Connect with us

የኦሮሞ እና የአማራ መሪዎች ዘር ተኮር ግድያዎችን በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩ መጠየቅ ለምን ሰጉ?

የኦሮሞ እና የአማራ መሪዎች ዘር ተኮር ግድያዎችን በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩ መጠየቅ ለምን ሰጉ?
Photo: Social media

ዜና

የኦሮሞ እና የአማራ መሪዎች ዘር ተኮር ግድያዎችን በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩ መጠየቅ ለምን ሰጉ?

የኦሮሞ እና የአማራ መሪዎች ዘር ተኮር ግድያዎችን በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩ መጠየቅ ለምን ሰጉ?

(እሱባለው ካሳ)

የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች  የጋራ ልማትና ሰላም ላይ በአዲስ አበባ እየመከሩ ስለመሆናቸው በትላንትናው ዕለት የሰጡትን የጋራ መግለጫ እንደአንድ ጉዳዩ እንደሚመለከተው ዜጋ በጥንቃቄ አየሁት። ሁለቱ ክልሎች ካነፀባረቁት የጋራ አቋም መካከል

  1. የሚከሰቱ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል በትብብር ስለመስራት፣
  2. በሁለቱም ክልሎች በሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ተከትሎ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሞትና መፈናቀል በፍጥነት ማስቆም፣
  3. የግጭቱ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ መውሰድ፣ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ፍትህ እንዲያኙ እና ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ፣
  4. የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቤት ንብረታቸው በፍጥነት መመለስና ማቋቋም፣
  5. የኦሮሞ እና የአማራ ወንድማማች ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትስስርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣
  6. አጎራባች ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መከላከል፣
  7. በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚሉ ይገኙባቸዋል።

በጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት እንደተካሄደ የተነገረለት የዚህ ስብሰባ አጠቃላይ የግምገማ ትኩረትና ውጤት ይኸ ብቻ ከሆነ በግሌ ስለተፈፃሚነቱ ከወዲሁ ብዙ እንድል ያስገድደኛል።

“ተቀናጅተን እንሰራለን” የምትለዋ ቃል ከፓለቲካ መሸነጋገል የዘለለ እርባና ወይንም ተፈፃሚነት ይኖረው እንደሆን አብረን የምናየው ሆኖ የተከሰቱት ተደጋጋሚ ዘር ተኮር ጭፍጨፋዎች ጀርባ ያሉ አካላትን በሚገባ ማወቅና መለየት ለቀጣይ ስራ ወሳኝ መሆኑን ስብሰባው ዘንግቷል ብዬ አምናለኹ። ምናልባት ያልተነገረን የስብሰባው ጭብጥ ከሌለ በስተቀር ከዚህ ስብሰባ እጠብቅ የነበረው ጉዳዩ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የጋራ ስምምነት ይኖራል ብዬ ነበር።

በእርግጥም በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ትክክለኛው የዘር ተኮር ጭፍጨፋ መነሻ ምክንያት መታወቁ ቀጣይ እርምጃ ለመውሰድ እና መንግስት ከጊዜያዊ የእሳት ማጥፋት ተግባር ለማላቀቅ ወሳኝ ነበር። ከምንም  በላይ ደግሞ በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ከጭፍጨፋው ጀርባ አንዳንድ የክልል መንግስታት አካላት እጃቸው አለበት የሚለውን ተደጋጋሚ ክስ አጣርቶ ማረጋገጥም ይገባ ነበር። በእርግጥም አንዳንድ የመንግስት አካላት እጃቸው ረዝሞ ከሆነ ከየትኛውም እርምጃ በፊት ይህን እጅ መቁረጥ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ወሳኝ ነበር።

በተጨማሪም ተደጋግመው ከሚነሱ ጥያቄዎች መንግስት “ኦነግ ሸኔ” የሚላቸው ታጣቂዎች ጠንክረው፣ መሰረት ይዘው መታየት የቻሉት ለምንድነው የሚለው በቀዳሚነት መመለስ የነበረበት ነው። ታጣቂዎች የሰላም ፀር፣ የሕዝብ ሥጋት መሆናቸው እየታወቀ የክልሉ መንግስታቱም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ነገሩን እያስታመመ እየተጓዘ ያለው ለምንድነው የሚለውም መልስ የሚሻ ነው።

አሁን ግን በዚህ መግለጫ ይዘት መሰረት የማጣራቱ መሰረታዊ ጉዳይ ተዘልሎ “ችግሩን ለመቅረፍ በጋራ እንስራለን” የሚል መግለጫ ተሰምቷል።

“በጋራ መስራት” ማለት ምን ማለት ነው? የኦሮሚያ ክልል እና የአማራ ክልል በጋራ  ፀጥታ ያስከብራሉ ማለት ነው?  ችግሩ ከኦሮሚያ ክልል አቅም በላይ ከሆነ የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት በይፋ መጠየቅ ለምን አልተቻለም?

ከምንም በላይ የሁለቱ መንግስታት እና የአደራዳሪው የፌደራል መንግስት አስገራሚ አስተሳሰብ በመግለጫው መንፀባረቁ ነው። ስምምነቱ ግድያና መፈናቀልን ለማስቆም፣ አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ፣ የተፈናቀሉትን ለማቋቋም መሆኑን ይነግረናል። 

ይኸ ምን ማለት ነው? የመንግስት ትልቁ ስራ የዜጎቹን ደህንነት ማረጋገጥ አይደለምን? በዚህ በታወቀ ጉዳይ ላይ መማማል፣ ተስማምተናል ማለት ምናልባት በዘዋዋሪ ስራችንን ዘንግተን ቆይተናል፤ አሁን ግን እንሰራዋለን የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ካልሆነ በስተቀር ፋይዳው ምንድነው?

ሁለቱ ክልሎች ተስማሙም፣ አልተስማሙም ሰላምና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የዜጎችን ተዘዋውሮ የመስራት፣ የመኖር፣ ሐብት የማፍራት ሕገመንግስታዊ መብት ማክበር ግዴታ አለባቸው። በዚህ ተፅፎ በተሰጣቸውጉዳይ በየመድረኩ የመማማላቸው ጠቀሜታ በግሌ አልታየኝም። ስምምነቱም በተጨባጭ መሬት ላይ ወርዶ ውጤት ሊያመጣ ይችላል ወይ የሚለውን በቅጡ ታይቷል ብዬ አላምንም።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top