Connect with us

አቶ ደመቀ መኮንን ከተሿሚ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አቶ ደመቀ መኮንን ከተሿሚ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ነፃ ሃሳብ

አቶ ደመቀ መኮንን ከተሿሚ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አቶ ደመቀ መኮንን ከተሿሚ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአውስትራሊያ፣ ጋና፣ ጣሊያን፣ ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሴኔጋል የተሾሙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደሮች ጋር ዛሬ፣ መጋቢት 02 ቀን ቀን 2013 ውይይት አካሂደዋል።

ተሿሚ አምባሳደሮቹ በተሾሙባቸው አገራት በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዘርፎች የሚያከናውኗቸውን ተግባራት የያዘ የ100 ቀናት እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአምባሳደሮችን እቅድ መሰረት በማድረግ በሰጡት የስራ መመሪያ የተመደቡባቸው አገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንዲሁም የዜጎቻችንን መብት፣ ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራትን በትኩረት ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው አምባሳደሮቹ ስራዎቻቸውን ሲያከናውኑ ከአገራችን አስፈጻሚ ተቋማት ጋር ጥብቅ ትስስር በመፍጠር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተው ገልፀዋል።

በመጨረሻም ሚኒስትሩ በአሁኑ ወቅት የሀሰት መረጃዎች በስፋት በማሰራጨት የአገራችንን መልካም ገጽታ ለማጉድፍ የተወሰኑ አካላት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰው፡ ለዲጂታል ዲፕሎማሲ ስራዎች ትኩረት በመስጠት ተጨባጩን የአገራችንን ሁኔታ ማስገንዘብ እንደሚያስፈልግ ገልጽዋል።(የውጭ ጉ/ሚ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top