Connect with us

ኢትዮጵያ  ፈጽሞ የሱዳንን አካሄድ መቀበል የለባትም!!

ኢትዮጵያ ፈጽሞ የሱዳንን አካሄድ መቀበል የለባትም!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ኢትዮጵያ  ፈጽሞ የሱዳንን አካሄድ መቀበል የለባትም!!

ኢትዮጵያ  ፈጽሞ የሱዳንን አካሄድ መቀበል የለባትም!!

ከሀምዶክ ደብዳቤ በስተጀርባ ያለው ሴራ

(ሳላባት ማናዬ)

በርካታ መገናኛ ብዙሃን ከትናንት ጀምሮ እያስነበቡት እንዳለው መረጃ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣የአውሮፓ ህብረት  ፣የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ በአደራዳሪነት እንዲሳተፉ በደብዳቤ ጠይቀዋል።

… Abdalla Hamdok has written to the United Nations, African Union (AU), European Union and the United States to formally request their mediation in a bitter regional dispute over the filling of a giant dam built by Ethiopia on the Blue Nile River…

እዚህ ላይ መታየት ያለበት አንድ ቁም ነገር አለ እስካሁን ሱዳንም ሆነች ግብፅ በዓባይ ናይል ወንዝ ላይ በገነቧቸው ግድቦች አንዳችም ድርድር አልተካሄደም።አለም አቀፍ ተቋማትንም ይሁን ድርጅቶች አልያም ኢትዮጵያን አንድም ጊዜ አማክረው አያውቁም ።

ከዚህ አኳያ አዲሱን የሱዳን አካሄድ በፍጥነት የሚያወግዝ መግለጫ ማውጣት ይገባል የሚል እምነት አለ። አዲስ አበባ ለሁሉም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የካርቱም አካሄድ አህጉራዊውን አጀንዳ 2063 መርህ የሚጥስ መሆኑን ጠቅሳ ማሳወቅ ይገባታል።

በአጀንዳ 2063 ሁሉም አባል ሀገራት እንደ ተስማሙት በአህጉሪቷ የሚፈጠሩ ችግርችን እና ውዝግቦችን አህጉራዊ መፍትሄ መሻትን ያስቀምጣል እና። አሁን ሱዳን ገና ከጅምሮ ጥሳዋለች ።

ከሀምዶክ ደብዳቤ በስተጀርባ ያለው ሴራ

እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን ማገናኘት ወሳኝ ነው። አንድ የግብፁ ፕሬዚዳንት  የካርቱም ጉብኝት እና የሃምዶክ የካይሮ ጉብኝት ሲሆን ሁለት የሃምዶክ ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራዎች እና የስጋት ፖለቲካ ተዛማች ተፅዕኖዎች ናቸው።

ሀምዶክ ኢኮኖሚስት ናቸው ፤የግድቡን ጥቅም እና ጉዳይ በሚገባ ያውቃሉ፡ አዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ፀሃፊ በነበሩበት ወቅት   በኢሲኤ አዳራሽ አንድ ጉባኤ ተካሂዶ ነበር።

የዚያ ጉባኤ አጀንዳ ደግሞ እንዴት የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ፖሊሲ አዋጭ ማድረግ ይቻላል የሚል ነበር። ደቡብ ኮሪያዊው የምጣኔ ሀብት ምሁር ነበር ፍኖተ ካርታውን ከቀድሞው የኢ ሲ ኤ ሃላፊ ካርሎስ ሎፔዝ ጋር ያዘጋጁት።

ያኔ ዶክተር አብደላ ሃምዶክ እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራትን በጥቅም የሚያስተሳስሩ ግድቦች ለአፍሪካ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በኩራት ተናግረው ነበር።እኔም ያኔ ለዜና ሽፋን ስለነበርኩ ነው።

ታዲያ ዛሬ ላይ ለም ን የህዳሴውን ግድብ ተቃርነው ቆሙ ?

ታሪክ እና ፖለቲካ በካርቱም ቤተ መንግስት

ወቅቱ ሱዳን ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችበት ሰሞን ነው። 1950ዎች መጨረሻ አካባቢ 1956። ከድህረ ቅኝ ግዛት ማግስት በሱዳን ኡማ ፓርቲ አዲስ መንግስት አዋቅሮ የተሻለ አመራር እየሰጠ ነው።

በታላቁ ወንዝ ላይ የተፈረመው የ1929ኙ የቀኝ ግዛት የውሃ ውል ይሻር ዘንድ አልያም በአዲስ ይተካ ዘንድ በካርቱም ሰዎች ግድ ብሏል።

ድርድር ተጀመር ፤ድርድሩ በካርቱም የውሃ ማህንዲሶች እና ዲፕሎማቶች የተሻለ ብቃት የካይሮን ሰዎች አደጋ ውስጥ ከተታቸው። የውሃ ጂኦ ፖለቲካ ምሁራን  እንዳስቀመጡት፤የካይሮ ጆሮ ጠቢዎች አንድ ነገር ዘየዱ በካርቱም መፈንቅለ መንግስት እንዲካሄድ ሴራ ወጠኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ካይሮ ጠሯቸው  ከዚያ የሆነው ሆ ነ።ጀኔራል ኢብራሂም አቡድ የካርቱም መፈንቅለ መንፍስት ተዋሪ ሆኖ ወጣ። ካይሮ ስምምነቱን እንደፈለገች አደረገች ታህሳስ 1959 ተፈራረሙት።

አሁናዊው የሱዳን ፖለቲካ በካይሮ ሰዎች እየታመሰ ለመሆኑ በርካታ መረጃዎች አሉ። ሀምዶክም ቢሆኑ የ1958ቱ ታሪክ በራሳቸው ላይ እንዳይሰልስ ፍርሃት አድሮባቸዋል ነው የሚባለው።

ኢትዮጵያ ይህን የሱዳን እምነት ያጣ አካሄድ ከዚህ ታሪክ ጋር በማገናኘት የእኔ የምትለውን አዋጭ የዲፕሎማሲ መንገድ መከተል አለባት።ድርድሩ ከአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ወጥቶ ሌሎች አካላትም የሚሳተፉበት ( የራሳቸውን ሴራ የሚጎነጉነበት ከሆነ) ነገሮች እጅግ ወደ ከፋ ሁኔታ ይለወጣሉ።

ያ ከመሆኑ በፊት ግን ከአፍሪካ ህብረት ውጭ ለሌሎች በሯን ዝግ ማድርጓ አዋጭ ጉዳይ ነው።  በመጨረሻም በዚህ አሳሳች መንገድ ከቀጠሉ እናንተ በአስዋን ግድብም ሆነ በሮዛሪ ግድብ ለድርድር እንዳልተቀመጣችሁ ሁሉ ደህና ሁኑ ብሎ አሰልችውን ድርድር መዝጋት የመጨረሻው አማራጭ ነው።

ከሱዳን አካሄድ በስተጀርባ ያለውን የግብፅ እና የአዲሱን የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ከሊቀ መንበር የኮንጎው ፕሬዚዳንት የሴራ ዶሴ መፈተሽም ተገቢ ይመስለኛል፤

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top