Connect with us

ሀመር ቡስካ ተራራ ላይ የተተከለው የአቡነ ሙሴ ፀሊም ገዳም ተመርቋል። ከሀመር እስከ ጠረፍ ጠባቂዋ ደብር የጉዞ ማስታወሻ

ሀመር ቡስካ ተራራ ላይ የተተከለው የአቡነ ሙሴ ፀሊም ገዳም ተመርቋል። ከሀመር እስከ ጠረፍ ጠባቂዋ ደብር የጉዞ ማስታወሻ
ይርጋለም እሸቱ

ባህልና ታሪክ

ሀመር ቡስካ ተራራ ላይ የተተከለው የአቡነ ሙሴ ፀሊም ገዳም ተመርቋል። ከሀመር እስከ ጠረፍ ጠባቂዋ ደብር የጉዞ ማስታወሻ

ሀመር ቡስካ ተራራ ላይ የተተከለው የአቡነ ሙሴ ፀሊም ገዳም ተመርቋል። ከሀመር እስከ ጠረፍ ጠባቂዋ ደብር የጉዞ ማስታወሻ

(ይርጋለም እሸቱ ~ ድሬቲዩብ)

በጉጉትና በናፍቆት ስንጠብቀው የነበረው የቡስካ ደብረ ጽዮን ማርያም ወአቡነ ሙሴ ፀሊም ገዳም የምረቃ በዓል ጉዞ ቀኑ ደርሶ ከ አራት ኪሎ ዋናው ቢሮአችን ከ ሌሊቱ 10:30 ጀምሮ እስከ 12:30 ድረስ የመንገደኞች ዕቃ። ለተጠማቅያን ደበላ ነጠላ። 

ለገዳሙ ንዋያተ ቅዱሳት ከወንድማችን የተሰጠን ለአርብቶ አደሩ የሚከፋፈል 600 ቲሸርት። ከምዕመናን የተሰበሰቡ አልባሳት: በረሀው ላይ ለሚገኙት ከ50 በላይ ለሚሆኑ ማንም ለማይደርስባቸው በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ ብቻ በዚህ ኮሚቴ ለሚጎበኙ  አብያተክርስቲያናት ከልደታ ቤተክርስቲያን የተሰጠንን ጧፍ ዕጣን ዘቢብ ሻማ አልባሳት። 

ከማህበረ ስላሴ ዘልደታና ከአባ ገብረመድህን የተሰጡንን ሌሎች ለጉዞ የሚያስፈልጉንን ቁሳቁሶች ጭነን በመጨረሳችን የጉዞ ፀሎት በቀሲስ አበባየሁ ሰላም ዕለኪን በመድገም ፀሎት አድርሰን ጉዞአችንን ጀምረን አዲስ አበባ ከ 4ኪሎ ተነስተን በሜክሲኮ ልደታን ተሳልመን እዛ አካባቢ ያሉ ተጓዦችን ጭነን በብስራተ ገብርኤል ቁልቁል ወርደን ጀሞ ሚካኤልን እጅ ነስተን ከጀሞ ያሉትንም ጭነን ወደዓለምገና በመጓዝ በስተቀኝ የሚታጠፈውን ዋናውን የደቡብ መውጫ መንገድን ይዘን በቀሲስ አበባየሁ ቃለ እግዚአብሔርን እየተማርን በዘማሪ ቃል በቃል ዝማሬ እየተመሰጥን ጉዞውን ይዘነዋል።     

ጉዞአችን በቃለ እግዚአብሔር እየተቀመመ ቡኢን አልፈን ቡታጅራን ተሻግረናል። በመንገዳችን ስለምናቋርጣቸው ከተሞች ማብራሪያ እየተሰጠን ነው። ዝማሬያችንም ልዩ ነው። የደቡብ አየር ንፁህ ከመሆኑ የተነሳ ከዝማሬው ጋር ልብን ይመስጣል። መንገዱ ጥገና ስለተደረገለት የከፋ እንግልት የለውም ከቡታጅራ በኃላ አብዛኛዉን የሚታየው መስጂድና ሂጃብ የተሸፋፈኑ እህቶችን እያየን የወራቤ ከተማን አልፈን ሀልባረግ ከተማ ደርሰናል። 

ሁልባረግ ከተማ አንድ መንገድ ወደ ሆሳዕና ሌላኛው ወደ ሀላባ ይወስዳል። የኛም መንገድ በዚሁ ነውና ዋናውን መንገድ ለቀን በስተቀኝ በኩል ታጥፈን ጉዞ ላይ ነን። ሰዓቱ ረፍዷል። ምሳ “ቃለ እግዚአብሔር ነው” ተብሎ ነው መሰለኝ እስከአሁን አልተሰጠንም። ወላይታ አርሴማ ቤተክርስቲያን እስከምንደርስ መኮራረፋችን ነው እንግዲህ! ደግነቱ በመንገዳችን የሚነገረው ታሪክና ቃለ እግዚአብሔር ሁሉን ያስረሳል። አሁን ሰዓቱ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሆኗል። 

የመመገብ ፍላጎታችን በመጨመሩ ሀላባ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ምሳ ለመብላት ወርደናል። እህታችን አስራት በጉዞ ሁሉ ያስለመደችንን አገልግል አጣጥመን ሻይ ቡና ለጊዜው ተከልክለን በፍጥነት ገዞአችንን ወደ ወላይታ ቀጥለናል። በመንገዳችን “እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ድንቅ ነው” በሚል ርዐስ ዲያቆን ያሬድ ከሰዓሊተ ምህረት ግሩም ትምህርት ተምረናል። 

በደቡብ ኦሞ ካሉት 16 ብሔረሰቦች ውስጥ ስለ ብራይሌ በና ፀማይ ኤርቦሬ ሐመር ካሮ ኛንጋቶም ዳሰነች ሙርሲ ቦዲ ማሌ ጫሌ ሙሩሌ ዲሜና አሪ ብሔረሰቦች ባህል ቋንቋ አኗኗር ህይወት ታሪክ ተተርኳል። በብሔረሰቦቹ አካባቢ ስለተሰሩ አብያተ-ክርስቲያናት ገለፃ ተሰጥቷል። 

አሁን በመኪናው ውስጥ ያለን ሁላችን እርስ በእርሳችን እንጠባበቅ ዘንድ ትውውቅ እያደረግን ነው። መሀል ላይ ግን ወላይታ በመድረሳችን የድካም ስሜት ስለተሰማን ሻይ ቡና ለማለት ወርደናል።

ከሻይ ቡና ተመልሰናል። የመኪናው ውስጥ ትውውቁም ቀጥሏል። የዛሬ ተጓዦቻችን በቁጥር 70 ናቸው። ወንበር በፈረቃ የሚደርሰን 5 ነን። ትውውቁ በቀሲስ አበባየሁ አጋፋሪነት እንደቀጠለ ነው። በመንገዳችን በስተግራ በኩል በቅርብ ርቀት የጫሞ ሀይቅን በስተቀኝ በኩል አልፎ አልፎ የእርሻ መሬት አብዛኛው ግን መልማት የሚችልና ያልለማ ሰፋፊ ሜዳማ ቦታዎችን እየታዘብን የፈጣሪን ድንቅ ሥራ እያደነቅን በተፈጥሮ እየተደመምን ጉዞ ወደ አርባምንጭ ቀጥለናል። 

አሁን ጫሞ ሀይቅን ጨርሰን የአባያ ሀይቅ የተንጣለለ ሜዳ መስሎ ከፊት ለፊታችን መታየት ጀምሯል። በስተቀኝ በኩል የብርብር ማርያም መግቢያ ታፔላ ይታያል። ብርብር ማርያም በሀገራችን የኦሪት መስዋዕት ከተሰዋባቸው ታላቅ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ነው። ቦታውን እግዚአብሔር ቢፈቅድ ስንመለስ ከምናያቸው ቦታዎች አንዱ ይሆናል። 

አሁን ያለነው የአርባ ምንጭ የሙዝ ልማት ሰፋፊ መሬቶችን እያየን ነው። በዕውነት ግሩምና ድንቅ ከማለት ውጭ ፈጣሪ እንዲህ ያለውን ፀጋ ስለሰጠን ከማመስገን ሌላ ምን እንላለን? የጫሞና የአባያ ሀይቅ የሚገናኙበት ቦታ “የእግዜር ድልድይ” ተብሎ ይጠራል። 

የአርባ ምንጭ ከተማ በአዞ እርባታዋ: በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርኳ: በውስጧ በሚገኙ 40 ምንጮቿ: በጋሞ አባቶች የዕርቅና ችግር አፈታት ባህላቸው: በሙዝ ምርታቸው: በሽመና ስራ ታታሪነታቸው: ከሀገር አልፈው በዓለም የሚታወቁበት መገለጫዎቻቸው ናቸው። 

ስለእነዚህ የአርባ ምንጭ ዕሴቶች ቀሲስ አበባየሁ እያስተዋወቁን መንገዳችንን እያገባደድን ሲሆን ቀሪውን የ55 ኪሎ ሜትር ቀሪ መንገድ በኦሞ ዙሪያ ስለተሰሩ አብያተክርስቲያናት እና ስለ ተደረገው ተአምር እየተተረከልን እነሆ ከፍ ባለ ሆታና ዝማሬ በእግዚአብሔር ቸርነት በድንግል ማርያም ምልጃ በቅዱሳን ጸሎት በቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ በሰላም አርባ ምንጭ ቅዱስ ገብርኤል ገብተናል።  በሰላም አድረን ሌሊት 9:00 ሰዓት ለጉዞ እንገናኝ ሰላም እደሩ።

ይቀጥላል 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top