Connect with us

ከከፍታዋ ያልወረደችው ጎንደር ምኒልክን በባልቻ ሳፎ አጅባ አድዋን አክብራለች

ከከፍታዋ ያልወረደችው ጎንደር ምኒልክን በባልቻ ሳፎ አጅባ አድዋን አክብራለች
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ከከፍታዋ ያልወረደችው ጎንደር ምኒልክን በባልቻ ሳፎ አጅባ አድዋን አክብራለች

ከከፍታዋ ያልወረደችው ጎንደር ምኒልክን በባልቻ ሳፎ አጅባ አድዋን አክብራለች

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ ድሬቲዩብ)

አከባበራችን የየራሱ ችግር ቢኖርበትም የዘንድሮ አድዋ ደማቅና ውብ ነበር፡፡ አድዋን ያየ ከአድዋ ተነስተው ኢትዮጵያን ያመሷት ጎጠኞች ከኢትዮጵያ ምድር መጥፋታቸውን ያረጋግጣል፡፡ አድዋ ደማቅና ውብ ነበር፡፡ በሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በምድቀት አክብረውታል፡፡ ሌላው ቀርቶ የራስ መኮንንን ሀውልት ሲፈርስ ቆሞ ያየው ሀረር ካቢኔ የራስ መኮንንን ድል ቆሞ አክብሯል፡፡

አዲስ አበባውያን በመስቀል አደባባይ የተከበረው ዝግጅት ከምኒልክ ይልቅ ሌሎችን ከፍ አድርጎ ማጉላቱ አድዋ ሳይሆን ምርጫ ቅስቀሳ ይመስላል በሚል ተሳልቀውበታል፡፡ ያም ቢሆን አድዋ በመስቀል አደባባይ ሲከበር ማየት የተቻለው ግን በህወሃት መቃብር ላይ መሆኑን የካደ የለም፡፡

ብልጽግና ዓላማው ምንም ይሁን ምን ከአድዋ አከባበሩ ግን ከአድዋ መንደር የጎጥ በሽተኞች የሚሻል አፍሪካዊ መንፈስና ስሜት እንዳለው አሳይቶናል፡፡ በኢትዮጵያ የተከበረበት ድባብ ምናልባትም ብዙ አመታት ወደ ኋላ የሚመልስና የሚመሰገን እንደሆነ አይተንበታል፡፡

ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስና ደብረ ብርሃን አድዋ ድምቅ ብሎ ከተከበረባቸው የሀገራችን ከተሞች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የአዲስ አበባው ምኒልክ አደባባይ እጅግ ውብና ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ያማረ ሆኖ ተዘክሯል፡፡

ጎንደር በዚህ የአድዋ ኩነትም በሌላ ማንነት ልዩ ከሆነው ስፍራው ከፍ ብላ የምትቀጥልበትን መንፈስ አሳይታለች፡፡ የጎንደር ወጣቶች የአድዋን በዓል ሲዘክሩ ዛሬም እምዬ ምኒልክ ከባልቻ ሳፎ ፎቶ ጋር ገጭ አድርገውታል፡፡

ጎንደር ዘረኝነትን ድል አድርጋለች፡፡ ባልቻ ለጎንደር መድፍ መተኮሱን ለኢትዮጵያ መዋደቁን ሀገር መውደዱን አክብራ ቦታ ሳይጠባት ትልቅ ቦታ ሰጥታ ዘክራዋለች፡፡ ጎንደር ባልቻን ከፍ ያደረገችው የበለሳ ሰው ስለሆነ አልያም እትብቱን አርማጭሆ በመቅበሩ አይደለም፡፡ ፍቅሯ ለሀገሩ ካለው ፍቅር ስለሆነ አድዋን ስትዘክር ምኒልክን ስታነሳ ለምኒልክ መድፍ አገላባጭ የሚሆን ቦታ አላጣችም፡፡

አንዳንድ የበዓሉ አከባበር ሥርዓቶች የበዓሉ አባት ለሆኑትና ዓለም በአንድ ድምጽ ለተስማማባቸው የድሉ ጌታ የሚሆን ቦታ አጥተው አይተናል፡፡ በየአካባቢው የየአካባቢውን የአድዋ ጀግኖች መዘከሩ በራሱ ችግር የለውም፡፡ ዋናውን የአድዋ አባት አውርዶ ለየዘመኑ ሹም በሚያደላ መንፈስ አድዋን ማክበሩ የአድዋን ቦታ ማሳነስ እንዳይሆን እንደ ጎንደር ካለው አከባበር መማር አለብን

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top