Connect with us

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለጫ ሰጠ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ስፖርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ በ09/07/13 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ በኔክሰስ ሆቴል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ  ሰጠ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢ.አ.ፌ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንትና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ ዶ/ር በዛብህ ወልዴ የኢ.አ.ፌ አቃቤ ንዋይና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሀሰን የኢ.አ.ፌ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፣ ኮ/ር አትሌት ማርቆስ ገነቲ የኢት/አት/ፌዴ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም የፌዴሬሽኑ የጽ/ቤት ረዳት ኃላፊው አቶ ዮሐንስ እንግዳ በሆቴሉ የጋዜጣዊ መግለጫው ሰጥተዋል።

በመግለጫው በተለያዩ ሶስት አጀንዳዎች የተገለፁ ሲሆን የመጀመሪያው አጀንዳ የነበረው

1) የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ዝግጅትን በተመለከተ

2) 50ኛ ዓመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል አከባበር እንዲሁም

3) ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ስላለው አለመግባባት የሚሉ አጀንዳዎች ይገኙበታል።

ጋዜጣዊ መግለጫው ሁሉንም አጀንዳዎች የዳሰሰ ሲሆን በተለይ ግን የቶኪዮ 2020 ዝግጅትን የተመለከተውና እየተንከባለለ ስለመጣውና ሊቀረፍ ስላልቻለው ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ያለው ቅራኔ ነው።

እዚህ ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች በመድረኩ የነበሩት አባላት አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የነበረው “ለቶኪዮ 2020 ዝግጅት አትሌቶች ሆቴል መግባታቸው የሚታወቅ ቢሆንም አትሌቶች በወቅቱ ሊሟላላቸው ይገቡና የስልጠናው ዋና አካል የሆኑ መሠረታዊ ግብአቶችና አለመሟላትና የአሰራር ክፍተቶች ከመፍታት ይልቅ ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸው እና ይህ ጉዳይ ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጎጂ እየሆኑ ያሉት አትሌቶችና አሰልጣኞች እንዲሁም በተዘዋዋሪ ውጤቱን የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዚህ በፊት በፌዴሬሽኑ ስራ ጣልቃ እንዳይገባና የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብን እንዲያከብር ቢጠየቅም ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ ጫና እየፈጠረብን በመምጣቱና ይህም በአትሌቶቻችንና አሰልጣኞቻችን ላይም ችግሩ እየከፋ በመሄዱ የሚመለከተው አካል፣ መንግስትና ባለድርሻ አካላት ፌዴሬሽኑ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ከመስመር የወጣ አሰራር ምክንያት እየደረሰበት ያለውን ችግር የመንግስት አካላትና ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን” የሚል ሐሳብ ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሰልጣኞች ፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችና አትሌቶች የተገኙ ሲሆን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ።(የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top