Connect with us

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የሮሃ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የሮሃ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተጀመረ
የአዲስአበባ ከተማ  አስተዳደር

ዜና

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የሮሃ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት የሮሃ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

የአዲስአበባ ከተማ  አስተዳደር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ላለፉት ሰባት ወራት በትኩረት ሲሰራበት የነበረውን እና ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባውን የሮሃ ህክምና ማዕከል ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት  አስጀመሩ።

ከ1ሺ 100 አልጋዎች በላይ ያሉት እና 7 ሺ 500 የስራ እድል የሚፈጥረው ሮሀ የህክምና ማዕከል፤ መንፈስን የሚያድስ ውብ መናፈሻን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ 5 ትላልቅ ሆስፒታሎች የሚኖሩት ሲሆን ፣ በአመት ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል ተብሏል።

ይህ ፕሮጀክት ከተማዋ ከዜጎቿና ከነዋሪዎቿ አልፋ የእንግዶቿን ጤና በብቃት መንከባከብ የምትችል መሆኗን ከማሳየት ባሻገር ፣ ሀገራችን ዜጎቿን ለማሳከም ወደ ውጭ የምትልከውን የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል።

የህክምና ማሰልጠኛ ኮሌጁም ብቁ የህክምና ባለሙያዎችን በማፍራት ለሌሎች የህክምና መስጫ ተቋማት አጋዥ ጉልበት እንደሚሆንም ጠቅሰዋል።

አዲስ አበባችን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የመሆን ህልሟን ታሳካ ዘንድ እንደ ሮሃ ያሉ ተጨማሪ የህክምና ማዕከላት እንዲኖሯት ተግተን መስራታችንን እንደምንቀጥል እያረጋገጥኩ ፣ በዚህ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ በተለይም ለግንባታው በተመረጠው አካባቢ ይኖር የነበረው ማህበረሰብ ለልማት ተነሳሽነቱን በማስመስከር፤ የታሰበው ስራ በፍጥነት እንዲከናወን ከፍተኛ ትብብር በማድረጉ በከተማው አስተዳደር ስም ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top