Connect with us

“ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

“ዛቻ!!” የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

“ዛቻ!!”  የካይሮ ፖለቲከኞች የተበላ ዕቁብ !

(ንጉሥ ወዳጅነው – ድሬቲዩብ)

 ለማንኛውም አለመግባባት ዘመናዊው መፍትሄ መነጋጋርና መደራደር ነው ፡፡ ተፈጥሮ በአባይ ያስተሳሳራቸው ኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን ግን ባለመስማማትም ተስማምተው እንዳይኖሩ የግብፅ ፖለቲከኞች እያደናቀፉ ነው ፡፡ እንኳንስ አገራችን ታላቁን የህዳሴ ግድብ መገንባት ጀምራ፣ ቀደም ሲልም ፊቷን ወደልማት እንዳታዞርና እንዳትረጋጋ ይፈፀም የነበረው ደባ ከፍተኛ ነበር ፡፡ ማስፈራሪያና ዛቻውም ምንም እንኮን የተነቃበት ቢሆንም የኖረው ስልታቸው ነው ፡፡

 ለአብነት ያህል  የቀድሞ የግብዕ ፕሬዝዳንት አንዋር ሳዳት “የአባይን የውሃ ፍሰት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውም ተግባር ግብፅን ወደ ጦርነት የሚያስገባና ጠንካራ አፀፋዊ እርምጃን የሚጠይቅ ይሆናል’’ ሲሉ፤ በህዝብ አመፅ ከስልጣናቸው በሃይል የተባረሩት ሆስኒ ሙባረክም በአባይ ተፋሰስ ላይ የሚሰራን ማንኛውንም ልማት እንደሚያወድሙት በተደጋጋሚ ሲዝቱ ነበር ፡፡

 በ2011 የቀለም አብዮትና እሱን ተከትሎ በተካሄደው ምርጫ ስልጣን ላይ የወጡት የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ መሪውና  በወታደሩ ሃይል ከስልጣን ተገፍተው የወረዱት ሙሃመድ ሙርሲም  “ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛ ላይ ናቸው’’ በማለት በይፋ ሲናገሩ ተደምጠዋል ። ይህ የጦርነት ጉሰማ ንግግር ሁሉ መልዕክቱ ግልፅ ነበር። ማስፈራራት !!

አሁን ግብፅን እየመራ ያለው የአብዱልፈታህ አልሲሲ አስተዳዳርም የሙርሲን መፈክር ከማስተጋባት አልተቆጠበም ፡፡ በተለይ በድርድር ስም የአገራችንን በሀብቷ የመጠቀም መብት ቅርቃር ውስጥ ለመክተት ፣ በሶስተኛ  ወገን ተፅኖ ለማድረስና በእጅ አዙር ግንባታውን ለማደናቀፍ ነው እየተሯሯጠ የሚገኘው ። በአገራችን የውስጥ ጉዳያ ገብቶ ለማተራመስም ሆነ ከጎረቤት አገሮች ጋር እያፋጠጡ የቀውስ ተፅኖ ለመፍጠር የሚካሄደው መራኮት እስከ ቅርቡ የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ውዝግብ መቀጠሉም ገጦ ታይቷል  ፡፡

ከቀናት በፊት ዲ.ሬ.ኮንጎ መዲና በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተካሄደው ድርድር ከመጀመሩ በፊት የግብፅና ሱዳን አየር ሃይሎች የጋራ ልምምድ ማድረጋቸው ፣ ወጣ ባሉ የካይሮ ፖለቲከኞችና ምሁራን የተደረጉ የጦርነት ጉሰማዎችም ሆኑ ፣ ከሳምንታት በፊት በካርቱም የተካሄደው የፕሬዘደንት አልሲሲ ጉብኝት አንድምታቸው የታወቀ ነው ፡፡እርግጥ ውጤት ካልታዬበት ያ ድርድር በሆላም ዛቻና ማስፈራሪያው ሰሚ የለውም እንጂ ማደንቆሩ አልቀረም ፡፡ 

 የኢትዮጵያን በራሷ የተፈጥሮ ሀብት የመጠቀም መብት ለመገደብና በትብብርና በመተሳሳብ ማደግን ለማደናቀፍ የሚፍጨረጨሩት የካይሮ መሪዎች ምኞታቸው አይሳካም እጂ ነገም ተኝተው እንደማያድሩ የታወቀ ነው ፡፡ ንስራዊያን ጦርነት በመለኮስ የቅድመ አያቶቻቸውን ውርደት ዳግም ለመቀበል ግን ሊደፍሩ አይችሉም ፡፡ አገራችን በተለያዩ የውስጥና የውጭ ቀውሶች እንድትደማ ፣ ከልማት ጉዙዋም እንድትናጠብ ከማሴር ሊቦዝኑ ግን  አይችሉም ፡፡ እናም ብቸኛው መፍትሄ አንድነታችንና ሰላማችንን ጠብቆ ፣ ግድቡን ከፍፃሜ ለማድረስ መረባረብ ብቻ ነው ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top