Connect with us

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ስያሜ ለመቀየር ታቅዷል

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ስያሜ ለመቀየር ታቅዷል
ኦቢኤን

ዜና

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ስያሜ ለመቀየር ታቅዷል

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ስያሜ ለመቀየር ታቅዷል

የኢ.ፊ.ዲ.ሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ  ሃገራዊ ለዉጡን ተከትሎ  የሚጠበቅበትን ሃገራዊና አለማቀፋዊ  ተልእኮ በአግባቡ እንዲወጣ  ሁሉ አቀፍ ተቋማዊ ለዉጥን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ በሚኒስትር ማዕረግ  የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ተናገሩ።

የአመራር አካዳሚዉ  ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስን ጨምሮ የአመራር አካዳሚዉ አመራርና ሠራተኞች  በሱሉልታ ከተማ እየተገነባ ያለዉንና በቅርቡ የሚመረቀዉን  ዘመናዊ  የአመራር አካዳሚ ጎብኝተዋል።

በአካዳሚዉ ቅጥር  ግቢ ዉስጥ ባለፈዉ ክረምት የተተከሉ ችግኞችን በጋራ ሆነዉ ዉሃ ያጠጡትና የተንከባከቡት የአመራር አካዳሚዉ ኃላፊዎች: ሠራተኞችና የሲቪል ሰርቪስ አመራሮች  በተቋሙ የስድስት ወራት የስራ አፈጻደም ሪፖርት ላይም በሱሉልታ ከተማ  ተወያይተዋል።

የአመራር አካዳሚዉ ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ከተቋሙ ስያሜ ጀምሮ የአካዳሚዉን አላማ፣ተልእኮ፣ ራእይና እሴቶችን ለመቀየር ሁሉአቀፍ  ተቋማዊ ሪፎርምን እየተገበርን ነዉ ብለዋል።

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በሕዝብና በሐገር ሃብት የተገነባ ሃገር አቀፍ ተቋም ነዉ ያሉት ኃላፊዉ አካዳሚዉ  ከልማታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና ማስተማሪያነትና  ከመለስ ዜናዊ ሌጋሲ ማስፈጸሚያነት ተላቆ በኢትዮጵያ: በአፍሪካና በአለማቀፍ ደረጃ ዘመናዊና  ታዋቂ  የአመራር ማሰልጠኛ  ማእከል እንዲሆን በትኩረት እየሠራን ነዉ ብለዋል።

የአካዳሚዉ  ስያሜና  የአካዳሚዉ  ተቋማዊ ተልእኮ  በቅርቡ ለመንግስት ቀርቦ ዉሣኔ ይሠጥበታል ያሉት ሃላፊዉ  የአመራር አካዳሚዉ ሃገራዉ ለዉጡን ከመቀላቀል አልፎ ሃገራዊ ለዉጡ እንዲመራም በትኩረት እየተሠራ ነዉ ብለዋል።

በቻይና መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እየተገነባ ያለዉ:  በባለ አምስት ኮከብ የሆቴል ደረጃ እየተገነባ ያለዉና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ የመጀመሪያዉ የሆነዉ አዲሱ  የአመራር አካዳሚ ግንባታዉ በአሁኑ ወቅት  ከ95 በመቶ በላይ መጠናቀቁንና በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚችልም አቶ አወሉ አብዲ ለOBN  ተናግረዋል።

አዲሱን የአመራር አካዳሚ የጎበኙት የሲቪል ሰርቪስ  ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ የተጀመረዉን  የብልጽግና ጉዞ  የተሳካ ለማድረግ ከአካዳሚዉ ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።

በሱሉልታ ከተማ የሚገኘዉ ነባሩ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በአሁኑ ወቅት 206 ተማሪዎችን በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ በማስተማር ላይ ይገኛል።(ኦቢኤን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top