Connect with us

” የአማራ ሕዝብ ታቅዶ በተሠራ የጥላቻ ትርክት በሚወዳት ሀገሩ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ነው!!”

" የአማራ ሕዝብ ታቅዶ በተሠራ የጥላቻ ትርክት በሚወዳት ሀገሩ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ነው!!"
አብመድ

ነፃ ሃሳብ

” የአማራ ሕዝብ ታቅዶ በተሠራ የጥላቻ ትርክት በሚወዳት ሀገሩ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ነው!!”

” የአማራ ሕዝብ ታቅዶ በተሠራ የጥላቻ ትርክት በሚወዳት ሀገሩ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ነው!!”

~ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፤  የአማራ  ክልል ርእሰ መሥተዳድር

ርእሰ መሥተዳድሩ በአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የግማሽ በጀት ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡

የትህነግ የጥፋት እና የክህደት ቡድን የአማራ ሕዝብ እና መንግሥትን በጠላትነት ፈርጆ ሲንቀሳቀስ እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡

ቡድኑ የአማራ ሕዝብ በሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች እንዲጠላ እና በጥርጣሬ እንዲታይ ብቻ ሳይሆን የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድምና እህት የሀገሪቱ ሕዝብ ጋር ተቻችሎ፣ ተዋዶ እና በመተባበር ላይ የተመሰረተ የሀገር ግንባታ ሂደት የራሱን አስተዋጽኦ እንዳያበረክት ሲሠራ እንደነበርም አውስተዋል፡፡ 

በዚህም ምክንያት የአማራ ሕዝብ በሚወዳት እና በሚሳሳላት ሀገሩ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልሎች ለ27 ዓመታት ታቅዶ በተሠራ የጥላቻ ትርክት ባፈራው ሀብትና ንብረት የባለቤትነት መብቱን ተገፎ እንዲፈናቀል ተደርጓል ብለዋል፡፡

የአማራ ሕዝብ እጅግ አሰቃቂና ግፍ በተሞላበት መንገድ ሲደበደብ እና ሲገደል እንደነበርም ርእሰ መሥተዳድሩ በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡ በተለይም አሁን በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የአማራ ሕዝብ እየተሳደደ፣ በብሔሩ፣ በማንነቱ፣ በቀለሙ እና በሃይማኖቱ ግፍና በደል በተሞላበት መንገድ ከሚኖርበት ቀዬ እንዲፈናቀል ተደርጓል ብለዋል፡፡ ሀብት ንብረቱን መዘረፉን እና እጅግ አሳዛኝ በሆነ መንገድ ሕይወቱን ማጣቱንም ርእሰ መሥተዳድሩ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡

“የዘር ማጥፋት ሥራ ተሠርቶበታል፤ ከሞት የተረፈውም በመጠለያ ካምፕ ሆኖ የመንግሥትን እጅ እንዲያይ ተደርጓል” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና በደል እየደረሰ ያለው በትህነግ የጥፋት እና የክህደት ቡድን ሴራ መሆኑ ግልጽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ቡድኑ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም የአማራን ሕዝብ እና መንግሥትን በጠላትነት ፈርጆ ክልሉን ለማተራመስ አቅዶ እየሠራ የመጣ ቢሆንም የውስጥ አንድነትን በማጠናከር በተሠራው ሕግ የማስከበር ሥራ ሴራው መክሸፉን አቶ አገኘሁ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

የትህነግ ቡድን ከጥላቻ ትርክቱ በላይ ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ዘመቻው ራሱን አግልሎ ለጦርነት ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበርም አንስተዋል፡፡ ይህንን ሴራውን ቀድሞ በመረዳት የአማራ ክልል መንግሥትም ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበርም አንስተዋል፡፡ በተለይ በ2012 ዓ.ም ቡድኑ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ቢያመራ እንዴት መመከት እንደሚቻል እቅድ ጭምር ተዘጋጅቶ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የትህነግ የጥፋት ቡድን ያሰማራው ኃይል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ በሁሉም አቅጣጫ ትንኮሳ እና የማጥቃት ሙከራ ማካሄዱን አቶ አገኘሁ አስታውሰዋል፡፡ በአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ላይም በተመሳሳይ መንገድ በማእከላዊ ጎንደር ጠገዴ፣ ቅራቅር እና በሶሮቃ ግንባር የትንኮሳ እና የማጥቃት ሙከራ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡ 

ሙከራው በጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ዳግም ላይመለስ መደምሰሱን ገልጸዋል፡፡ ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ከሌላው የጸጥታ መዋቅር እና ከሕዝቡ ጎን በመሰለፍ የትህነግን የጥፋት እና የክህደት ቡድን በተለይም በአውደ ውጊያዎች ድልን እየተቀዳጀ የጠላት ኃይልን ድባቅ መምታቱን አቶ አገኘሁ አውስተዋል፡፡

በተለይም ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ራሱን እስኪያዘጋጅ፣ ኃይሉን እስኪያጓጉዝ እና ሎጀስቲክስ እስኪያደራጅ ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ በሁሉም ግንባሮች በተለይም በጠገዴ፣ ቅራቅር እና በሶሮቃ የጠላት ኃይልን ከንቱ ምኞት በመመከት እና በመደምሰስ የሀገር ማፍረስን እኩይ ተግባር ማክሸፉን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ክቡር መስዋእትነትን ከፍሏል ብለዋል፡፡

ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን በመሆን የተጎናጸፈው ድል ታሪክ የማይረሳው መሆኑን ነው የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ በሪፖርታቸው፡፡

የአማራ ሕዝብ የታገለለትን የፍትህ፣ የነጻነት እና የማንነት ጥያቄ ጀግኖች ልጆቹ ተጋድሎ እውን አድርጓል ብለዋል፡፡ “የትህነግን የሴራ ፖለቲካ በማክሸፍ እና ሀገረ መንግሥቱ እንዲቀጥል በማድረግ ዘመን የማይሽረው ትልቅ ድል ተቀናጅተናል፤ ስለሆነም የአማራ ሕዝብ እና መንግሥት በሀገር ደረጃ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ ቁልፍ ድርሻ ተወጥቷል” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡

የአማራ ሕዝብ እና መንግሥት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያደረገው ድጋፍ ጉልህ እንደነበር ርእሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡ በተለይም ታግተው የነበሩ የሰሜን እዝ አባላትን የሰሜን ጎንደር፣ የበየዳ እና የጠለምት አካባቢ ሕዝብ፣ የሰሜን ወሎ የራያ ቆቦ ሕዝብ፣ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሕዝብ የሠራዊቱን ሕይወት ለመታደግ ያደረጉትን ርብርብ በአድናቆት ጠቅሰዋል፡፡(አብመድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top