Connect with us

የመስቀል አደባባይ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ!

የመስቀል አደባባይ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ!
ም/ከንቲባ ወ/ሮአዳነች አቤቤ

ዜና

የመስቀል አደባባይ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ!

የመስቀል አደባባይ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ!

የአዲስአበባ ከተማ ም/ከንቲባ ወ/ሮአዳነች አቤቤ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል አሉ።

የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በመጠናቀቅ ላይ ያለው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

ይህ የለውጡ ትሩፋት የሆነ የግንባታ ፕሮጀክት ባለፉት 9 ወራት በቀን ለ24 ሰአታት ሳይቋረጥ ሲከናወን የቆየ እና ትልቅ ግብ አስቀምጠን መስራት እና ማጠናቀቅ እንደምንችል ያሳየንበት ነው ያሉት ከንቲባዋ ወደፊትም ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

አዲሱ ግንባታ ስድስት ለማስታወቂያ አገልግሎት የሚዉሉ  LED ስክሪኖች ፣ ከመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት 3.5 ኪ.ሜ የሚረዝም የእግረኛ እና የሳይክል መንገድም አደባባዩን ውብ እና ጽዱ ከማድረግ ባሻገር ፣ ፕሮጀክቱ ከወለል በታች ሱቆችን ፣ ከ1 ሺህ 400 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ፣ 155 መጸዳጃ ቤቶች፣ እና የተለያዩ መገበያያ ሱቆችን ያካትታል ተብሏል።

መስቀል አደባባይ የቀድሞ ይዘቱን ሳይለቅ ዘመናዊ ተደርጎ መሰራቱም ልዩ እንደሚያደርገው ወ/ሮ አዳነች በማህበራዊ ድረገፃቸው አስፍረዋል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top