Connect with us

‹‹ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ከማድረግ መቆጠብ አለበት››

‹‹ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ከማድረግ መቆጠብ አለበት››
ኢኘድ

ዜና

‹‹ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ከማድረግ መቆጠብ አለበት››

‹‹ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ከማድረግ መቆጠብ አለበት››

– በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በህውሓት ደጋፊዎች ብሎም ተከፋይ ጋዜጠኞች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆኑ ጫናዎች ከማድረግ መቆጠብ እንዳለበት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሳሰቡ፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ትናንት በጄኔቭ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን በመቃወምና በአገር ቤት የተካሄደውን የሕግ ማስከበርና የመልሶ ግንባታ በመደገፍ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፣ የኢትዮጵያ ሉአላዊነትን እንዲከበር፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ በህወሓት ጥቅመኞች የውሸት ፕሮፖጋንዳ እንዳይታለሉ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት ጄሪአ በጻፉት ደብዳቤም፣ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በድርጅቱ ፊት ለፊት ነፍሰ በላው የህወሓት መንግሥት ሲፈጽማቸው የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ሀገሪቱን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲመቸው ሆን ብሎ በሚያቀናብራቸው ብሎም በሚደግፋቸው የብሔር ግጭቶች ስለደረሱ ጥፋቶች፣ ጭፍጨፋ እና መፈናቀሎች ሲገልፁ፣ ሲቃወሙ እና የበደሉ ተጠቂዎችን ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ ሲጠይቁ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡(ኢኘድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top