Connect with us

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ
© EOTC TV

ዜና

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ የድሬዳዋ እና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ የስራ ዘርፍ ባለሙያዎች  በተገኙበት   በመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት  አዳራሽ የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ፡፡

ብፁዕነታቸው ክትባቱ በዓለም ጤና ድርጅት አመካኝነት ተረጋግጦ በሽታው ለመከላከል   በመላው ዓለም መጀመሩ የሚታወቅ  መሆኑን ጠቅሰው የመከላከል አቅም የሚያጎለብት መከላከያ ስለሆነ  ሁሉም ሰው መከተብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ  የጥንት አባቶቻችን  ዘመናዊ ህክምና ከመምጣቱ በፊት  ለተለያዩ ወረርሽኝ መከላከያ  በማዘጋጀት ይጠቀሙ እንደነበረ አስታውሰው አሁንም በዘመናችን በሳይንሳዊ መንገድ ተዘጋጅቶ የቀረበውን ክትባት  መጠቀም ይገባል ብለዋል ፡፡ 

በአንዳንድ የኀብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ክትባትን  ከሃይማኖት ሥርዓት ጋር  የሚያጋጭ ሀሳብ  ተቀባይነት እንደሌለው  ኀብረተሰቡ ሊገነዘበው ይገባል በማለት

ክትባቱ በሽታው የሚያስከትለውን ጉዳት የሚቀንስ በመሆኑ ሌሎች  የጥንቃቄ እርምጃዎች ቸል እንዳይባሉ አሳስበዋል፡፡

© EOTC TV

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top