Connect with us

ከአባይ ወንዛ ወንዙ እስከ ደሞ ለአባይ (ክፍል ሁለት )

ከአባይ ወንዛ ወንዙ እስከ ደሞ ለአባይ (ክፍል ሁለት )
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ከአባይ ወንዛ ወንዙ እስከ ደሞ ለአባይ (ክፍል ሁለት )

ከአባይ ወንዛ ወንዙ እስከ ደሞ ለአባይ (ክፍል ሁለት )

   (እስክንድር ከበደ)

የአባይ ወንዝ በእንግሊዝ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በሥነጽሁፍ ሥራዎቻቸው አሻራው ጉልህ ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ ልብወለድ ደራሲዋ አጋዛ ክርስቲ  ”ዴዝ ኦን ናይል ”(Death on the Nile ) መጽሀፍ ጽፋለች፡፡ መጽሀፉ ልብአንጣልጣይ የወንጀል ምርመራ ድርሰት ቢሆንም፤”የወንጀል ምርመራ ልብወለድ ንግስት” የተሰኘችውን እንግሊዛዊ ደራሲ ”ዴዝ ኦን ናይል ሪቨር” በተሰኘው መጽሀፏ መቼቱን የመረጠችው ያለምክንያት አይደለም፡፡ 

በአባይ ወንዝ የተፈጠረው  የውሃ ላይ መዝናኛ የእንግሊዝና የምእራባውያን ዲታዎች ምርጫ መሆኑን በተዘዋዋሪ ይነግረናል፡፡ ይህ ደግሞ የታላቁ አስዋን ግድብ ከመሰራቱ በፊትም ካይሮን ያጌጣት የአባይ ውሃ የግብጽ ህልውና ብቻ ሳይሆን የገቢ ምንጫቸው ከሆነ መቆየቱን ይጠቁማል፡፡ 

እንግሊዛዊው ገጣሚ ጆን ኪትስ በእንግሊዝ ሥነጽሁፍ እጅግ የሚታወቅ ገጣሚ ነው፡፡ በ25 አመቱ የሞተው ይህ ዝነኛ ገጣሚ  ለናይል (አባይ)  To the Nile የሚል ግጥም አለው፡፡ ኪትስ በግጥሙ  ከአባይ (ከናይል ይልቅ አባይ ሚለው አጠራር ከ86 በመቶ በላይ በምታበረክተው ኢትዮጵያ በሚጠራበት ስም መጠቀሙን  እመርጣለሁ) ጋር በቀጥታ የሚነጋገርበት ስልት አለው፡፡ አባይ (ናይል)  የአፍሪካ ተራሮች ልጅ መሆኑን ይተርካል፡፡ጋጣሚው ጆን ኪትስ  ”ለአባይ” በተሰኘ ግጥሙ የግሪክን አፈታሪክ ተንተርሶ ቢጽፈውም በእውኑ የጨበጡትና የዳሰሱት የአባይ ልጆች  የስለሺ ደምሴና የእጅጋየሁ ሺባባው(ጂጂ)  የአባይ ዝፈኖች  የኪትስን ግጥም ለሁለት የተቋረሱት ይመስላል፡፡

ኪትስ የአባይን ወንዝ የአፍሪካ ተራሮች ልጅ ብሎ ሲጀምር፤ስለሺ ደምሴ ደግሞ ”አባቱ  ደጀን… እናቱ ጣና” ብሎ ምንጩን ይነግረናል፡፡ ጋሽ አበራ አባይን ለአንድ አካባቢ ሳይሆን በአራቱ መአዘን ለሚገኙ የኢትዮጵያ ልጆች ሀብት መሆኑን ከማብሰር ባሻገር ” የኢትዮጵያ ልጆች መጡ እንደገና…የአፍሪካ ልጆች መጡ እንደገና…” በሚል የሕዳሴ ዘመን ላይ መድረሳችን የሚጭር ግጥምም ሆነ ቅላጼ ይዘራብናል፡፡  ዘፈኑ አባይ  የኢትዮጵያ፣የአፍሪካና የዓለም ሀብት መሆኑን ይነግረናል፡፡

”ተከዜ እጁ ነው …ዘር መጨበጫው ..” ብሎ እንደዋዛ የሚያልፈው ነው፡፡ የአባይ  ተከዜ ሲደርስ የሚሰጠውን ፍሬ በገደንዳሜ ነግሮን ያልፋል፡፡  ግብጽ በዘመናት የሀይማኖት መሪዎችን እየሾመች በፈጠረችው  የዘመናት ትምህርት የተቃኘው ጋሽ አበራ ሞላ ወንዙን እንዲፈስ የሚፈልግበት መንገድ በአግባቡ ላጤነ  የሚገባው ነገር ይኖራል፡፡

አባይ መነሻው ከኢትዮጵያ መሆኑን ይነግረንና ቁጭቱን የሚቀዳው ግን ከሜዲትራኒያ ባህር ይሆናል፡፡ አባይ ከሜዲትራኒያ  ተነስቶ በግብጽ አድርጎ ወደደ ሱዳን በመፍሰስ ኢትዮጵያን እንዲጠይቅ የጋሽ አበራ ሞላ ዘፈን ይለምናል፡፡ 

የወንዙን ፍሰት ሲያደንቅ ከደጀንና ጣና የተወለደውን ወንዝ ሱዳንን አልፎ ግብጽ ድረስ  እንደሚጓዝ ብሎም እስከ ሜዲትራኒያ በስስት የሚሸኘው ዘፋኙ ፤ ግብጽን አረስርሶ የደጇን ዳርዳር በጥጥ ሲያንበሸብሻት ቁጭት ይጭርብናል፡፡ ወንዙን ከኢትዮጵያ ሸንቶ ፤ኢትዮጵያ እንዴት እንደምትናፍቀው አሽሞንሙኖ የሚጠራው ግን ከሜዲትራኒያ ባህር በተገላቢጦሹ ነው፡፡ 

”ከእለታት አንድ ቀን ጎረቤት መጣና ዘጠኝ ሞት ደጅህ ቆሟል ቢለው..

ዘጠኝ ሞት መጥቶ ከደጅ ምን አስቆመው አንዱን ግባ በለው ይባል ነበር ድሮ ከነምሳሌው ” ይለናል ጋሽ አበራ ሞላ በዘፈኑ፡፡(ይቀጥላል)

ጂጂ  ወንዙን ጠይቃ  “አባይ ወንዛ ወንዙ ብዙ ነው መዘዙ” ብላ ትዘጋዋለች። “መዘዙ” ምንድነው? የሚለውን ባትነግረንም “ውሀው ሲነካ የሚያንቀጠቅጣቸው ” መኖራቸውን በውብ ዜማዋ የጫረችብንን  ደጋግመን እንድናስብ ትታን ትነጉዳለች።

ከጂጂ በኋላ ስለአባይ  የዘፈነው ጋሸ አበራ ሞላ  ነው።  የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ በኋላ የመጣ ዘፈን ነበር። የአባይ ወንዝ አገር ያስተሳሰረ ፤ ከመነሻው ጀምሮ የወንዙን መልካአምድራዊ ፍሰትና ከሰው አካል ጋር አመሳስሎት ይቃኛል።

ግዮን ተጸነሰ ከሰሜን ተራራ

አባይ ተወለደ ከእናቱ ጣና

መረብ ግንባሩ ነው

ተከዜ እጁ ነው ዘር መጨበጫው

አዋሽ እምብርቱ የልጅ እትብቱ

ወገቡ አባይ ነው መነቃነቂያው…

አባቱ ደጀን

እናቱ ጣና

“የኢትዮጵያ ልጆች መጡ እንደገና ” በሚል አርበኝነትን የሚያጭር ዘፈን ይዞ መጣ።

የጂጂ፣የጋሽ አበራ ሞላና ቴዲ አፍሮ ሶስቱ ዘፈኖች በቀጭን ገመድ የሚያገናኛቸውን እና የተዘፈኑበትን እይታን የኔን እይታ በቀጣይ አነሳለሁ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top