Connect with us

እስካሁን 15 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል

እስካሁን 15 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

እስካሁን 15 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል

እስካሁን 15 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል

      ፓርቲዎቹ በበጀት እጥረት ተቸግረዋል፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር አየተወያየ ነው፡፡ ውይይቱ በእጩዎች ምዝገባ ሂደት እና በሂደቱ በቀረቡ አቤቱታዎች እንዲሁም በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እስካሁን ባለ መረጃ 15 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ማስመዝገባቸውን እና በዚህም ከ2 ሺህ በላይ እጩዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ብልጽግና፣ ኢዜማ፣ ባልደራስ፣ አብን እና ሌሎችም ፓርቲዎች በእስከዛሬው የምርጫ ሂደት ታይተዋል ያሏቸውን ችግሮች አንስተዋል፡፡

ከተነሱት ችግሮች መካል የአስፈፃሚ አካላት በቢሮ አለመገኘት እና የእጩዎች መታሰር የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ተሰብሳቢዎቹ በእነዚህ እና ሌሎችም ችግሮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን አሁን ላይ ችግሮቹ ከስር ከስር እየተፈቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እጩዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ፓርቲዎቹ በበኩላቸው የጊዜ ገደቡ እንዲራዘምላቸው ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ የበጀት እጥረት መኖሩንም አንስተው መፍትሄ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል፡፡(ኢቢሲ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top