Connect with us

የኮቪድ ክትባት ቅድሚያ የሚያገኙ!!

የኮቪድ ክትባት ቅድሚያ የሚያገኙ!!
ጤና ሚኒስቴር

ዜና

የኮቪድ ክትባት ቅድሚያ የሚያገኙ!!

የኮቪድ ክትባት ቅድሚያ የሚያገኙ!!

እድሚያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከ55-64 ዓመት  ሆነው የሚታወቅ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያባቸው የህረተሰብ ክፍሎች ከመጪው ሰኞ ጀምሮ (መጋቢት 27/2013 ዓ.ም)  የኮቪድ 19 ክትባት አገልግሎት ይሰጣቸዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ  ታደሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  እንደተናገሩት  በአገራችን መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም  ለጤና ባለሙያዎች መሰጠት የተጀመረው   የኮቪድ 19 ክትባት በጥሩ ሁኔ እየተከናወነ እንደሆነ አስታውሰው  እድሚያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከ55 ዓመት በላይ ሆነው የሚታወቅ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያባቸው የህረተሰብ ክፍሎች ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የኮቪድ 19 ክትባት አገልግት እንደሚሰጣቸው የገለጹ ሲሆን ዕድምያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑት የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ  እንዲሁም ተጓዳኝ የጤና እክል ያለባቸው ዕድሜያቸው ከ55 – 64 የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ ክትትል ከሚያደርጉበት ጤና ተቋም የሚከታተሉበትን የህክምና ማስረጃ በመያዝ  አቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያ ወይም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመሄድ እንዲመዘገቡና ክትባቱን መውሰድ እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል::

እንደ ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገለጻ ክትባቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ብሎም በወረርሽኙ ሊከሰት የሚችለውን ሞት እና ጽኑ ህመምን  ለመቀነስ የሚያግዝ  ሲሆን የመከላከያ ዘዴዎችን (ማስክ መጠቀም፣ ርቀትን መጠበቅ እና የእጅ ንጽህናን መጠበቅ) በየዕለቱ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴርም  ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን  በማጠናቀቅ ወደ ተግባራዊ እርምጃ መግባቱ ይታወቃል፡፡(ጤና ሚኒስቴር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top