ውረድ !

ሹመኛ ሁሉ- ቢሮህን  ክፈት፣ ወደ ህዝብ ውረድ !

(ንጉሥ ወዳጅነው~ ድሬቲዩብ)

 ወቅታዊ ፈተናዎቹ እንደተጠበቁ ሆነው ፣ከጅምሩ ሀገርዊ የውጥ ጉዞ ውስጥ አሁንም የተለያዩ ዝግመቶች እየተስተዋሉ ነዉ ፡፡ በየደረጃዉ ባለዉ የመንግስት መዋቅር ዉስጥ አሰራርና የህግ ማእቀፍ ወይም ዋናዋና መዋቅሮች ባይቀየሩም አብዛኛዉ አመራር በአዲስ ተተክቶ ነበር ፡፡ 

ቀላል የማይባሉ አዳዲስ ባለሙያዎችና ፈፃሚዎች በየመዋቅሩ መግባታቸዉ ብቻ ሳይሆን ፣ ነባሩ ሃይልም ቢሆን ከነችግሩ  በለዉጥ መንፈስ የግልፅነትና የተጠያቂነት መርህን እንዲተገብር በመደመርና በሀገር ተቆርቋሪነት መንፈስ ህዝብ እንዲያገለግል አደራ  ተሰጥቶታል ፡፡

ይሁንና ግን አሁንም ያልተሻሻሉና በተለይ በአመራር ደረጃ ያሉ ሰዎች ኋላቀር የአመራር ዘይቤዎች እንደቀጠሉ ናቸዉ ፡፡ ለዚህ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተዟዙሬ ያየኋቸዉ መስሪያ ቤቶች አስረጅ ናቸዉ ፡፡ በቀዳሚነት አሁንም ተደጋጋሚ የሰብሰባና ከመደበኛ ስራ የሚያስወጣ ተግባር እንደቀጠለ ነዉ ፡፡ በተለይ ጉባኤ፣ የምርጫ ስራ፣ ስልጠናና መሰል ተግባራት የስራ ሰዓት መብላታቸዉ አልተገታም ወይም ጋብ አላለም ፡፡ 

በየመዋቅሩ ከመርህ ውጭ መሳሳብና የህዝብን ቅር ማሰኘቱም አለ፡፡ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት በለውጡ ሰሞን እንደተባለው ሳይሆን፣ ቅንጡና ውድ ተሽከርካሪዎችን ከመጠቀም ፣ወጣገባ ከማለትና በር ዘግተው ከመቀመጥ አልወጡም ፡፡

 በተለያዩ መስሪያ ቤቶች አሁን ህዝብ የሚደመጥበት ሰፊ እድል ገና እየዳበረ አይደለም ፡፡ እውነት ለመናገር አንዳንዱ አካባቢ እንዳውም ወደኋላ መመለስ እየታየ ነው!! በአንድ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ መመላለስ ፣ በድርድርና ጥቅማጥቅም መፈፀም በዝቶ እንደሁ እንጂ አልቀነሰም።

በተለይ እንደመሬት ፣ገቢዎች፣ኢንቨስትመንት ፣መዐድን … የታየ ለውጥ አለ ማለት አይቻልም ፡፡ በርከት ያለው አመራር ደግሞ አሁንም ቢሮ ዘግቶ መቀመጥና አገልግሎት ፈላጊዉን ማጉላላት እንደወግና መእረግ ይዞ መቀጠሉ ችግሩን አባብሶታል ፡፡

አሁን ካለዉ ሀገራዊ ለውጥና መነቃቃት አንፃር ደግሞ እንደዜጋ ፤ በመካከላችን የሚገኝ አብሮን የሚበላ ፣ አብሮን የሚጠጣ በመከራና በደስታችን ጊዜ ከጎናችን የሚገኝ ‹‹ሰው-ሰው የሚሸት›› መሪ በየደረጃዉ እንፈልጋለን፡፡ እንደዜጋ እሱ ሲፈልገን ብቻ ሳይሆን እኛም ስንፈልገው የሚገኝልን አለቃና መሪ ብናገኝ አንጠላም ፡፡ አለመጥላት ብቻ ሳይሆን እዉን እንዲሆንም እንሻለን ፡፡

በእኔ እምነት አሁን በተጨባጭ የሚታየዉ ሁኔታ በኢህአዴግ 27 ዓመታት ከተለመደዉና ተንሰራፍቶ ከቆየዉ ብዙም የተለየ አይመስልም ፡፡ ዛሬም ቢሆን በየደረጃዉ አብዛኞቹ ሹመኞቻችን  ቢሮአቸውን ቆልፈው ፤ ስልካቸውን አጥፍተው እንደ ድመት አድፍጠው ‹‹ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ናቸው›› እያሰኙ የሚደበቁ አለመሆናቸውን በጥብቅ ማረጋጋጥ ያለበት ራሱ መንግስት ነው መሆን ያለበት  ፡፡

ያኔ ብቻ ሳይሆን ፤አሁንም አንዳንድ  የመንግስት ሃላፊዎች  በራቸውን መክፈት ይፈራሉ…ወደህዝቡ ወርደው ማገልገልንም ሆነ መወያያትን ይሸሻሉ፡፡ ከተገልጋዩ ህብረተሰብና ደምበኞች ጋር ፊት ለፊት ለመገናኘት ልብ የሌለዉም እንደበዛ ነዉ ፡፡ ኔትወርክና ቡድነኝነቱም ቢያንስ ስለመቀነሱ የጎላ ምልክት አልታየም ፡፡ ከሁሉ በላይ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማረጋጋጥ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጀ አመራር መመናመኑ አሳዛኝ እየሆነ ነው ፡፡ ፅንፈንነትና የደቦ ፍርድን ላስቆም አለመቻሉ ከዚህ የሚመነጭ ነው፡፡

ይህ አይነቱ ክፍተት ደግሞ ዳግም የስርዓት ብልሽት  እንዳያስከትል  መፈተሸ  አለበት ፡፡ በተለይ የፅህፈት ቤታቸው ቢሮ ለተገልጋይና ለግልፅ አሰራር፤ሲከፈት የሚያማቸው፤ ተጠያቂነት የሚያርበተብታቸዉ  /open door syndrome ያለባቸው/ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ማስተካከል ብሎም መጥረግ ያስፈልጋል ፡፡ ለዚህ ደግሞ በቅጥር ፣ በምደባም ሆነ ሹመት ቀዳሚዎቹ መስፈርቶች ብቃት ፣ ችሎታና አገር ወዳድነት መሆን አለባቸው ፡፡ ቢሮክራሲው ሲለወጥ ፣አጠቃላይ አገራዊ ለውጥ ለማስፈን ያመቻልና !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top