Connect with us

አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ዋልያዎቹን ሸለመ

አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ዋልያዎቹን ሸለመ
አ/አ ፕረስ ሴክሬቴሪያት

ስፖርት

አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ዋልያዎቹን ሸለመ

አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ዋልያዎቹን ሸለመ

*5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን በአንድነት ተደምሮ ላስመዘገበው ውጤት እጅግ የላቀ ክብርና አድናቆት እንዳለው ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ገለጹ።

የቀጣዩ አፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ በወጣትነት እድሜ ታሪክ ሰርቶ ማለፍ በምኞት የማያገኙት፣ ይልቁንም በትጋት በመስራት የሚጎናጸፉት ክብር ነውና በጥረታችሁ ታሪክ ለማስመዝገብ በመብቃታቹህ፤ ለሃገራችሁ የተለየ የመነቃቃት ስሜት ፈጥራችኃል ብለዋል ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ።

በእግር ኳስ በግል የሚመዘገብ ውጤት የለም  ያሉት ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ውጤት የሚመጣው ሜዳ ላይ በሚጫወቱት ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆን፣ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተጠባባቂዎች፣ ወጌሻዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ አማካሪዎች፣ ደጋፊዎች  … ወዘተ በአንድነት ተጋምደው እንደ አንድ ሆነው ሲሰሩ ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን  ለጀመርነው የብልጽግና ጎዳናና የመደመር ታላቅ ማሳያ ምሳሌ ነው ብለዋል።

በእርግጥ ይህን በአንድነት፣ በአብሮነት በመተባበር የተገኘን ታላቅ ደስታ አጣጥመን ሳናበቃ የእኩይ እቅዳቸውን ለመፈፀም የንፁሃንን ህይወት በመቅጠፍ ሃዘን የጨመሩብን ክፉዎች ታግለን ከማሸነፍ ወደኋላ አንልም፤ እሱንም እናሸንፋለን ብለዋል።

በጅምሩ የድል ጉዞ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን በክብር የገለፀ ሕዝብ አደራውም ከባድ ነው፤አደራውን ለመወጣት  ከቀደመው የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ሩቅ አስባችሁ በትጋት ዓላማችሁን ታሳኩ ዘንድ ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ ብለዋል ።

የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ብሄራዊ ቡድኑን እና አጠቃላይ ለስፖርቱ እድገት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል  ለ33ኛ አፍሪካ ዋንጫ  ያለፈውን የኢትዮጸያ ብሄራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን (ዋልያዎች)5.6 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ ሽለማት ተበርክቷል።(አ/አ ፕረስ ሴክሬቴሪያት)

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top