Connect with us

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ / ቤት

ነፃ ሃሳብ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)

እውነት ስንነጋር በኢትዮጵያ ያፈረሰ እንጂ የሰራ መቼ በላ? የገደለ እንጂ የሞተላት መች ከበረ? ስንቱ አውራ አንገቱን እንደ ደፋ ወደ ሞት የተሸኘባት ሀገር እኮ ናት፡፡ ስንቱን ባለውለታ እንደ ውለታ ቢስ ስጋውንም ስሙን ቀብረን የምንኖር ህዝቦች እኮ ነን፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ውዝፍ እዳ አለብን ብለው አምነዋል፡፡ ደግሞም እውነት ነው፤ ያላከበርናቸው ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ሀገርና ትውልድ ረግመው አልፈዋል፡፡ ይሄንን አስቦ ያሉትን እናመሰግናለን ማለት ጠቢብነት ነው፡፡

ጠቅላዩን ባልሰሩት መውቀስ የአባት ሆኖ በሚያስመሰግን ስራቸው ማላገጥ ደግሞ የጠላት ሀሳብ ነው፡፡ “ሀገር እንዲህ ሆና እንዴት ሽልማት?” የሚሉ ሞኞች ይገርሙኛል፡፡ የተሸለሙት እኮ ሀገር ናቸው፡፡ የሀገር ጌጦች እንደ ሀገር አፈር የትም ተጥለው በሚኖሩበት ልማድ የሀገር ባለውለታን “አመሰግናለሁ” ማለት ሀገር የመስራትና ሀገር የማክበር አንድ ማሳያ ነው፡፡

ዶክተር አብይ ትናንት አመሻሹን ለአንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ ባለውለታ ከያኒያን እናመሰግናለን ብለው በክብር እውቅና ሰጥተዋል፡፡ እንጦጦ በሚገኘው የጥበብ ማዕከል በተካሄደው የእውቅና ሥነ ሥርዓት ብዙ አንጋፋዎቻችን በክብር መንግስት ለሰሩት ስራ ባለውለታ ናችሁ ብሏቸዋል፡፡

የሜዳይ እውቅና የተሰጣቸው አንጋፋዎች የተመረጡት በእድሜያቸው በቅቡልነታቸውና ለረዥም ዘመን ባገለገሉበት ሙያ ደረጃ ሲሆን ብዙዎቹ ከስድሳ አመት በላይ የሆናቸው ናቸው፡፡ እንደ ጃዝ አባቱ ሙላቱ አስታጥቄ እንደ ቲያትር አባቱ ተስፋዬ አበበ እንደ ሳቅ አባቱ ልመንህ ታደሰ ያሉት መንግስት ለአበረከታችሁን አበርክቶ አመሰግናለሁ ብሎ እውቅና አበርክቶላቸዋል፡፡

ደበበ እሸቱ፣ ፋንቱ ማንዶዬ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ዳዊት ይፍሩ፣ ይልማ ገብረ አብን ጨምሮ በርካታ ለረዥም ዘመን ሀገራቸውን ያገለገሉ በሀገራቸው ህዝብ ክብርን መልካም ስምንና ዝናን ያተረፉ ተወዳጅ የጥበብ ባለሙያዎች ተመስግነዋል፡፡

የዘንድሮው እውቅና የተጠራቀመውን እዳ ለማወራረድ አንጋፋዎቹን ቅድሚያ ሰጥቶ የተካሄደ መሆኑ ተገልጽዋል፡፡ እንዲህ ያለ ብሔራዊ የሽልማት ድርጅት በተለይም በጥበብ ዘርፍ የሌለባት ሀገር የምንኖር ሆነናል፡፡ የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሽልማትም ሆነ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት መንግስት በሥርዓት ህግ አውጥቶ እንዲቀጥል ያልተለመው ስለነበር ተጀመረ እንጂ አልቀጠለም፡፡

ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ሽልማትም ነገ ከነገ ወዲያ በታሪክ ፊት ስም የለሽ እንዳይሆንና ኩነት ማድመቂ ቁስ ብቻ ተደርጎ እንዳይቆጠር እንደ ሰለጠነው ዓለም የዛሬ ሁኔታ እንደ ነበርንበት የትናንት የንጉሥ ክብር ሜዳያችን በህግ በሥርዓትና በደንብ ቀጣይነት እንዲኖረው ቢደረግ መልካም ነው፡፡

ዶክተር አብይ እንዲህ ያለውን እውቅና በመስጠት አንጋፋ የጥበብ ሰዎችን ቦታ ሳንሰጥ የኖርን መሆናችንን በማመን ከስሜታዊ አድናቆት ባለፈ ዘላቂ ክብር እንዳልሰጠናቸው አምነው እንደ መሪ ያደረጉት ነገር እንደ ህዝብ ጭምር ልንኮራበት የሚገባ መልካም ሥራ ነው፡፡

ይህንን ሀሳብ ማንም ያመንጨው ማን ሀሳቡን ላነሱ ሰዎች ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ በምርጫ ዋዜማ መሆኑን ለሚጠራጠሩት ወገኖች ደግሞ ለምርጫም ቢሆን እንዲህ ያሉ አንጋፋዎች ዋጋ አላቸው ብሎ ማመን ታላቅ ክብር ነውና የቱም ምክንያት የተደረገውን ነገር አያጎድፈውም በድጋሚ የምናመሰግናቸውን መንግስትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላመሰገኑልን እናመሰግናለን፡፡

(ፎቶው የተወሰደው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ / ቤት ፌስ ቡክ ገፅ ነው፡፡)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top